EVEN Pharmacy

EVEN Pharmacy

Share

You may expect the best Pharmacy service .

26/11/2022

የየቀኑን መድኃኒትዎን ማስቀመጫ።
Daily Pill Organizer, 7Compartments Portable Pill Case, Weekly Pill Organizer.

Photos from EVEN Pharmacy's post 12/09/2022

ብጉር | Acne vulgaris

◈ ብጉር በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቅ፤ ወዝ አመንጪ እጢዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው የአካል ክፍሎች ላይ (ፊት ፣ ደረት ፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል) የሚወጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው።

◈ ብጉር ከጨቅላ ህጻናት ጀምሮ የሚከሰት ቢሆንም በአብዛኛው ከ12-25 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ይታያል።

◈ ብጉር አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከወጣትነት የእድሜ ክልል በኋላ (30 እና 40ዎቹ) የሚከሰተው የብጉር አይነት ግን በብዛት ሴቶች ላይ ይታያል።

➡ ለብጉር መከሰት አራት መሰረታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ናቸው

1- Follicular hyperkeratinization; ይህም የሞቱ ህዋሳት ተጠራቅመው የወዝ መተላለፊያ ቱቦ እንዲዘጋ ያደርጋል

2-የወዝ በብዛት መመረት (increased sebum production)

3-Propionibacterium acne የሚባለው የባክቴሪያ አይነት

4-ብግነት (Inflammation)

➡ ብጉርን እና ብጉር መሰል ሽፍታዎችን (Acneiform eruption) የሚያባብሱ ነገሮች

👉ጭንቀት (stress)
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት
👉በወር አበባ አካባቢ
👉የሚዋጡም ሆነ የሚቀቡ መድሀኒቶች (steroids, phenytoin...)
👉በስራ ሁኔታ የሚያጋጥሙ ኬሚካሎች

👉በቆዳችን ላይ በሚከሰተ መፈጋፈግ (friction) ወይም ጫና (pressure) ፤ ለምሳሌ በህመም ሆነ በሌላ ምክንያት ለረጅም ግዜ በጀርባው የሚተኛ ሰው ጀርባው ላይ ብጉር ሊወጣ ይችላል ወይም የጡት ማስያዣ ገመድ የሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ ሊወጣ ይችላል
👉 ለረዥም ሰአት የፊት ማስክ ማድረግ
👉በውስጣቸው comedogenic ingredients የያዙ የፊትና የጸጉር ቅባቶች

➡ ብጉር እንዴት ይታከማል?

✔️ ብጉር በአብዛኛው ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የቆዳ ህመም በመሆኑ በራሱ የሚጠፋውም ከእድሜ ጋር ተያይዞ ነው ፤ ስለዚህም ምልክቶቹን መቆጣጠር እንጅ በህክምና ማዳን (በአንድ ህክምና እስከ መጨረሻው እንዳይመጣ ማድረግ) አይቻልም።

በዚህም ምክንያት የብጉር ህክምና ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ታካሚዎች ከቆዳ ሐኪማቸው ጋር እየተመካከሩ ህክምናውን መከታተል ይኖርባቸዋል።

✔️ እዚህ ጋር ብጉር በራሱ ጊዜውን ጠብቆ የሚጠፋ ከሆን መታከም ለምን ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ፤ብጉር ከሚያሳድረው የስነ-ልቦና ጫና በተጨማሪ ሳይታከም በቆየ ቁጥር ፊታችን ላይ ጠባሳ የመፍጠር እድሉ የሰፋ ስለሆነ በጊዜ መታከሙ ይመከራል።

✔️ የብጉር ህክምና እንደ ጥንካሬው መጠን በሚቀባ ፣ በሚቀባና በሚዋጥ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ሊታከም ይችላል

✔️ ከዋናው ህክምና በተጨማሪ በውስጣቸው Salicylic acid, Benzyle peroxide የያዙ መታጠቢያ ሳሙናዎች መጠቀም ያስፈልጋል

➡ ከህክምናው በተጨማሪ ማድረግ የሚጠበቅብን

👉እንቅስቃሴ ማድረግ (ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳል)
👉ብጉሮቹን ለማፍረጥ አለመሞከር (ጠባሳ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ)
👉ለቆዳ ጤና መጠበቂያም ሆነ ለውበት የምንጠቀማቸው ምርቶች Oil-free & non-comedogenic መሆናቸውን ማረጋገጥ
👉ፀሐይ መከላከያ (sun-screen) መጠቀም (መጠቀም ያለብን የፀሐይ መከላከያ እንደ ቆዳችን አይነት ስለሚለያይ የቆዳ ሐኪም ያማክሩ)
👉ቆዳችን ላይ ጫና (pressure) የሚፈጥሩ ነገሮችን (helmets, ስልክ, የቦርሳ/የጡት ማስያዣ ገመድ, የፊት ማስክ) መቀነስ
👉ሰውነታችንን ካላበን መታጠብ

✔️ በመጨረሻም ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል‼️

ምንጭ:-ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

Want your business to be the top-listed Health & Beauty Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Yerer-Goro
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 22:00
Tuesday 09:00 - 22:00
Wednesday 09:00 - 22:00
Thursday 09:00 - 22:00
Friday 09:00 - 22:00
Saturday 09:00 - 22:00
Sunday 10:00 - 22:00