Maysh Media.Com

Maysh Media.Com

Share

የአራት ማዕዘናት የመረጃ ማዕከል

08/06/2026

4 ሎሚ ገበያ ይዘው የወጡት እናት ( እመትገሎ ኮበሺህ)!

"በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አራት ፍሬ ሎሚ ይዘው ለመሸጥ ገበያ ወጥተው በነበሩበት ምስላቸው የብዙዎችን ልብ የሰበሩትና ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆኑት እናት እመት ገሎ ኮበሺህ፣ ሰይፉ ፋንታሁን አጊንቷቸዋል።

እመት ገሎ (Gelo Kebeshi) ይባላሉ። በአዲስ አበባ ከተማ ከ20 ዓመታት በላይ ኖረዋል። አማርኛ ቋንቋ ብዙም ስለማይችሉ የሚግባቡት በጉራጊኛ ነው።

ህይወታቸውን በጉሊት ንግድ እየደገፉ፣ በዚህ እድሜአቸው ዛሬም ድረስ በላስቲክ በተሰራ ጎጆ (መጠለያ) ውስጥ ነው የሚኖሩት።

እማማ ወደ ገበያ የወጡት 4 ፍሬ ሎሚ ብቻ ይዘው ነበር። የያዟት 4 ሎሚ ተሸጣላቸው፣ ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው የሚሆን አንድ እንጀራ ገዝተው ለመግባት... የቤት ነገር ቢያስጨንቃቸው እንጂ በዚህ በደከመ እድሜአቸው ድጋፍ እንጂ ድካም አይገባቸውም ነበር።

እማማ ሰው እጅ ከመጠባበቅና ከመለመን ይልቅ፣ በወዛቸው ሰርተው ለመኖር የሚያሳዩት ተጋድሎ ለእኛ ለወጣቶቹ ትልቅ የሥራ ፍቅርና የጽናት ትምህርት ነው። ነገር ግን አቅማቸው የደከመ አረጋዊ እናት በመሆናቸው የሁላችንም ሰብአዊ ድጋፍ አሁን ያስፈልጋቸዋል።

የእማማን እንባ ማበስ የሁላችንም ድርሻ ነው።የባንክ አካውንት፦1000769117125 Gelo Kebeshi (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)"

Photos from Maysh Media.Com's post 24/05/2026

22 ዓመት ዛሬ ተሸነፈ
የፅናት ጉዞ በክብር ተሞሸረ

05/05/2026

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

​በትግራይ ክልል ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የክልሉ ምክር ቤት በድጋሜ በመሰባሰብ ባካሄደው ጉባኤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ። ምክር ቤቱ ወ/ሮ ኪሮስ ሓጎስን አፈ ጉባኤ፣ ወ/ሮ ምህረት በርሄን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ በመሾም ጉባኤውን አጠናቋል።

የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እና የፌዴራል መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።(ማህበራዊ ድህረገጽ )

02/02/2026

" "!

የሰሞኑ አነጋጋሪ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ የሚገርም ትወና ፣የሚገርም መልዕክት ።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Bole Road/Africa Avenue
Addis Ababa