Addis Ababa Police
መሪ ቃል፦ በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!!!
እሴቶቻችን፡- ሙያዊ ብቃት፣ ምሉዕነት፣ ብዝሃነትን ማክበር፣ ሰብዓዊ መብት ማክበር
Motto: Protect with courage Serve with Compassion!
02/06/2026
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የድምፅ መስጫ ሂደቱ እስከ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ሲከናወን ቆይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግንቦት 24 ቀንም ሆነ ሌሊት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙ ተገልጿል።
ድምጽ የመስጠት ስርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላት ኮማንድ ፖስቱ ምስጋናውን አቅርቧል።
ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል።
ድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ጥሪውን አቅርቧል።
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
01/06/2026
በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተጣለበትን ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ ስለመሆኑ ማምሻውን ገመገመ።
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ እና በአዲስ አበባ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ሊዲያ ግርማ በተመራው መድረክ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዦች ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድና ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ እና የየተቋማቱ የጸጥታ አመራሮች በተገኙበት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የጸጥታ ሁኔታ ማምሻውን ተገመገመ።
የምርጫ ኮማንድ ፖስቱ ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተጣለበትን ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ ስለመሆኑ እንዲሁም በምርጫው ዋዜማና በምርጫው ዕለት የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት ገምግሟል።
ግምገማው የክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ኃላፊዎች ከነ ማኔጅመንታቸው በዙም በተደረገ ስብሰባ ጭምር የተደረገ ሲሆን አጠቃላይ በመዲናዋ እየተከናወነ ያለው የምርጫ ሂደት ሠላማዊ እንደሆነም ተገልጿል።
ጥምር የጸጥታ ኃይሉ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስም የጸጥታና ደህንነት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
*
ዘገባ፡- ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
30/05/2026
በምርጫና ድህረ ምርጫ ቀናት በሚከናወኑ የፀጥታ ማስከበር ተግባራት ምርጫው ሠላማዊ እንዲሆን አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሠላም አዳራሽ በቅድመ ምርጫ የተከናወኑ ተግባራትን ለመገምገም በተዘጋጀው መድረክ የአዲስ አበባ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ፣ የከተማው ሠላምና ጸጥታ ቢሮ አስተዳደር ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዦች ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እና ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ፣ የአስራ አንዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ እና የወረዳ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የጸጥታ አካላት አስቀድመው የጋራ እቅድ በማውጣት ወደ ተግባር በመግባታቸው ቅድመ ምርጫው በጥሩ ሁኔታ ማከናወን እንደተቻለ በውይይቱ ተነስቷል።
የምርጫን ደህንነት የማረጋገጥ ተግባር ልዩ ጥንቃቄን የሚሻ ተግባር መሆኑን ሌ/ጀነራል አስራት በውይይቱ ላይ ገልፀው ቀሪ ተግባራት ካሉ ማጠናቀቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በምርጫው ላይ አሉታዊ ጫና ለማሳደር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች እንዳሉ በመረዳት በምርጫ ዕለት እና ድህረ ምርጫም በስኬት እንዲጠናቀቁ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የዋናው ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አስታውቀዋል።
የጸጥታ ስራችን ለህብረተሰቡ ደህንነትን ያረጋገጠ ለጸረ-ሠላም ኃይሎች ጫናን የሚያሳድር መሆን እንዳለበት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ባደረጉት ንግግር ገልጸው በተለይ ፀጉረ-ልውጦችን ለመቆጣጠረ በሸገር ከተማ ስር ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ ቅድመ ምርጫ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ተገምግሟል።
ምርጫው ያለ ምንም የፀጥታ እንከን እንዲከናወን ህብረተሰቡ ማንኛውም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪ ተላልፏል።
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
29/05/2026
ተቀጥራ ከምሰራበት መኖሪያ ቤት ከ1ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ንብረቶችን የሰረቀች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተከሳሽ ዓለም ሲሳይ የተባለች የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በልዩ ስሙ አትሌቶች መንደር ነው።
በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ያለ ምንም ተያዥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የአሰሪዎቿን እንቅስቃሴ በሚገባ ስታጠና የቆየችው ተጠርጣሪዋ በተቀጠረች በ9ኛ ቀኗ የተለያዩ አልባሳት እና መዋቢያ ጌጣጌጦችን፣ የአሜሪካን ዶላር 500፣ የቻይና ሀገር ዩዋን 400፣ የህንድ ሩፒ 600 የCCtv ካሜራ ዳይመንድ የጣት ቀለበት በአጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው አንድ ሚሊየን አራት መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ብር (1,423,192.00) የሚያወጡ የተለያዩ ንብረቶችን ሰርቃ ከአካባቢው መሰወሯን የግል ተበዳይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ጎሮ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው አመልክተዋል፡፡
የጎሮ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ ባደረገው ክትትል ተከሳሿን ከነሙሉ ኤግዚቢቱ ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጥቷት የተወሰኑ ኤግዚቢቶችን በመሸሸግ የተባበራትን ተጠርጣሪ ከሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B-95611 አ/አ ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን ጭምር የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ለክፍሉ አቃቤ ህግ በማቅረብ ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡
ህብረተሰቡ ማንኛውንም ዓይነት ቅጥር ሲፈፅም ህጋዊነትን በተከተለ መልኩ ቢሆን የተሻለ መሆኑን ያስገነዘበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላትም ከወንጀል ፈፃሚዎች ጋር በጥቅም ተሳስረው የወንጀል ተጠያቂ ላለመሆን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
*
ዘገባ ፦ ዋና ሣጅን አዳነ ደስታ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
29/05/2026
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አዲስ የተሾሙትን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፎች አስተባባሪና ልዑካቸውን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፎች አስተባባሪ ተደርገው የተሾሙትን ናይጄሪያዊውን ኦዞኒያ ኦጂሎንና ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
አስተባባሪው በትውውቃቸው ወቅት እንዳነሱት የአዲስ አበባ ከተማ ዕድገት ከዕለት ወደ ዕለት የመላው አፍሪካውያንን ቀልብ እየሳበ መሆኑን ገልጸው በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከዋና ጠቅላይ መምሪያው ጋር አንድ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረው ኢትዮጵያ በቀጣይ በ2027 ለምታካሂደው 32ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እያደረገች ያለችውን ቅድመ ዝግጅት አደንቃለሁ ብለዋል፡፡
በአሁን ወቅት እየተሰሩ ያሉ ተቋማዊ አዳዲስ ተግባራት መጀመራቸውን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀኔራል አስራት ደኔሮ ከተማዋን የሚመጥን የወንጀል መከላከልና የፀጥታ ማስጠበቅ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2027 32ኛውን የተ.መ.ድ. /UN/ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንድታካሂድ መመረጧ የሚታወስ ነው።
*
ዘገባ፡- ም/ሳጅን መልካሙ ዜና
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Arada Sub City , Addis Ababa Police
Addis Ababa
5647