FLAG OF ETHIOPIA

FLAG OF ETHIOPIA

Share

The colours of African unity (red, green and yellow) are seen here on one of the oldest African flags

28/07/2024

እስከ አሁን 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት በዓይነት እንዲሁም 16 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን የተከሰተውን የመሬት መንሸራተት አደጋ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ ገልፀው ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
አደጋው በስፍራው ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የክልሉ መንግሥት የአፋጣኝ የነፍስ አድን ስራና የሰብዓዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው በቀጣይም የክልሉ መንግስት የተጎዱ ወገኖችን የመደገፍና መልሶ የማቋቋም ስራን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ በፊትም በአካባቢው የዝናብ ወቅት የጎርፍ አደጋ የመድረስ ሁኔታዎች በመኖራቸው የክልሉ መንግስት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራ ሲሰራ እንደነበር የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ሁለት ቤተሰቦች ሙሉ በሙሉ በናዳ በመዋጣቸዉ እነሱን ለመታደግ በወጣው ቁጥሩ ከፍ ያለ ህዝብ ላይ ያልተጠበቀ ናዳ መጥቶ የዜጎችን ህይወት መቅጠፉን አስረድተዋል።
በደረሰው ከፍተኛ አደጋ እስከአሁን በተደረገዉ ፍለጋ የ232 ወገኖች ህይወት መጥፋቱን ገልፀው 10 ሰዎች በህይወት ተገኝተው የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው በመልካም ሁነታ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የክልሉ መንግስት በዘላቂነት ጉዳት የደረሰባቸውን ለመደገፍ ከፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጸው እስከአሁን በተደረገው ድጋፍ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ በዓይነትና 16 ሚሊዮን በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ዕቅድ አዘጋጅቶ እየሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተፈጠረው አደጋ ከ5 መቶ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ከ 6 ሺ በላይ ዜጎች የመሬት ናዳ ሊደርስ በሚችልበት ተጋላጭ ቦታ ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አደጋ አስቀድሞ ከመከላከል አንጻር የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቋሞ በመስራት ላይ ሙኑን ተናግረዋል።
በደረሰው አደጋ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የክልል መንግስታት፣ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የአከባቢው ማህበረሰብ፣ አርቲስቶች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና አለም አቀፍ መንግስታት በማድረግ ላይ ስላሉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

Photos from FLAG OF ETHIOPIA's post 28/07/2024

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን በአደጋው ​​ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል።
በአስተዳዳሪው በአቶ ጥላሁን ከበደ የተመራ የልኡካን ቡድን፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ቄንጮ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መደርመስ አደጋ የተጎዱ እና የተጎዱ ዜጎችን አጽናንቷል።

የጉዞ ማስታወሻ 2 Gamo Gofa Arba Minch {'አርባ ምንጭ'} (Amharic, "forty springs") 15/05/2024

በ ህትመት ለይ ያለው በቅርብ ቀን ለንባብ የሚበቃው የምድረ ገነት አርባምንጭ ጋሞ ዞን ባህል ፣ የአኗኗር ስርአት ፣ የተፈጥሮ በረከቶቿ
በ መክተው ቢያድግልኝ ክፍል 2
https://youtu.be/qkWlGvgr8d0?si=a1e9wS4x4gZytvZS
The culture, lifestyle, and natural blessings of the Medre genet Arba minch Gamo Zone, which will be available for reading in the near future.
Part 2

የጉዞ ማስታወሻ 2 Gamo Gofa Arba Minch {'አርባ ምንጭ'} (Amharic, "forty springs") Arba Minch {'አርባ ምንጭ'} (Amharic, "forty springs") is a city in southern Ethiopia; less common names for this city include Ganta Garo and Minghi. Located in t...

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa
ETH