Ethio Inform
provide relevant information to society
01/10/2021
የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር
ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ዛሬ ይወያያል
ተባለ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ አርብ
በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ እንደሚወያይ ተገለጸ።
የምክር ቤቱ መርሃ ግብር እንዳመለከተው ቀደም ሲል ከተያዘ
ጉዳይ ውጪ በሆነ መድረክ የፀጥታው ምክር ቤት አባልት
በትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ ይወያያሉ ብሏል።
ይህ የምክር ቤቱ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰባት
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ከፍተኛ
ኃላፊዎች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደገቡ በመግለጽ
ከግዛቱ እንዲወጡ ካዘዘ በኋላ የሚደረግ ስብሰባ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔን ተከትሎ የተመድ ዋና ፀሐፊ
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በእርምጃው መደንገጣቸውን አመልክተው፤
ውሳኔውን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣንት ጋር
እየተወያዩ መሆኑን ገልጸዋል።
የአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጀርመን መንግሥታት
በዓለም አቀፉ ድርጀት የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች ላይ
የተወሰደው እርማጃ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ የኢትዮጵያ
መንግሥት ውሳኔውን እንዲያጤን ጠይቀዋል።
ዛሬ ይካሄዳል የተባለውን ይህንን የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ
እንዲካሄድ የጠየቁት የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ኢስቶኒያ ፣
ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዩክሬንና አሜሪካ ናቸው።
አስራ አምስት አባላት ያሉት ከፍተኛው የተባበሩት መንግሥታት
ድርጅት የውሳኔ አካል የሆነውን የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤትን
የፕሬዝዳንትነት መንበር ዛሬ በሚጀምረው የፈረንጆቹ የጥቅምት
ወር የምትረከበው ኬንያ ናት።
ምክር ቤቱ ለዛሬ በያዘው ስብሰባው በጥቅሉ በኢትዮጵያ
የትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ እንደሚወያይ የተነገረ ሲሆን፤
ሐሙስ ዕለት የኢትዮጵያ መንግሥት የመንግሥታቱ ድርጅት
ሠራተኞችን ከአገሩ እንዲወጡ የሰጠው ውሳኔ ላይ
እንደሚነጋገር ይጠበቃል።
በተጨማሪም በሠሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት
ሳቢያ የትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትንና ያለውን
አሳሳቢ ሰብአዊ ቀውስ በተመለከተ ሊወያይ ይችላል ተብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት የትግራይ ክልል ይፋዊ ባልሆነ የሰብአዊ
እርዳታ እገዳ ስር ነው ሲል የገለጸ ሲሆን፣ የድርጅቱ የሰብአዊ
እርዳታ ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ
በክልሉ ረሃብ ሳይከሰት እንደማይቀርም ብለው እንደሚገምቱ
መግለጻቸው ይታዋሰል።
ኃላፊው የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦት የያዙ
ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ እንዲያደርግ ጠይቀው
"ይህ ችግር ሰው ሰራሽ ነው፣ መንግሥት እርምጃ ከወሰደ
መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል" ሲሊ ለሮይተርስ ዜና ወኪል
ተናግረዋል።
ኒው ዮርክ ሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ተልዕኮ
በበኩሉ ወደ ትግራይ እርዳታ እንዳይገባ "እገዳ ተጥሏል
የሚባለው ክስ መሰረተ ቢስ ነው" ሲል አጣጥሎታል።
ጨምሮም የረድኤት ድርጅቶች "እርዳታ ለማቅረብ የሚያስችሉ
የጭነት ተሽከርካሪዎች እጥረት የገጠማቸው ቀደም ሲል ወደ
ትግራይ እርዳታ ለማድረስ የተሰማሩ መኪኖች ሳይመለሱ
በመቅረታቸው ነው" ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
በትግራይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የእርዳታ ድጋፍ
እንደሚያስፈልጋቸውና በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በረሃብ
ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የመንግሥታቱ ድርጅት ሲገልጽ ቆይቷል።
ይፋዊ ያልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ ተደርጓል የሚሉት
የተባበሩት መንግሥታት የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ
አቅርቦት ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ፤ ወደ ትግራይ መድረስ
ከሚገባው እርዳታ 10 በመቶ ብቻ ለተረጂዎች መቅረቡን
በመግለጽ በክልሉ ረሃብ ጉዳት እያስከተለ ነው ብለው
29/09/2021
ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን ለቀረፃ መጠቀምና ማብረር
በህግ ያስጠይቃል - የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት
ህጋዊ እውቅና ሳያገኙ ድሮኖችን የሚጠቀሙና ሲያበሩ የሚገኙ አካላት
በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት
አገልግሎት አሰታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ
አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ
በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ቀረፃ
የሚያካሂዱና ሲያበሩ የሚገኙ አካላት ከህገውጥ ከህገ ወጥ
ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሀገሪቱን ደህንነትና
ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም መሆኑ
አስታውሶ ÷ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን
ለቀረፃ ሲጠቀም እና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም
ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅ አስጠንቅቋል፡፡
FBC
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa