VOFAD

VOFAD

Share

VOFAD works on prevention and mitigation of HIV/AIDS, and we address the reproductive health problems of communities through awareness creation

Photos 20/09/2022

ጉዳዩ፡- ከኤች.አይቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ 18 ህፃናትን ስለመደገፍ
ድርጅታችን እናትና አባታቸውን በኤድስ ምክንያት ያጡና (ወላጅ አልባ የሆኑ) ራሳቸውም ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ 18 ህፃናትን ዕድሜያቸው 18 ዓመት እስኪደርስ ድረስ በአደራ ተረክቦ ያሳድጋል፡፡ እነዚህ ህፃናት ድርጅታችን ከማህበረሰቡ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ከህብረተሰቡ ውስጥ በጎ ፈቃደኞች የሆኑ አሳዳጊ ሞግዚቶች ተገኝተውላቸው አስፈላጊው ሁሉ የምግብ፣ የህክምና፣ የትምህርትና መሰል ወጪዎች በድርጅቱ በኩል እየተሸፈኑላቸው በማደግ ላይ ይገኛሉ፡፡
ህፃናቱ ላይ አልፎ አልፎ ከሚታዩ የጤና ችግሮች በተረፈ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ሳይገለሉ ማደጋቸው፣ የመድሃኒታቸውም ሰዓት ሳይዛነፍ መውሰዳቸው፣ (የአገር ውስጥ ጉዲፈቻ አባትና እናት) በቤተሰብ ውስጥ የማደግ እድል ማግኘታቸው ህይወታቸው እስካሁን እንዲቀጥል አስችሎታል፡፡
ይህንን ስራ ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር የሚያከናውነው ድርጅታችን ቮለንቲርስ ኦፍ ፋሚሊ ዴቨሎፕመንት/ቮፋድ ይባላል፡፡ ቮፋድ እኤአ በ2001 የተመሰረተ መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ የማይሰራ አገር በቀል ወይም የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጊ ድርጅት ሲሆን ከፌደራል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በእናቶችና ህፃናት ዙሪያ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የሥራ ፈቃዱ ከጥር 9 ቀን 2008 ጀምሮ ለሚቀጥለው ሦስት ዓመታት በኤጀንሲው ታድሷል፡፡
ድርጅታችን ህፃናቱን ከአሳዳጊ ቤተሰቦች (ከጉዲፈቻ ወላጆቻቸው) ጋር በመተባበር እስከዛሬ ድረስ እየተንከባከበና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ከውጪ አገራት እያሰባሰበ ሲያሳድጋቸው የቆየ ቢሆንም የውጪ ዕርዳታና ዕገዛ ዘላቂነቱ አስተማማኝ ባለመሆኑ በአገራችን ውስጥ ከሚከኙ የግል ድርጅቶችና ተቋዋማት (Privet Sectors) ጋር የማህበረሰባዊ ሃላፊነት (Social Responsibilities) ትብብሮችን ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ቮፋድ የእርስዎን ተቋም ከመሳሰሉት ድርጅቶች (ተቋዋማት) ጋር ተባብሮ ለመስራት ያሰበበት ዋናው አላማዎች 5 ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
1. የ18ቱን ህፃናት የትምህርት ወጪ፣ የህክምናና የምግብ ወጪያቸውን (ቢያንስ ለአዲሱ /2015-2016፣17 ብቻ እሰከ ሚቻል ድረስ ለመሸፈንና) እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው የሚደረገውን መጠነኛ የገንዘብ ድጎማ ለመሸፈን፣
2. ህፃናቱ ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁና ክህሎታቸውንም እንዲያዳብሩ የኮምፒውተርና መሰል የኢንፎርሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በሽልማት እንዲያገኙ ማስቻል፣
3. ከዓመቱ ወራቶች የተወሰነ ጊዜ ከከተማ ወጣ እያሉ የመዝናኛና የመማማሪያ ፕሮግራሞች እንዲኖራቸው ማድረግ፣
4. ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩና የአሳዳጊ ቤተሰቦች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በግልጽ ማወቅ ስለሚኖርባቸው የስነ-ልቦና ዝግጅት ከወዲሁ እንዲያደርጉ የሚረዱ የምክክር አገልግሎቶችን ለመስጠት፣
5. የድርጅታችንን አቅም ለማሳደግና አስፈላጊውን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለማካሄድ እንዲችል ለማገዝ ነው፡፡
ከሰላምታ ጋር

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
P.O.B41434