Eden Eden

Eden Eden

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eden Eden, Grocers, Addis, Addis Ababa.

Photos from Eden Eden's post 22/06/2026

የሸገር ዳቦ ምርት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሸገር ዳቦ አቅራቢ ማህበራት ለማህበረሰቡ የሚያቀርቡትን ምርት በጥራትና በተደራሽነት ማቅረብ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ ላይ ማህበራቱ የዳቦ ምርትን በአግባቡ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ በስፋት የተመካከሩ ሲሆን ማህበራቱ የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትም የጋራ ምክክር ተደርጓል።

በተጨማሪም ማህበራቱ በስራ ሂደት ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ ውይይት ተደርጓል።

ዉይይቱን የመሩት የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የአቅርቦት ሰንሰለቱን ውጤታማ ለማድረግና የዳቦ ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማህበራቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቀዋል።

Photos from Eden Eden's post 25/05/2026

ጃዋር ዛሬ ያሳያቸው የምርጫ ካር ሁሉም ውሸት መሆናቸው ተጋልጧል

ሰውዬው ሁሌም ስራው እንደዚህ ህዝብን ማጭበርበር ነው። በውስጥ እንደተላከለት አድርጎ የለቀቃቸው ሁሉም ፎቶዎች የቆዩ እና ከአምስት አመት በፊት በሶሼል ሚዲያው ልክ እንደ እሱ ለፕሮፓጋንዳ ሲጠቀሙበት የነበረ ነው። ጀዋር መሃመድ በጣም የዘቀጠ እና በውሸት ላይ ብቻ ጊዜውን የሚያጠፋ ስለመሆኑ ከዚህ በላይ ማሳያ የለም።

ዛሬ እና ትላንት ስለምርጫው የሚለቃቸው ነገሮች ውሸት መሆናቸውን ያጋለጡ መረጃዎች ይሄው ሁሉም ሰው እያየው ነው። የሚገርመው ነገር ይሄ ሰው ብዙ መረጃ በውስጥ ደረሰኝ የሚለው ሁሉም ውሸት መሆናቸው ነው።

ምርጫውን ለማንቋሸሽ ይሄን ሁሉ እርምጃ ሄዷል። ህዝብ በእሱ ውሸት ምክንያት አንቅሮ እንደተፋው ግልፅ ነው። ውሸት መቼም መቼም አያሻግርምተ በጀዋር ማወቅ ይቻላል።

20/05/2026

የሰዎችን ደስታና የከተማዋን እድገት መሸከም ያቃተው አፍራሽ ኃይል ይውደም

በአንድ በኩል ለሺዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገነባ፣ ለሕፃናትና ለደካሞች የምገባ ፕሮግራም የሚዘረጋ እና ዛሬ በጥቅሉ ገብስ ተራ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ደግሞ ከ370 በላይ አባወራዎችንና እማወራዎችን የቤት ባለቤት አድርጎ የእንባ አባሽ የሆነ የከተማ አስተዳደር አለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይሄ ሁሉ መልካም ስራ ሲሰራ እንቅልፍ የሚያጣ፣ የሰዎችን ደስታና የከተማዋን እድገት መሸከም ያቃተው አፍራሽ ኃይል አለ።

ዛሬ የተረጨው የኮዬ ፈጬ እና የአራብሳ ሳይት የሱቆች የውሸት ወሬ፣ ከተማዋ እያስመዘገበችው ያለውን ተከታታይ የልማት ድሎች ለመሸፈንና የህዝብን ልብ በጥርጣሬ ለመሙላት የተወረወረ የክፋት አረር ነው። አስተዳደሩ የዜጎችን መሰረታዊ ጥያቄዎች በተግባር ሲመልስ፣ እነሱ ግን በወሬና በሃሰት ክስ ህዝብን ለማደናገር ይሮጣሉ።

ይህ የፈጠራ ዘገባ ተቃዋሚዎች ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ምንም ዓይነት አማራጭ ሃሳብ እንደሌላቸውና ስራቸው በሙሉ መልካም ስራዎችን ማጠልሸት ብቻ መሆኑን ያረጋገጠ ነው። የ370 ዜጎች የቤት ቁልፍ የመረከብ ደስታና የ20 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተስፋ በወሬ አይሸፈንም፤ የከተማው አስተዳደርም በእንደዚህ ዓይነት የፌስቡክ አሉባልታዎች ሳይገታ የጀመረውን የልማትና የፍትሃዊነት ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም የነዚህን አካላት አፍራሽ ዓላማ በመገንዘብ፣ ከወሬ ይልቅ ለመሬት ላይ እውነታዎችና ለከተማዋ ብልጽግና ትኩረት ሊሰጡ ይገባል።

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 15/05/2026
Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 03/05/2026
Want your business to be the top-listed Grocery Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis
Addis Ababa