Ethio-Cinema

Ethio-Cinema

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio-Cinema, Film/Television studio, Mexico, Addis Ababa.

18/11/2022

#ስለ sur-realism ከፊልም ጋር ስላለው ቁርኝት ትንሽ እንበላችሁ
# ዲበ_እውነታዊነት

========©=========
ዲበ-እውነታዊነት # Sur_realism የሚለው ቃል ከፈረንሳይ ቃል የመጣ ሲሆን Sur ማለት በእንግሊዘኛው Beyond ባሻገር ፣ ዲበ ማለት ሲሆን Realism ደግሞ እውነታዊነት ተብሎ ይተረጐማል፡፡ ዲበ እውነታዊነት በፊልም ሆነ በስነ-ስዕል አስተምሮት ለማግኘት ሆነ ጥናት በማድረግ ከተለመደው የተፈጥሮ ህግ ውጪ በሆነ ልማደ ህይወት የሚገለጹ ነገሮችን ከ “Psychoanalytical” በህይወት የሚደረግ ጥናታዊ ስራን መሠረት በሚያደረግ መልኩ የሚቀርብበት
ነው፡፡ ዲበ-እውነታዊነት Sur-Realism የመጣው ከትርጉም የለሻዊነት Dadaism ሲሆን ከዚያም የራሱን የሆነ ፍልስፍና፣ ዘይቤ ለመከተል የቻለ ነው፡፡

በስነ ውበት ዙሪያ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ በስነ-ጽሁፍ፣ ስነ-ስዕል ለፊልም በቅድሚያ የሚታወቁ አስተሳሰቦችን እንደ ትርጉም የለሻዊነት ዘይቤ የማይቀበል ከእውነታ ፍልስፍና ዘይቤ ያፈነገጠ ነጻ የሆነ ዘመናዊ አስተሳሰብን የሚከተል ነው፡፡

በዚህ የፍልስፍና ዘይቤ ከፊልም ጽሁፍ አጻጻፍ shooting Script በፊልም
ዝግጅት ለማሳየት የሚሞክረው ውስጣዊ ህሊና Sub-Conscious ነጸብራቅ የሆነው ስነ - ጥበብን ነው፡፡
ዲበ-እውነታዊነት ንቃተ ህሊና Consciousness ትኩረት የሚያደርግ ሓልዮት ያሉበት የገጸ-ባህሪያት characte r አሳሳል የቃለ ፊልም አቀራረብ፣ የዋና ገጸ-ባህሪ Main Character ልዕለ አእምሮ super mental ወይም የመንፈስ ዝለት ያለበት የህሊናን ጥያቄ መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በዚህ የፊልም ዘይቤ ውስጥ ከተለመደው ወይም ግራ የሚያጋባ ሰዎች ከተስማሙበት እውነታ ያፈነገጠ የአጻጻፈ “የዝግጅት”ሓልዮትን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

የዲበ-እወነታዊነት መሥራች የሚባለው በ1924 Andre Breton ሲሆን ለዚህ
ዘይቤ መነሻ የሆነው ትርጉም የሌሻዊነት ብለን የጠቀስነው ዘይቤ ነው፡፡
የዚህ ዘይቤ ዋናው መነሻ ጭብጥ አዳሪያን Bourgeois Society ለመቃወም ነው፡፡ ቀድሞ ከተቀመጠው በፊልም ህግ ውጭ በሆነ ሁኔታ አዲስ ልዩ ህግን በመፍጠር “Pure Psychic Automatism” የምንለው በፊልም ውስጥ ያሉ ገጸ-ባህሪያት ገደብ በሌለው በሁሉ ቦታ መገኛ ፣ በሁሉ ቻይነት Omnipotence and Omnipresent አድርጐ የመቅረጽ ዘይቤን የተከተለ ነው፡፡ ዘይቤው በአስተምሮቱ ከማህበረሰቡ የወጣ “እብደት” የምንለው ከተለመደው
የማስተማር ሒደት የተለየ መንገድን የሚከተል ነው፡፡ ዲበ-እውነታዊነት
መፍጠር የሚፈልገው በራሱ እውነት ብለን ከተቀበልነው ከአመንበት በላይ ያለ
እውነትን ነው፡፡

በተለይ በሚያስደንቅ ሁኔታ ዘይቤውን የሚገልጹ ፊልሞ King Kong, the
illusionist የመሳሰሉት ፊልሞች ናቸው በተለይ በ1928 የተሰራው unchien
Andalou (An Andalusia Dog) እና L’Age D’ The Age of Gold
193ዐ ዘይቤውን በመከተል ተጠቃሽ ፊልሞች ናቸው፡፡

Critics - Ethiopia

Film Critics - Ethiopia🇪🇹 (Online Cinema School)📽 16/11/2022

Summary!

ስለ Screenplay ቀለል ባለ መንገድ ሙሉ ሃሳቡን እንደሚከተለው ይረዱት!

ስክሪን ፕሌይ ምንደን ነው?አፃፃፉስ እንዴት ነው?

ስክሪን ፕሌይ ማለት የ ፊልሙ ፅሁፍ ወይም ስክሪፕት ሲሆን ፊልሙን ለሚሰሩት ሰዎች እንደ መመሪያ ሆኖ ያገለግላል። ስክሪን ፕላይ ሲፃፍ ሶስት ዋና ነገሮች አሉት

1 በ SlugLine ይጀምራል ስለግላይን ማለት አንድ ሲን(Scene) የት እና መቼ እየተከሰተ እንደሆነ የሚገልፅ ነው። ለምሳሌ “ውስጥ - ቢሮ-ምሽት” (“INT-OFFICE-NIGHT”) ይሄ በየ ሲን መጀመሪያ ላይ መፃፍ ያለበት ሲሆን ቦታ ለሚፈልጉት (Location Scout) የታሰበውን ቦታ እንዲያገኙ፣ ፕሮዳክሽን ዲዛይነሩ የተገኘውን ቦታ ቢሮ አስመስሎ እንዲሰራው፣ ሲኒማቶግራፈሩ ምን አይነት ላይቲንግ እንደሚጠቀም እንዲሁም ላይን ፕሮዲውሰሩ(Line Producer) ደግሞ ፊልሙ የሚፈጀውን ወጪ ለመስራት ያገለግላል ። ብዙ ጊዜ በምሽት የሚቀረፁ ቀረፃዎች ውድ ዋጋ ያስወጣሉ፣
2 Action Line አክሽን ላይን ታሪኩ ላይ የሚከሰተውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እና ተግባር ይገልፃል። ለምሳሌ ድርሰት ላይ በባሏ መሞት ጥልቅ ሃዘን ላይ ናት ብቻ ብለን መግለፅ የሚቻለውን ስክሪን ፕሌይ ላይ ግን ያቺ ሴት ስታለቅስ፣ ፀጉሯን ስትነጭ፣ ስትጮህ፣ ወዘተ በግልፅ ምን እንዳደረገች መፃፍ አለበት። አሳይ እንጂ አትንገር (SHOW DON’T TELL) ማለት ይህ ነው።

3 ቃለምልልስ

ፊቸር ፊልሞች ከ 90 እስከ 120 ገፆች ብቻ ሲሆኑ 1 ገፅ 1 ደቂቃ ተደርጎ ይቀረፃል ። ፊልሞች በዋናነት በ 3 ነግሮች ላይ ያተኩራሉ። 1 - መሪ ገፀባህሪ ዋናው የታሪኩ ካራክተር ነው። 2- አላማ - መሪው ገፀ ባህሪ የሚፈልገው ወይም የሚኖርለት አላማ ሲሆን 3ኛው ደግሞ እንቅፋቶች ናቸው፣ ስለዚህ ፊልሙ አንድ ገፀባህሪ የሚፈልገውን አላማ ለማሳካት የሚያልፍበትን ጉዞ እና የሚያጋጥሙትን ችግሮች እንዴት እንደሚያልፍ የሚያሳይ ነው ማለት ነው። ለምሳሌ ፊልሙ ጋ ገፀባህሪው ከ እስር ለማምለጥ የሚሞክር ቢሆን አላማው ማምለጥ እንቅፋቱ ደግሞ ጥበቃዎች ሲሆኑ ፊልሙ የሚያጠነጥነው እንዴት እንዳመለጠ ወይም ሞክሮ እንዳልተሳካለት ላይ ይሆናል።

ስክሪን ፕሌይ ብዙ ጊዜ 3 አክት ክፍሎች ያሉት ተደርጎ ይፃፋል። ይህ የመጣው ታካቁ ፈላስፋ አርስቶትል ባስቀመጠው መሰረት ነው።ሲድ ፊልድ በ መፅሃፉ እንደሚያስከምጠው Act 1 -> 20-30 ገፆች Act-2 -> 35-70 ገፆች Act-3 -> 75-90 ገፆች ይህም መጀመሪያ ፣ መሃል እና መጨረሻው ነው። እያንዳንዱ ምዕራፍ ላይ የሚከሰቱት ነገሮች ጠቅለል ባለ መልኩ የሚከተለውን ይመስላሉ : ለመርዳት እንዲያግዝ ወደፊት የሚለውን የወንድም አገኝ ለማ ን ፊልም እንደምሳሌ እንጠቀማለን

ACT-1 - መጀመሪያ

-ፊልሙ ላይ ያሉት ገፀባህርያትን ያስተዋቀናል
-ገፀባህሪው ያለበትን አለም ይገልፃል
-መሪው ገፀባህሪ (Hero)ን ያስተዋውቃል

-እንዱሁም ገፀባህሪው የሚኖርለትን አላማ ይገልፃል።

“ህይወትን አባቷ ሙላት ለሚባል ባለሃብት ሊድራት ነው።

የምታፈፍቅረው ፍፁም ደግሞ ድህነቱን አሸንፎ ከህይወት ጋር የተድላ ኑሮ ለመኖር የሚለፋ ሾፌር መሆኑን ተቀጥሮ የሚሰርበት ድርጅት ባለቤት መዓዛ ደግሞ በድብቅ እንደምታፈቅረው እንዲሁም ኪስ አውልቅ የሆኑትን የ ህይወትን ጓደኞች ያስተዋውቀናል ::”

ACT-2- መሃል

-ከፍተኛ ግጭት ፣ ችግር ያጋጥመዋል
-ወዳጅም ጠላትም ይሸምታሉ
-ጥሩም መጥፎም ያጋጥማቸውል
-በመጨረሻም ተስፋ የሚቆርጥበት ደረጃ ላይ ይደርሳል

“ህይወት እና ፍፁም ለሚያሰሩት የሪልስቴት ቤት ከ አቅማቸው በላይ ገንዘብ የጠየቃሉ። ጓደኛዋ ደግሞ ልታገባ መሆኑ ውጧን በጣም ረብሾታል ። ከነሱ አንሳ ላለመታየት የባጡን የቆጡን ትቧጥጣለች። ከዚ ጭንቀት ለመውጣት ፍፅም የሚሾፍርላትን የድርጅቱን ባለቤት ለገንዘብ ብሎ በፍቅር እንዲያጠምዳት ህይወት ታስገድ ደዋለች። ህይወትን በጣም ስለሚወዳት እና ለረጅም ጊዜ ቃል የሚገባላትን ህይወት ሊያኖራት ስላልቻለ ይሄን በማድረግ ኑሮን እንደሚያሸንፉ አምኖበት ይስማማል ። መዓዛ ደግሞ ተናግሮ የማሳመን አቅሙ የስራ እንደሚያግዛት ስላመነች ፍፁም ሾፌርነቱን ትቶ በድርጅቱ ውስጥ እንዲሰራ በጠየቀችው መሰረት ስራውን ይቀበላል እንደሚያፈቅራትም ነግሯት የፍቅር ኑሮ ይጀምራሉ ።”

ACT-3 መጨረሻው

-ግጭቱ ወይም ችግሩ ጣራ ይነካል ከችግሩ ጋር ፊትለፊት ይጋጫሉ።
-አላማቸውን ያሳካሉ ወይስ አያሳኩም የሚለውን ነገር የሚወስነው ክፍል ነው
-አብዛኛው ፊልሞች ላይ አላማቸውን ያሳካሉ።

መዓዛ ከፍፁም ጋር የሚኖሩበትን አዲስ ቤት ገዝታ ቁልፉን ት ሰጠዋለች ። ፍፁምም ቢሆን መዓዛን ቀርቦ ሲመለከታት የምሩን ወደዳት። ድርጅቱም ጥሩ ስኬት ማግኘቱን ተከትሎ ከመዓዛ ጋር ለመዝናናት በወጡበት ሰክረው አብረው ያድራሉ። መዓዛም ታረግዛለች።ህይወትም ብት ሆን ገንዘብ ከሚያሳድ ዱ ጓደኞቿ ጋ መዋል ከጀመረች በኃላ እየተቀየረች ፍፁም የሚወደው ማንነቷ እየመነመነ መጥቷል :: ፍፁም ብቸኛ ሆኖ በማደጉ ገንዘብ ባይኖረውም ልጅ መውለድ የምን ጊዜም ምኞቱ ስለነበር መዓዛን አግብቶ ህይወትም ገንዘን ስታሳድ ድ ብዙ መስዋት የከፈለችለትን ፍቅሯን አጥታ መዓዛም ለረጅም ጊዜ ስታፈቅረው ለኖረችው ሰው የልጁ እናት ይሆናለች

3- ACT አፃፃፍን አብዛኛው የ አለማችን ክፍል ይጠቀመዋል። ቀጥተኛ ያልሆነ (non-Linear) አፃፃፍን መከተል ይቻላል ነገር ግን አይመከርም ። ማንኛውንም አይነት አፃፃፍ ብንከተል ግን ግልፅ የሆነ ስክሪን ፕሌይ ፊልሙ የሚሰራበትን መሰረት ይጥላል::

ቴሌግራም፦ https://t.me/filmcriticss ይቀላቀሉን!

Critics - Ethiopia

Film Critics - Ethiopia🇪🇹 (Online Cinema School)📽 የፊልም እና የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ትምህርቶች እዚህ ያገኛሉ!

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Mexico
Addis Ababa