Delanta Tube.com
share trusted news videos and photo
ከ‹‹እከሌን ፍቱት!›› ወደ ‹‹እከሌን የት አደረሳችሁት!››? (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
ዛሬ እህቴ በጠዋት ከሀዋሳ ደውላ፣ ‹‹ትዝ ይልሀል በወያኔ ጊዜ፣ ያኔ አንተ በፍትህ ጋዜጣ ላይ በምትጽፍበት ዘመን?›› ስትለኝ፤ ‹‹ምኑ ነው ትዝ የሚለኝ?›› አልኳት፡፡ ‹‹እከሌ ይፈታ! እያላችሁ ነበር የምትጽፉት፤ ዛሬ የፌስቡኩና ዩቲዩቡ ቅኝት ‹‹የት አደረሳችሁት? ሆኗል›› አለችኝ፡፡ . . . . ሀዘን ተጫነኝ፤ ተከዝኩ፤ ጠዋቴን በተብሰልስሎት አሳለፍኩ፡፡ . . . .
በላይ በቀለ ወያ ከጠፋ ቀናት እየተቆጠሩ ነው፡፡ ብዙዎች ‹‹መንግስት አፍኖታል›› ብለው እየከሰሱና ምላሽ እንዲሰጥ እየወተወቱ ነው፡፡ ‹‹ለምን መንግስት ባልተረጋገጠ ጉዳይ ይከሰሳል?›› የሚሉም አሉ፡፡ በሁለት ምክንያቶች የተነሳ የመንግስትን ከሳሾች ሀሳብ እጋራለሁ፡፡
የመጀመሪያው ምክንያት፤
መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወንጀል የሚጠረጥራቸውን ሰዎች የሚያስረው ህግን ተከትሎ ሳይሆን፣ ካሉበት ሄዶ በማፈን ነው፡፡ ህግን ለማስከበርና ወንጀልን ለመከላከል እንኳን ቢሆን ህገወጥ መንገድ መከተል እራሱ ህገወጥነት ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ አንድ ዜጋ (በተለይ መንግስት ላይ የተቃውሞ ሀሳብ የሰነዘረ) ሲጠፋ የመጀመሪያው ተጠርጣሪ መንግስት እንዲሆን አድርጓል፡፡ ህግን ተከትሎ ተጠርጣሪን መያዝ የሚችል መንግስት ህገወጥነትን የሚመርጥበት ምክንያት አይገባኝም፡፡
ሁለተኛው ምክንያት፤
መንግስት ዜጎች ሲጠፉ የሚያሳየው ዝምታ ነው፡፡ ልጅ ሲጠፋ ቀድሞ የሚጮኸው፣ የሚፈልገው፣ አፋልጉኝ የሚለው የቤተሰብ አስተዳዳሪው (አባወራ ወይም እማወራ) ነው፡፡ ዜጎች ሲጠፉ መጮህና ፍለጋ መውጣት የፖሊስ (መንግስት) ሀላፊነት ነው፤ ዋና ፈላጊው መሆን ያለበት እሱ ነው! ቤተሰብና ዜጎች አፈላላጊ ናቸው፡፡ እንዴት ነው አንድ ሰው ጠፋ ሲባል ፖሊስ ‹‹የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ›› የሚለው? እና መንግስት ተከሳሽ የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፡፡
‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› - ይህ ድርጊት የመንግስት ባህርይ ሆኖ መቀጠልም፤ መወሰድም የለበትም፡፡ እዚሁ ላይ መስተካከል አለበት፡፡ ይህ የማይሆንና የመንግስት አፋኝነት በዜጎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ካገኝ፣ ነገ ማንኛውም ቡድን ዜጎችን እያፈነ ለመውሰድና ለማሰቃየት ብሎም ለመሰወር ትልቅ ቀዳዳ ይፈጥራል፡፡ . . .. . . መንግስት ይህን ድርጊት ማቆም አለበት፡፡
ጤናማ ማህበረሰብ የሚቆመው በህግ የበላይነት ብቻ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አንድ ሰው በወንጀል ከተጠረጠረ በህጋዊ መንገድ በህግ እንዲጠየቅ የህዝብም ፍላጎት ነው፡፡ በመሆኑም፣ መንግስት በወንጀል የሚጠረጥራቸውን በግልጽና በህግ መሰረት መጠየቅ አለበት፡፡ ይህ ሲሆን ከእሱ እውቅና ውጭ የሚሰወሩ/የሚታፈኑ ሰዎችን ጉዳት ሳይደርስባቸው በፊት ሊታደጋቸው ይችላል፡፡ አይበለውና በላይ በቀለ ወያ የታፈነው በወንጀለኛ ቡድን ቢሆን እኮ ያለ ፖሊስ ክትትል ባለፈው ሶስት ቀን የፈለጉትን ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
እባካችሁ!
27/03/2022
30/09/2021
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ
************************************
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ሀላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በራሄል ፍሬው
26/09/2021
ከጀነራል አበባው ወቅታዊ ንግግር የተወሰደ..!
"..የእነሱ ትልቁ ሀይል #ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን #ኢትጵያዊነት ነው...!!"
ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ
[የጦር ሀይሎች ም/ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ]
አሸባሪዎቹ ህወሓቶች ከጦርነቱ በፊት ከጀርባ ይዘውት የነበረው ዓላማ የእነሱን ጥቅም በኢትዮጵያ ላይ መጫን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ካለ አብሮ ለመስራትና የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት በጉልበት ጠምዝዘው የራሳቸውን ፍላጎት ማሟላት የሚል ነው፤ ይሄ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነበር ዓላማቸው...።
ለዚህ ዓላማ መሳካት ደግሞ ወታደር ያስፈልገናል ብለው ህጋዊ የሆነውን ልዩ ሀይል እንደ ሽፋን ተጠቅመው ከ200 ሺህ በላይ ሰው ያለበት ሀይል አደራጅተው ነበር..።
የጀመረው ጦርነት ዓላማውም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው፤ እኛ ደግሞ የተከተልነው ስትራቴጂ ኢትዮጵያን ከብተና የማዳን ነው፤ የጦርነቱ ፍትሀዊነት የሚመነጨውም ከዚህ ነው...።
የጦርነቱን ዋነኛ ማዕከል መቀሌን አድርገን በፍጥነት በመሄድ ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ መቀሌን መቆጣጠር አለብን ካልሆነ አደጋ ነው ብለን አንድ ሰው እንደ አስር እየተዋጋ በፍጥነት ጨርሰናል...።
በሰው ሀይል ማደራጀት እነሱ ይበልጡን ነበር፤ ነገር ግን የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው...።
የኢትዮጵያዊነቱ መንፈስ እንደገና ደግሞ ዩኒፎርም ለብሰህ ዩኒፎርም የለበሰህ ጓደኛህ ከኋላህ ሲመታህ የሚፈጥረው መንፈስ አለ ያንን ጉልበት ይዘን ነው የተዋጋነው...።
ከሰራዊት አንጻር ያስቀመጥነው ግብ አሳክተናል፤ የታገቱብንን አባሎቻችንን አስለቅቀናል፤ የተወሰዱብንን ብረትና ተተኳሽ አስመልሰናል፤ ኢትዮጵያን አድነናል...።
ህወሓትን እንደ ድርጅት በትነነዋል፤ የሚደመሰሰውን ደምስሰናል፤ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የነበረውን የድርጅቱን አስኳል በትነን ለሰባትና ስምንት ወራት ዋሻ ውስጥ ከተናል፤ የቀረውን ደምስሰናል...።
ኢትዮጵያን ሁሌም የሚወጋት የእኛ የራሳችን ሰው ከውጭ ሃይል ጋር በመሆን ነው..!!
የውጭ ሃይል ቀጥታ አይመጣም፤ የውስጥ ሰውን እየያዘ ነው እየተዋጋን ያለው፤ ከውጭ የሚመጣው ጠላት በግልጽ ቢመጣማ ኖሮ ምንም ችግር አልነበረም...።
ኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ሰው የፈለገውን አስተሳሰብ፣ የትኛውንም እምነት ይከተል፤ የትኛውንም ፖለቲካ ይከተል እኛ አያገባንም..!!
ኢትዮጵያን ከነኩ ግን ከውጩ ሰው ሳይሆን የምንጀምረው ከራሱ ነው፤ የራሳችንን ቤት ቆሻሻ ካላጸዳን ኢትዮጵያን ማቆም አንችልም...።
በአሁኑ ወቅት መከላከያ በስፋት ነው እየተጠናከረ ያለው በትጥቅ፣ በአየር ሃይላችን፣ በእግረኛ ሃይላችን፣ ሊገመት በማይችል አይነት መልኩ ነው እየተዘጋጀን ያለነው...።
መከላከያን ማጠናከር ለማንኛው ኢትዮጵያዊ በሩ ክፍትነው፤ ማንም ሰው መከላከያን መቀላቀል ይችላል፤ መደገፍ ይችላል፤ ማረም ይችላል ምክንያቱም የራሱ ሀብት ነው...።
የውስጥ እና የውጭ ስጋት አለብን፤ የውስጥ ስጋቱ ጊዜ የሚፈጅ አይደለም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚስተካከል ነው....።
ለውጩ ስጋት ጠንክረን መዘጋጀት አለብን፤ በዚህ ሁለት አመት መከላከያ ፍጹም ሙሉ ለሙሉ ይቀየራል...።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ይሄ ጊዜ መለማመጃችን ይሆናል።
እኛ የሚያስፈልገን ዘር አይደለም፤ ሰውነታችን ነው፤ ሰውነታችን ካለ አገር አለ...።
17/09/2021
አብዛኞቹ የሰበአዊ አርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከመቐለ አልተመለሱም - የዓለም ምግብ ፕሮግራም
አዲስ አበባ ፣መስከረም 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰበአዊ አርዳታ ጭነው መቐለ የገቡ አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች አልተመለሱም ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።
በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ እንዳስታወቀው የዕርዳታ እህል እንዲያደርሱ 466 የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ መቐለ ቢላኩም የተመለሱት 38ቱ ብቻ ናቸው።
ቢሮ እንደሚለው ለትግራይ ህዝብ የሰበአዊ አርዳታ ለማድረስ ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልጉት ገልጾ ጉዳዩ እንዳሳሰበው አስታውቋል።
አሸባሪው ህወሓት ተሽከርካሪዎችን በመውሰድ ለጥፋት ተግባሩ መፈፀሚያ እያዋላቸው እንደሆነ የሚያሳዪ መረጃዎች ከሳምንታት በፊት ሲወጡ ነበር።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the establishment
Website
Address
Addis Ababa
1000