COPHA TIMES
The source of true information Educational,Technology,the independent media for humanity.
30/07/2024
The best one of our creative logo design for
30/07/2024
Effective of our work design
02/10/2023
“ከአውሮፓ ህብረት የምንጠብቀው የለም”፡- ፕሬዝዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶሃን!!
የቱርኩ መሪ በሀገሪቱ ፓርላማ ፊት ባደረጉት ንግግር “ቱርክ ለአውሮፓ ህብረት የገባችውን ቃል ኪዳን ሁሉ ጠብቃለች፤ እነሱ ግን ቃል አባይ ሆነዋል” ብለዋል፡፡በዚህም ምክንያት አንካራ ለ60 ዓመታት ደጅ ካስጠናት የአውሮፓ ህብረት ምንም ነገር አትጠብቅም ብለዋል፡፡
ብራስልስ በቱርክ ላይ ያላትን ፍትሃዊ ያልሆነ አካሄድ በተለይም ለቱርክ ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ያለውን እንግልት ካልስተካከሉ ከእኛ የተሻለ አገልግሎት እያገኙ ሊቀጥሉ እንደማያገባ ይወቁት ሲሉም አስጠንቅቀዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ለቱርካውያን ምንም አይነት እንቅፋት የፈጠረ አሰራር አልተከተልኩም ቢልም፣ ቱርክ ከቅርብ ወራት ወዲህ ዜጎቿ የ #ሼንገን ቪዛ ጥያቄ ውድቅ እየተደረገባቸው ነው በማለት ቅሬታዋን አሰምታለች፡፡
ቱርክ አብዛኛው ግዛቷ በእስያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አባል ለመሆን በፈረንጆቹ 1987 ብታመለክትም በ1999 እጩ አባል ሆና እውቅና ከማግኘት የዘለለ ምላሽ አላገኘችም፡፡
#ቱርክ ከህብረቱ ጋር መቀላቀል እንድትችል ንግግሮች እ.አ.አ. በ 2005 ቢጀመርም፣ ንግግሩ እየተቀዛቀዘ መጥቶ እ.አ.አ. በ 2016 ቆሟል። ብራሰልስ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኤርዶጋን #ከአውሮፓ ህብረት ህጎች ጋር በሚጋጭ መንገድ ስልጣኑን ለማራዘም ሞክሯል በማለት በአንካራ ላይ የሰላ ትችት እያቀረበች ነው።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የአውሮፓ ፓርላማ ቱርክ የዜጎቿን መሰረታዊ ነፃነቶች፣ የሰብአዊ መብቶችን እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ህግ በተጻራሪ መንገድ ተጉዛለች በማለት ሀገሪቱን የሚያወግዝ ሪፖርት አጽድቋል፡፡
ኤርዶጋን ለዚህ ምላሽ በሰጡ ጊዜ ቱርክ በእንደዚህ ዓይነት አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶች ምክንያት ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት ልትገድብ ትችላለች ማለታቸውን አርቲ አስታውሷል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Rwanda Street
Addis Ababa
1000