EyohaMedia

EyohaMedia

Share

Official Page of EyohaMedia, The premier destination to watch and share original videos related to Ethiopia.

07/03/2026

የአርቲስት ታደለ ሮባ እናት ወይዘሮ ብርቱካን ብሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የታዋቂው ድምፃዊ ታደለ ሮባ እናት ወይዘሮ ብርቱካን ብሩ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል። የእናታችን የወይዘሮ ብርቱካን ብሩ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ እሁድ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን የሚፈጸም ይሆናል።

የአርቲስቱ አድናቂዎች፣ የሙያ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በነገው ዕለት በቦታው በመገኘት ለእናታችን የመጨረሻ ሽኝት በማድረግ በሐዘኑ እንድትካፈሉ ጥሪ ቀርቧል። ለወንድማችን አርቲስት ታደለ ሮባ እና ለመላው ቤተሰቡ መጽናናትን እየተመኘን፣ ለእናታችን ነፍስ በአፀደ ገነት ያኑርልን እያልን ጥልቅ ሐዘናችንን እንገልጻለን።
ምንጭ: ጉርሻ page

06/03/2026

በሳምንት እስከ 137 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ እያጣ ያ'ለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት በሳምንት 160 በረራዎችን ለመሰረዝ እየተገደደ መሆኑን ገለጸ። በዚህም አየር መንገዱ በሳምንት እስከ 137 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ እንደሚያጣ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት መንገደኞችን እንዲሁም ጭነቶችን ያመላልሳልስ የነበረ ሲሆን በተለይ ደግሞ ወደ ዱባይ በቀን ሦስቴ ወደ ሻርጃ ደግሞ አንዴ ይበር ነበር።

በወጪም ደረጃ የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ከፍተኛ የነዳጅ አምራች በመሆናቸው እና ቀጠናው ሰላም አለመሆኑ በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ ተገልጿል። አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን የአየር ጉዞ አስተጓጉሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዳይንቀሳቀሱ አድርጓል። የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የአየር ክልላቸውን ዘግተው የሚቆዩ ከሆነ እና ጦርነቱ ካልቆመ ከባህረ ሰላጤው አገራት ወደ አውሮፓ፣ አፍሪካ እና እስያ የሚሄዱ ተጓዦች ተጨማሪ ተግዳሮቶች ይገጥማቸዋል ተብሎ ይታመናል።

Photos from EyohaMedia's post 01/03/2026

ታዋቂው ጋዜጠኛና የጥበብ ሰው ተመስገን ባዲሶ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ

​ | በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነትና የሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ ጉልህ አሻራ ያሳረፈውና በብዙኃኑ ዘንድ "የማይረሳውና ጨዋታ አዋቂው" እየተባለ የሚጠራው ተመስገን ባዲሶ፣ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በ51 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

​የጋዜጠኛው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን፣ ወዳጅ ዘመዶቹና የሙያ ባልደረቦቹ በተገኙበት በክብር ተፈጽሟል።

​የሕይወት ታሪክና የሥራ ዘመኑ
​ተመስገን ባዲሶ ታህሳስ 16 ቀን 1967 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ "አውቶቢስ ተራ ደጃዝማች ገነሜ ትምህርት ቤት" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአባቱ ከአቶ ባዲሶ ባደታና ከእናቱ ከወይዘሮ ባዬሽ ዳዊት ተወለደ።

ትምህርቱን በደጃዝማች ገነሜ ትምህርት ቤት የጀመረው ተመስገን፣ ገና በወጣትነቱ ለጥበብና ለንባብ የነበረው ፍቅር ለየት ያለ እንደነበር ይነገርለታል።

​በ1985 ዓ.ም "የፍቅር ማህደር" በተሰኘ ጋዜጣ ላይ ታሪኮችን በመጻፍ የጀመረ ሲሆን፣ ከዚያም ባለፉት ዓመታት በበርካታ ታዋቂ ህትመቶች ላይ በመሳተፍ ለአንባቢዎች ምክርና እውቀትን ሲያጋራ ቆይቷል። ከእነዚህም መካከል ቃልኪዳን፣ ጽጌረዳ፣ ማክዳ፣ እንኮይ እና ሮዝ መጽሔቶች እና ሊቢሮ፣ ኔሽን እና ሆሊዴይ በተሰኙ ጋዜጣዎች ላይ ተሳትፏል።

​ተመስገን ባዲሶ በህትመት ውጤቶች ብቻ ሳይወሰን በቴሌቪዥን መስኮትም ተወዳጅነትን አትርፏል።
​ከ1999 - 2002 ዓ.ም፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) "ጉራማይሌ" ፕሮግራም ላይ በጋዜጠኝነት ሰርቷል።
​ከ2005 - 2007 ዓ.ም "ጉራማይሌ ቶክ ሾው" በዩቲዩብ ላይ አስተማሪና አዝናኝ ፕሮግራሞችን በማቅረብ የሚዲያ ዘርፉን አገልግሏል።

​በማህበራዊ ሚዲያ በነበረው ንቁ ተሳትፎና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በስነጽሁፍ ዘርፍ በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው ሶስተኛው የ"ጣና አዋርድ" ሽልማት አሸናፊ መሆን መቻሉም የሚታወስ ነው።

​ተመስገን ከሙያው ባለፈ በደግነቱና ለሰዎች በነበረው አሳቢነት ይታወቃል። ጓደኞቹን በማስተባበር የተቸገሩ ወገኖችን እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ሲረዳ የቆየ ሲሆን፣ በተለይም ​ከከተማ ርቀው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይዘጉና አገልግሎታቸው እንዳይቋረጥ በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።

​ተመስገን ባዲሶ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Africa Avenue/Bole Road
Addis Ababa