Sport View

Sport View

Share

sport tips

07/01/2026

♦️ለግማሽ ቀን ውድድር ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሶስት ስራ አስፈፃሚ መጓዙ ተቃውሞ አስነስቷል

♦️የትኬትና የሆቴል ወጪን ሳይጨምር ለሶስቱ አመራሮች ከ4,200 የአሜሪካን ዶላር በላይ ወይም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቧል

♦️ውድድሩ ግማሽ ቀን የተያዘው አበል ለ7 ቀን መሆኑም አነጋጋሪ ሆኗል

♦️የአትሌቲክስ ቡድኑ በአውቶቡስ የ6:00 ጉዞ አድርጓል

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ትናንት ማምሻውን ውድድሩ ወደሚካሄድባት አሜሪካ ፍሎሪዳ ታላሃስ ከተማ ለመድረስ ትናንት ማምሻውን ወደ አታላንታ ያቀና ሲሆን አታላንታ ከተማ ከገባ በኃላ ወደ ውድድሩ ቦታ የሚወስድ በረራ ላይ ከአዲስ አበባ ሳይነሱ ተገቢው ግንኙነት ባለመፈጠሩና በኮኔክሽን ፍላይት ለመጠቀም ረዥም ሠዓት ኤርፖርት ውስጥ ለመቀመጥ ይገደዳሉ ከዚህ ይልቅ ወጥተን አውቶብስ ብንጠቀም ታላሃስ ፕሌኑ ከመነሳቱ በፊት ስድስት ተጉዘን ታላሃስ የውድድሩ ስፍራ እንደርሳለን የሚል አቋም በመያዛቸው የግማሾቹ የተከፈለበት የአውሮፕላን ትኬት ተሠርዞ የልዑካን ቡድኑ ከ4:30 እስከ 6:00 የሚፈጅ ጉዞ በአውቶቡስ ለማድረግ መገደዳቸውና በተለይ አትሌቶቹ ላይ ከረዥሙ የአውሮፕላን ጉዞ ወደሌላ የአውቶቡስ ጉዞ በማድረግ ለከፍተኛ ድካምና መንገላታት እንደዳረጋቸው ነው ከስፍራው እየደረሱን ያሉት ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን የሚጠቁሙት።

በቪዛ ችግር ሲታመስ የነበረው የአትሌቲክስ ቡድኑ ቀድሞ አዲስ አበባ እያሉ በኮኔክሽን ፍላይት እንዲጓዙ የሚያደርግ ዕውቀትም ልምድም ያለው የቡድን መሪን ባለማካተቱ ለአትሌቶቹ መንገላታትና በጉዞ መዳከም ትልቁን ቦታ እንደሚይዝ ነው እየተነገረ ያለው፤

አስገራሚው ነገር ግማሽ ቀን ከሚወስደው ውድድር በላይ ጉዞው ለሚበልጠው የፍሎሪዳ ታላሃስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ሶስት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መጓዛቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

በሠዎች ህገ-ወጥ ዝውውር(Human Trafficking)፣በገንዘብ ብክነትና በብልሹ አሠራር የምርመራ ዶክመንተሪ የተሠራበትና በጀግኖች ላብና ደም ተገንብቶ መመኪያ የነበረው ፌዴሬሽን ስሙ ጠልሽቶና በክፉ እየተነሳ ባለበት በዚህ ሠዓት ለግማሽ ቀን ውድድር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ፌዴሬሽኑን ለአላስፈላጊ ብክነት በሚዳርግ ሁኔታ ሁለት የቡድን መሪ(ዋናና ምክትል በማለት) በተጨማሪ ፕሬዝዳንቱ ወደ ውድድሩ ስፍራ መጓዛቸው በርካቶችን አስቆጥቷል።

ታማኝ የመረጃ ምንጮች በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል እንደጠቆሙት ከውድድሩ ይልቅ ጉዞው ለሚበልጠው ለግማሽ ቀን ውድድር ሁለት የቡድን መሪና ፕሬዝዳንቱ ሙሉ ወጪያቸውና አበል ተመድቦላቸው(ይውሠዱ አይውሠዱ መረጃው ባይኖረንም) መሄዳቸው ፌዴሬሽኑን ለከፋ የገንዘብ ብክነት አያዳርገውም ወይ?ደግሞስ ለግማሽ ቀን ውድድር አንድ ሠው አይበቃም?በማለት ከጠየቁ በኃላ ለአውሮፕላን ትኬት፣ለአበል የወጣው ገንዘብ ሲደመር ብክነቱን ያንረዋል።

በዚህም በህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውርና በገንዘብ ብክነት ስሙ የጠለሸው የኦዲተሮችና አይን ያረፈበትና ዘገናኝ የኦዲት ሪፖርት የተሠማበት ፌዴሬሽኑ ካለፈው ውድመትና ስህተቶቹ ከመማር ይልቅ ጥፋትን አሻሽሎ መቀጠልን እንደመረጠ ይጠቁማል ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል።

ለግማሽ ቀን ውድድር ሁለት የቡድን መሪና ፕሬዝዳንቱ በአጠቃላይ ሶስት ስራ አስፈፃሚ የተመደበላቸውን አበል ይውሠዱ አይውሠዱ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት ባይሳካም እንደ ታማኝ ምንጮቻችን ከሆነ በቀን 200፣በአጠቃላይ ከ4,200 የአሜሪካን ዶላር በላይ ወይም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለ7 ቀን አበል እንደተያዘላቸው መሰማቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው፤

ይሄ የገንዘብ መጠን የአውሮፕላን ትኬትንና የሆቴል ወጪን ሲጨምር ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ከፌዴሬሽኑ ካዝና እንዲወጣ ያስገድዳል በማለት በአንድ ሠው ማለቅ የሚችለውን ሶስት ስራ አስፈፃሚ በመሄዱ ድርጊቱን ከአላስፈላጊ ብክነት ጋር አያይዘው ተችተዋል።

ሁለቴ ቪዛ ለማግኘት ኤምባሲ ገብተው ወደ 60ሺ ብር ወጪ ከፌዴሬሽኑ ካዝና አስወጥተው ለኪሳራ የዳረጉትና ሁለቴ ቪዛ በተከለከሉት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) ምትክ እንደሄዱ የተነገረላቸው ፕሬዝዳንቱ ጉዞም አላማው ምንድነው?በማለትም በርካቶች ጥያቄ መዘዋል።

በክልል በሚካሄዱ ውድድሮችና በአፍሪካ ውድድሮች ብዙም ሲጓዙ የማይታዩትና ጉዞን እንደፊልም እየመረጡ ሲጓዙ የሚስተዋሉት ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ሲሆን ከፊት መገኘታቸው ጥያቄ የፈጠረባቸው ታዛቢዎች የአለም ሻምፒዮና ወይም ኦሎምፒክ ቢሆን የኮንግረስ ስብሠባ ስለሚኖር ፕሬዝዳንቱ መጓዛቸው ጥያቄ አያስነሳም፣ተገቢም ነው ካሉ በኃላ ለግማሽ ቀን ውድድር ያለበቂ ምክንያት ሶስተኛ ሠው ሆነው መሄዳቸው ግን ከብክነት ውጪ ሌላ ፋይዳ የለውም ሲሉም ተናግረዋል።

ከምንም በላይ ደግሞ በፌዴሬሽኑ ቀድሞ ባልተሠራ ደካማ ዲፕሎማስያዊ የኤምባሲ ግንኙነትና የፌዴሬሽኑ ሠዎች ባድበሠበሱት የሠዎች ህገ-ወጥ ዝውውር ኤምባሲው ጥርስ ነክሶ ቪዛ የከለከላቸው፤ ነገር ግን ሞራላቸው ሳይነካ፣እንደማይሄዱ እያወቁ ለ47 ቀናት ከተጓዦች ጋር እስከ መጨረሻው ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ አትሌቶችና አሠልጣኞች ሞራላቸው ሳይጠበቅ፣ ማበረታቻም፣ተገቢው ክብር ባልተሠጠበት ሁኔታ ሶስት ስራ አስፈፃሚዎች ቡድን መሪና ምክትል ቡድን መሪ በሚል ማዕረግ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ተንጋግተው መሄዳቸውን በርካቶች ቅሬታ እንዲያሠሙ ምክንያት ሆኗል።

በቀጣይ ጋዜጠኛ ጠል ስለሆኑትና አንዱን ልጅ ሌላኛውን የእንጀራ ልጅ በማድረግ ጋዜጠኛውን ስለሚከፋፍሉት የፌዴሬሽኑ አመራሮችና አሜሪካ ኤምባሲ ሁለቴ የቪዛ ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገባቸው የፅ/ቤት ኃላፊ ወንበራቸው ላይ ሁለት ወር እንኳን በቅጡ ሳይደፍኑ በአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ለማመልከት የሚረዳውን፣የጋዜጠኛው መብት የሆነውን አክሠስ ኮድ በመቆጣጠራቸው ዙሪያ የምመለስበት ይሆናል።

መልካም ዕድል ለጀግኖች አትሌቶቻችን💪💪

Ethiopian Athletics Federation’s new rules upset coaches 15/04/2025

Ethiopian Athletics Federation’s new rules upset coaches The requirement for a master's degree in sports for the position of the head coach of the Ethiopian national team sparks discontent among current coaches

አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ኦሎምፒክና የአለም ዋንጫን ታዘጋጃለች/ What is Trump's stance on sports? 09/11/2024

ትራምፕ እና ስፖርት በቀጣዮቹ 4 አመታት ምን አይነት ግንኙነት ይኖራቸው ይሆን?
አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ኦሎምፒክና የአለም ዋንጫን ታዘጋጃለች፡፡ ትራምፕ ስለ ስፖርት ያላቸው አቋም ምን ይመስላል? USA will host the Olympics and World Cup in the Trump era. What is Trump's stance on sports?

ይህንን አስገራሚ ዝግጅት እንድትከታተሉ ጋበዝናችሁ!

👇👇👇👇👇

አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ኦሎምፒክና የአለም ዋንጫን ታዘጋጃለች/ What is Trump's stance on sports? ትራምፕ እና ስፖርት በቀጣዮቹ 4 አመታት ምን አይነት ግንኙነት ይኖራቸው ይሆን?አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ኦሎምፒክና የአለም ዋንጫን ታዘጋጃለች፡፡ ትራምፕ ስለ ስፖርት ያላቸው አቋም ምን .....

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa
1000