Anbesa Bank
LET'S GO FOR IT! Lion International Bank is dedicated to ensuring the satisfaction of its customers, both in their personal lives and business endeavors.
30/05/2026
Vacancy Announcements
=======================
Anbesa Bank Invites competent and qualified candidates for the following positions.
1. Branch Manager I
2. Sub Branch Manger
3. Resident Auditor
4. Senior Customer Service Officer I
5. Trainee Bank
Please visit the below link to our Websites for the details:
https://anbesabank.com/careers/
Deadline: June 03, 2026
#እንጀምረው
27/05/2026
ውድ ደንበኞቻችን
====================
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ዒድ ሙባረክ!
አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!
#እንጀምረው
ጋንዲ እና አንፎ ቅርንጫፎቻችን አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
===========================
ባንካችን ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በአዲስ አበባ ከተማ ጋንዲ 392ኛ፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር አንፎ 393ኛ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስንገልጽ በደስታ ነው።
አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!
#እንጀምረው
08/05/2026
አንበሳ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሼሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላቱን አስተዋወቀ
===============================
አንበሳ ባንክ በሼሪዓ መርሆች ላይ ተመስርቶ የሚሰጠውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የአስተዳደር ስርዓት የተደራጀ እንዲሆን እና አገልግሎቶቹ መሰረታዊ የሸሪዓ መርሆችን ያከበሩ እንዲሆኑ ለማስቻል የሼሪዓ አማካሪ ቦርድ ያቋቋመ ሲሆን የአማካሪ ቦርድ አባላቱን ከባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ጋር የማስተዋወቅ መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡
የሼሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላቱ ሸይኽ አደም አብዱልቃድር - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ ሸይኽ ሙባረክ መሐመድ አወል - የፌዴራል ሸሪዓ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና አቶ ኢብራሂም ዳውድ ሙዜይን - የፓን አፍሪካ የሸሪዓ አማካሪ ማህበር የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ሲሆኑ አባላቱ በእስልምና እምነት እና በሼሪዓ መርሆች ከፍተኛ ስፍራ ያለቸው፣ ከበሬታን እና አንቱታን ያተረፉ የኃይማኖች አባቶች ናቸው፡፡
የቦርድ አባላቱ የተመረጡት በእስልምና፣ በሸሪዓ ህግ፣ በሕግ ዳኝነት እንዲሁም ከወለድ ነፃ የባንክ አሰራር ዙሪያ ባላቸው ሰፊ ልምድ እና እውቀት መሰረት እንዲሁም በእስልምና ኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ባላቸው ጠንካራ የአመራር ብቃት እና በማህበረሰቡ ዘንድ ባላቸው ከፍተኛ ተቀባይነት መሰረት መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
አማካሪዎቹ የአንበሳ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር የተጣጣሙ፣ ግልፅ እና ታማኝ መሆናቸውን በመገምገም የተሻለ ሃሳብ የሚሰጡ ሲሆን ባንኩም ተወዳዳሪ እና ተገልጋዩን ህብረተሰብ የሚጠቅሙ አገልግሎቶችን ማቅረብ እንዲችል በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖራቸዋል፡፡
አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!
#እንጀምረው
ወረታ፣ ለገጣፎ እና መቱ ቅርንጫፎቻችን አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
===========================
ባንካችን ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በአማራ ክልል ወረታ ከተማ 389ኛ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር 390ኛ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል መቱ ከተማ 391ኛ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስንገልጽ በደስታ ነው።
አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!
#እንጀምረው
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Athlete Haile G/Selassie Avenue, Lex Plaza Bldg. Addis Ababa
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 19:00 |
| Tuesday | 08:00 - 19:00 |
| Wednesday | 08:00 - 19:00 |
| Thursday | 08:00 - 19:00 |
| Friday | 08:00 - 19:00 |
| Saturday | 08:00 - 19:00 |