Nigat
This page is about telling the real truth that Ortodox church have.......
ሰሞኑን ከወደ ኦርቶዶከስ መንደር የደለበው ኑፋቄ ለምን ተነካ በሚል ጫጫታው በዝቷል። የሚገርመው ግን የጫጫታው ብዛት "ድንግል ማርያም የዓለም ቤዛ አይደለችም" የሚለውን አንድን የእውነት ቃል መቀየር አለመቻሉ ነው።
15/01/2021
ምንም እንኳ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ስምምነት ባይኖርም፣ የኬልቄዶን ጉባኤ (451 ዓ.ም) 4ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እየተባለ ይጠራል፡፡ ይሁን እንጂ ጉባኤውን ቀረብ ብለውያጠኑት ሰዎች ጉባኤውን በጉባኤነት ለመቀበል የሚቸገሩባቸውን በርከት ያሉ ምክንያቶች ያነሳሉ፡፡ እኔም ካስተዋልኳቸው ነጥቦች መካከል የተወሰኑትን በተከታታይ የማቀርብ ሲሆን ለአሁኑ በርዕስ ደረጃ ብቻ ልጠቁም፡፡
የመጀመሪያው፣ የኬልቄዶኑ ጉባኤ ከመከናወኑ በፊትና በኋላ የሊዮ አቋም አንድ አልነበረም፡፡ ለምሳሌ፣ ለምዕራቡ ገዢ ቫለንቲነስ፣ ለእናቱና ለእህቱ ለፑልቼሪያ በላከላቸው ደብዳቤዎች ውስጥ ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ (በኋላ የወንበዴዎች ጉባኤ ያለው) እግዚአብሔርን በመፍራት የተከናወነ ጉባኤ እንደ ነበር ገልጿል፡፡
ሁለተኛው፣ የኤፌሶኑ ጉባኤ (449 እ.ኤ.አ) ከመከናወኑ አስቀድሞ ሊዮ ለአውጣኬ በጻፈለት ደብዳቤ የንስጥሮሳውያንን የሁለት ባሕርያት እምነት ለመቃወም ያደረገውን ጥረት ማድነቁንና ለፍላቪያን በላከው ደብዳቤም አውጣኬን በቅን ልብ እንዲያየው ያሳሰበው መሆኑን ይታወቃል፡፡
ሦስተኛው፣ ሊዮ ጦማሩን ያዘጋጀው ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ ከመከናወኑ አስቀድሞ ሲሆን፣ ንጉሥ ማርሲያንና ንግሥት ብርክልያ ከ450 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡለት አድርጓል፡፡ ይህም ማለት ጉባኤው የተካሄደው በፊርማቸው ያጸደቁትን ጦማር በዓለም አቀፍ ጉባኤ ስም ሕጋዊ ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡
አራተኛው፣ በጉባኤው መጀመሪያ ላይ በሮሙ ጳጳስ ሊዮ የተወከሉ መልእክተኞች “የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የበላይ” ብለው በሚጠሩት በሊዮ በተሰጣቸው ተልእኮ መሠረት ዲዮስቆሮስ ከጉባኤው እንዲወጣ መጠየቃቸውና እርሱ ካልወጣ ጉባኤውን ለቀው እንደሚወጡ ማሳወቃቸው ነው፡፡ በዚህ መሠረት ዲዮስቆሮስ እንዲወጣ ተደረገ፡፡
አምስተኛው፣ በጉባኤው ላይ የተከሰተውና በበርካታ ጸሐፊዎች ትኩረት ያልተሰጠው፣ ዲዮስቆሮስ የተወገዘበት ሒደት ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዲዮስቆሮስን ጉዳይ እንዲመረምር ከተቋቋመው ቡድን ውስጥ አንዱ በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘ፣ በኬልቄዶን ጉባኤ እንዲገባ በመደረጉ ከጳጳሳት ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶበት የነበረና የዲዮስቆሮስ ከሳሽ ተብሎ በጉባኤው እንዲገኝ የተደረገ ሰው ነው፡፡
ስድስተኛ፣ ጉባኤው ከንጉሥና ከሮም ጳጳሳት ተጽዕኖ ነጻና ገለልተኛ አልነበረም፡፡ አስቀድመው ያቀዱትን ሐሳባቸውን ነው ተግባራዊ ያደረጉበት፡፡
ስባተኛ፣ በኬልቄዶን የተሰበሰቡት አባቶች የእምነት መግለጫ ያዘጋጁት በንጉሥ ማርሲዮን ተደጋጋሚ ጫና ነው፡፡ እንዲሁም የእምነት አቋም መግለጫውን እንዲያዘጋጅ የተመረጠው ቡድን አርቅቆ ያቀረበው “አንድ አካል አንድ ባሕርይ” የሚል ሲሆን የፖፕ ሊዎ መልእክተኞች፣ ይህ ሐሳብ “አንድ አካል ሁለት ባሕርያት” በሚል ቃል ካልተተካ በቀር ጉባኤውን ለቀን እንወጣለን በማለታቸው “አንድ አካል አንድ ባሕርይ” የሚለው ወጥቶ “አንድ አካል ሁለት ባሕርያት” በሚል ቃል እንዲተካና እንዲጸድቅ የተደረገ ነው፡፡
ስምንተኛ፡- ጉባኤው የቀደመውን የእምነት መግለጫ ወይም የእምነት መግለጫው የተመሠረተበትን አስተምህሮ ሳያወግዝ ሌላ ዐዲስ መግለጫ ያዘጋጀ ነው፡፡ የቄርሎስን ትምህርት አላወገዘም፣ ዲዮስቆሮስንም ያወገዘው በአስተዳደራዊ ግድፈት እንጂ በትምህርት ችግር አይደለም፡፡ እነዚህ አባቶች የሚያምኑት “አንድ አካል አንድ ባሕርይ” ሲሆን ኬልቄዶን ግን ይህንን ትምህርት ሳያወግዝ ከትምህርቱ ጋር የሚቃረን “አንድ አካል ሁለት ባሕርያት” ብሎ መግለጫ አወጣ፡፡
ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት የኬልቄዶንን ጉባኤ የማይቀበሉበት ምክንያት በአጭሩ ይህን ይመስላል፡፡
ባዩ ታደሰ፣ “ኦርቶዶክሳውያን” የሚፈሩት ኦርቶዶክሳዊ እውነት፡ “የቃላት እንጂ የመሠረተ እምነት ልዩነት የለንም”፣ ህዳር 2013፤ገጽ 53-79
05/11/2015
ቤተ ክርቲያን “ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የቤተ ክርስቲያን ምንነት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የተጠሩ ሰዎች ስብስብ ጉባኤ ወይም ማኅበር ናት እንጂ ሕንፃ ወይም ሌላ አይደለችም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቤት ለመሆን እንደሕያዋን ድንጋዮች በሚገነቡ ምዕመናን የተሞላች መንፈሳዊት ሕንፃ ናት ኤፌ. 2÷20-22 1ኛ ጴጥ.2÷4-5፡፡ ብዙ ብልቶች የያዘች አንድ አካልም ናት 1ኛ ቆሮ.12÷12-27፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ አካል ነች ይህም ሁሉን በሁሉ የሚሞላ ሙላቱ የሚገለጽባት ታላቅ መንፈሳዊ አካል መሆኗን ያመለክታል ኤፌ.1÷22-23፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት የክርስቶስ አካል ናት እንጂ ብዙ አካላት አይደለችም፡፡ ለትምህርተ ሐዋርያት የታመኑ ብዙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለአደረጃጀት እና ምዕመናንን ለመጠበቅ እንዲመች ቢኖሩም ብዙ አካላት ግን አይደሉም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተሠራች በመሆኗ የገሀነም ደጆች አይችሏትም ማቴ.16-18፡፡ ቤተ ክርስቲያን የማን ነች አንዳንዶች በተለምዶ ቤተክርስቲያኔ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይህ ስህተት ሲሆን የቤተክርስቲያን ባለቤት ራሱ የሠራት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ማቴ.16÷18 ኤፌ. 5÷23፣25-27 የሐዋ. 20÷28፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የማንም አይደለችም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ሠሪ እና ራሷም ነው ኤፌ.5÷23፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያን እረኞች አለቃም ነው 1ኛ ጴጥ.5÷2-4፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያን እረኞች ወይም አለቆች (መሪዎች) ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠየቂዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ያለው ዓላማ ያለነውርና እድፍ የሆነች ንጽሕት ቤተክርስቲያን ለራሱ ማቅረብ ኤፌ. 5÷25-27፡፡ በቤተክርስቲያን በኩል ወንጌልን ለሰዎች በማድረስ ደቀመዛሙርት ማድረግ ማቴ.28÷18-20 የሐዋ.ሥራ 1÷7-8፡፡ ለዘላለም በመንግሥቱ የሚኖር አንድ ሰማያዊ ቤተሰብ መፍጠር ኤፌ. 2÷19 የቤተ ክርስቲያን ምግባራት ቤተክርስቲያን ፣ ወንጌልን መስበክ፣ ሥርዓተ ጥምቀትን መፈጸም፣ ያመኑትን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማድረግ ማቴ.28÷18-20፣ ስርዓተ ቁርባንን መፈጸም 1ኛ ቆሮ.11÷23-26፣ ሥርዓተ ጋብቻን መፈጸም፣ ምእመናንን ማነጽ 2ኞ ቆሮ.11÷23-26፣ ሥርዓተ ጋብቻን መፈጸም፣ ምእምናንን ማነጽ 2ኛ ቆሮ.10÷8 እና ባልቴቶችንና ደሃ አደጎችን የመንከባከብ ትልቅ ኃላፊነት አለባት 1ኛ ጢሞ.5÷16 ያዕቆብ 1÷27፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ማኅበረ ምዕመናንና አገልጋዮች ለቤተክርስቲያን መሪዎች ሊታዘዙ ይገባል ዕብ.13÷17፡፡ ቤተ ክርስቲያን በሐሰት ትምህርት የተገኘውን የመለየት ሥልጣንም አላት፡፡ የቤተ ክርስቲያን አራቱ ምልክቶች “ከሁሉ በላይ የምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡ 1. ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ ክርስቶስ አንድ እንደሆነ ሁሉ በምንም ሁኔታ ይሁን ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት (ዮሐ.17÷21) ቤተ ክርስቲያን መከፋፈል አትችልም ከተከፋፈለችም አንድ መሆን አትችልም አንድ መሆን ካልቻለች ቤተ ክርስቲያን መሆን አትችልም፡፡ 2. ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ናት፡፡ ቅድስና የቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮና ባህርይ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን በመቀደሰ በመምራትና በመጠበቅ ሥራ ላይ ነው፡፡ (ኤፌ.5÷26-27) ክርስቶስም በቃሉ እድፈት ነውር እንዳይኖርባት ያነጻታል፡፡ 3. ቤተ ክርስቲያን በሁሉም ስፍራ ያለች ዓለም አቀፋዊት ናት፡፡ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን የዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን አካል ናት፡፡ ( ማቴ.28÷19፣ ማር.16÷8) 4. ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት፡፡ ጌታ ለሐዋርያት አባቴ እኔን እንደላከኝ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ (ዮሐ.20÷21) ጌታ ሐዋርያትን ደቀ መዛሙርት አድርጉ በማለት ታላቅ አደራ ሰጠቷቸዋል፡፡ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፡፡ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ (ኤፌ.2÷20)
http://nigat.net/%e1%89%a4%e1%89%b0-%e1%8a%ad%e1%88%ad%e1%89%b2%e1%8b%ab%e1%8a%95/
ቤተ ክርቲያን ቤተ ክርቲያን “ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የቤተ ክርስቲያን ምንነት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የተጠሩ ሰዎች ስብስብ ጉባኤ ወይም ማኅበር ናት እንጂ ሕንፃ ወይም ሌላ አይደለችም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቤት ለመሆን እንደሕያዋን ድንጋዮች በሚገነቡ…
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
USSR
Addis Ababa