FRESTUDIOS
This page Is a portfolio and blog site for sharing our works and filmmaking experience in Ethiopia,
18/08/2022
መልካም ቡሄ
ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡በአገራችን የክረምቱ ጨለማ ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘች።
በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ።የቡሄ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁኑ የፍልስጥኤም ሀገር ነው፡፡ የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ተብሎ ይጠራል። ብርሃነ በተገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ፡፡ ታዲያ ያንን ማስታወሻ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Yemiru Senay Building
Addis Ababa