Zinash Tayachew
Philanthropist and Gospel Singer. Wife and Mother
10/04/2026
የቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት አንጀሊን ንድያይሺሚዬን ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ክቡር ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬጋ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት በብሄራዊ ቤተመንግስት ተቀብዬ ጉብኝት ያደረግን ሲሆን በነበረን ቆይታም በምንሰራቸው ስራዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ነበረን፡፡
07/04/2026
መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ለሚኖሩ ለ150 አቅመደካማና ዓይነስውራን ወገኖቻችን ማእድ አጋርተናል፡፡
የትንሳኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ፍቅሩን የገለጸበት በመሆኑ በዓሉን የምናከብር የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ማዕድ በማጋራት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን ፍቅር በተግባር የምንገልጽበት ይሁን እያልኩ መጪው የትንሳኤ በዓል የሰላም፣የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
ገበታ ለትውልድ የኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ
20/03/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
13/03/2026
የቁንድዶ ተራራ እና የተራራው ልዩ የዱር ፈረሶች አስደናቂ ውበት ያየንበት ጉብኝት
11/03/2026
በአስደማሚ ውበት የተሞላው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘው ናሲኦል ዋሻ
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘው ናሲኦል ዋሻ
27/02/2026
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር በአዘርባጃን በካሄድነው የኦፊሻላዊ ጉብኝት ወቅት፣ ከአዘርባጃን ቀዳማዊት እመቤት ክብርት መህሪባን አሊዬቫ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርጌያለሁ።
በቢሮአችን ቅድሚያ ሰጥተን በምንሰራባቸው ተጋላጭ ማህበረሰቦች በተለይም ሴቶች፣ ሕፃናት እና የአካል ጉዳተኞች ላይ ስላሉን ፕሮጀክቶች ማብራሪያ ሰጥቻለሁ። በማህበራዊ ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማምተናል፡፡
ተዛማጅ ማዕከላትን በመገንባትና የክህሎት ስልጠና በማመቻቸት ለመርዳት ዝግጁነታቸውን ገልጸውልኛል።
በቆይታዬ ወቅት በባኩ አቅራቢያ ያለውን ጋላ የአርኪኦሎጂና የባህል ሙዚየም እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች የእደ ጥበብ ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝቻለሁ። ጉብኝቱ በቢሮአችን በተጋላጭ ዜጎች ላይ የምንሰራውን ሥራ ለማጠናከር ጠቃሚ ልምድ አግኝቸበታለሁ።
ሁልጊዜ ስለሚረዳን እግዚአብሔር ይመስገን::
ሀዋሳ
ከ39ኛው የOAFLAD ስብሰባ ጎን ለጎን በአድዋ ሙዚየም ውስጥ ከውድ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች እህቶቼ ጋር ደስታና ትርጉም የሰጠንን ጊዜ በማሳለፋችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል።
ከመደበኛ ፍሪያማ ውይይቶቻችንና ልምዶቻችንን ከመካፈል ባሻገር ያሳለፍነው የእህትነት ጊዜ አንድነታችንን ያጠናክራል ፡፡በአንድነት ስንሰራ ለአፍሪካውያን ሴቶች እና ህፃናት የተሻለ ወደፊት መገንባት እንችላለን፡፡
15/02/2026
30ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም ጉባኤ መሪ ቃል "የአፍሪካን ሴቶች ፈተናዎችን የመቋቋም ዐቅም መገንባት፡- የአየር ንብረት፣ግጭቶች እና ዘላቂ ነገ” የሚል እንደመሆኑ የመሪ ቃሉ ዓላማ በጾታ እኩልነት፣ በጤና እና በትምህርት መርሐ ግብሮች፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የአፍሪካ ሴቶችን ዐቅም የበለጠ ማሳደግ ጠቃሚ ሚና አለው፡፡
በተለይ ደግሞ ሴቶችን ማዕከል ያደረጉ የማኅበራዊ ልማት ተግባራት የሴቶችን ዐቅም የበለጠ ስለሚያጎለብቱ ይሄንን ታሳቢ በማድረግ በፅ/ቤታችን ባለፉት ስድስት ዓመታት 37 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በተለያዩ አካባቢዎች ገንብቶ የሴቶችን እና የሕጻናትን የትምህርት ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ ሰርተናል፡፡
በተጨማሪም ለሴቶች የሞያና የንግድ ክሂሎት ሥልጠና፣ የመሥሪያ ቦታ፣ ግብአትና የመነሻ ካፒታል በማመቻቸት ሴቶች በገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ ተሠማርተው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ሕይወት እንዲቀይሩ አድርገናል፡፡
ሴቶችን በየዘርፉ ማሳተፍም ሀገርን በሙሉ እንደ ማሳተፍ ይቆጠራል፡፡ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ሊሳካ የቻለው ብዙ ሚሊዮን ሴቶች በፈቃደኝነት ስለተሳተፉበት ነው፡፡ የአየር ንብረት መዛባትን ለመቋቋምም ሆነ ሌሎችንም የአፍሪካ ችግሮች ለመቅረፍ፤ ሴቶች ወሳኙን ቦታ የሚያገኙበትን ዐውድ መፍጠር አለብን፡፡ ለዚህ ደግሞ እኛ ቀዳማዊ እመቤቶች ከፍ ያለ ኃላፊነት አለብን፡፡
14/02/2026
ከውድ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች እህቶቼ ጋር የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተናል፡፡ በአድዋ ድል የተመዘገበውን ታላቅ ታሪክ እያደነቅን በአፍሪካዊነት መንፈስ እርስ በእርስ ልናጠነክረው ስለሚገባን የአንድነትና የጽናትን ሀይል እየተወያየን በአድዋ ሙዚየም ውስጥ የምሳ ጊዜ በማሳለፋችን እጅግ ደስ ብሎኛል።
Together with my dear sisters, the African First Ladies, we visited the Adwa Victory Memorial Museum.
As we admired the great history recorded through the Victory of Adwa, we reflected on the power of unity and resilience, and on our responsibility to strengthen one another in the spirit of African solidarity.
I was truly delighted to spend our luncheon time together at the Adwa Museum.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa