Gerd network

Gerd network

Share

mobilization

01/04/2022

Great Ethiopia Renaissance Dam is a question of fairness!

24/03/2022

አባይ ወንዝና ተፋሰሱን አለማልማት በራስ ላይ ሞትን መፍረድ ነው፡

እንዳይለማ መከራከር ደግሞ በዓለም ብቸኛው ቀልድ ነው፡

ይህን ለመደገፍ መሞከርም የዩንቨርሳችን ብቸኛው ኢፍትኃዊነት ነው!

11/03/2022

ታላቁ ግድባችን ለኛና ለተፋሰሱ ሀገራት!

አባይ ኤሌክትሪክ እያመነጨልኝ ይፍሰስ በማለት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በመገንባት ላይ ትገኛለች። ይሁን እንጂ ሁለቱ የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት “ምን ሲሆን በአባይ ላይ ግድብ ይሰራል” በማለት የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ፕሮጀክቱን ለማስተጓጎል ሲሞክሩ ይታያል። ምክንያታቸው የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብታዊ ጥንካሬ የኃይል ሚዛን ሊቀይር ይችላል የሚል ስጋት ነው።

የአፍሪካ እና እስያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተፈራ ግን እንዲህ ይላሉ፡፡

“ህዳሴ ግድብ የግጭት ምክንያት ሳይሆን በጋራ የመልማትና የጋራ ተጠቃሚነት እቅድ ያነገበ ፕሮጀክት ነው”

“ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቀጠናውን አገራት በብዙ መልኩ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ከብክለት የፀዳ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን እውን የሚያደርግ ግዙፍ የአፍሪካ ፕሮጀክት ነው”

“ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ኢትዮጵያ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን እንድታንቀሳቅስ ያስችላታል”

“የቀጠናውን አገራት አውንታዊ ግንኙነት በማጠናከርም የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ ያስችላል”

“የንግድ ትስስር በማጠናከር፣ የማህበረሰብ ግንኙነት በማሳደግ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታን በማስፋት፣ ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ያደርጋል”

“ኢትዮጵያ ጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ እና ያላት ሰፊ የህዝብ ቁጥር ለዓረቡ ዓለም፣ ለኤስያ፣ ለአውሮፓ፣ ለመካከለኛው ምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል መግቢያ በር በመሆኗ ተመራጭ መዳረሻ ያደርጋታል”

በመሆኑም

“ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ መጠናቀቅ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው በማስቀጠል ከግብ እንዲደርስ ማድረግ አለባቸው”
ህዳር 13/2014 (ኢዜአ)

Photos from Grand Ethiopian Renaissance Dam's post 11/03/2022
Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Abeba
Addis Ababa