GebetaTube
Gebeta Tube art & entertainment
23/03/2026
“የልጃችን እውነት ዛሬም ድረስ አልወጣም እና እስኪወጣ እገዛችሁ አይለየን”
ቀነኒ አዱኛ ህይወቷ ካለፈ ያሳለፍነው ሳምንት አንድ አመት ሞልቷታል። እሁድ ጠዋት አንደኛ ዓመቷን ለመዘከር ቤተሰብ እና የተወሰነ ሰው ስላሴ ቤተክርስቲያን ተሰብስቦ ነበር።
ሁሉም ቤተሰብ ውስጥ ለእህት ወንድም እንደ እናት ፤ ለእናት አባት ደግሞ ችግር ተካፋይ የሚሆኑ ልጆች አሉ። ቀነኒ ለቤተሰቧ ያን አይነት ልጅ ነበረች። የእናት በማመን እና ባለማመን መካከል መቸገር፣ የአባት ጠንክሮ ማጠንከር ውስጥ መባዘን እና የወንድም እና እህት አንገት መደፋትን ማየት ከምንም በላይ ያማል።
ቤተሰብ ዛሬም ድርስ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ምላሽ እና እገዛን እየጠበቀ ይገኛል። “የልጃችን እውነት ዛሬም ድረስ አልወጣም እና እስኪወጣ እገዛችሁ አይለየን” ሲሉ አባቷ አቶ አዱኛ ዋቆ መልዕክት አስተላልፈዋል። ቢዘገየም የመንግስት ተቋማት ለልመናቸው ምላሽ ይሰጣሉ የሚል ተስፋ አለኝ።
ዛሬም ስለ ቀነኒ ማውራት መጠየቅ እንቀጥል። የቀነኒ ጉዳይ ብዙዎች ዘንድ የደረሰ እና ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ነው። እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ሲኖሩ የሚፈፀሙ በደሎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ለማሳየት አስረግጦ ሀሳብን ማቅረብ የግድ ነው። በሴቶች መብት ጉዳይ በሀገራችን ላይ ያለውን አመለካከት እና ‘conversation’ በደንብ ቅርፅ ያስያዘ ያለ ጉዳይም ነው።
ነፍስሽ በሰላም ትረፍ 🕯️🕊️
You have touched so many hearts, your impact will go on and you will be remembered.
Via Suad Ahmed
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa