Buzuayehu Tadele Family Foundation
Buzuayehu Tadele Family Foundation is a non-governmental organization (NGO) Buzuayehu Tadele and His Family Foundation (BTFF).
06/01/2026
መልካም ገና !
ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን በዓሉ የደስታና የፍሰሃ እንዲሆንላችሁ ይመኛል!!
05/01/2026
የጌታችን የመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ገናን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ማዕድ አጋርተናል።
በተጨማሪም በቪላ አፍሪካ የምገባ መርሃ ግብራችን የዕለት ጉርስ ለምናቀብላቸው ወገኖችም እንደዚሁ ማዕድ አጋርተናል።
ፋውንዴሽናችን በዘድሮው የገና በአል በድምሩ ለ1200 ዜጎች ማዕድ አጋርቷል።
ባለፉት ተከታታይ 4 አመታት በበአላት ወቅት ለወገኖቻችን ማዕድ በማጋራት እና ሌሎች ማህበራዊ ድጋፎች በማድረግ ፋውንዴሽናችን አጋርነቱን ሲያሳይ ቆይቷል ።
ኢኮኖማያዊ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወኖች ድጋፍ ማድረጋችንን በማጠናከር ማህበራዊ ሃላፊነታንን እንወጣለን።
12/12/2025
05/12/2025
ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን በልደታ ክፍለ ከተማ ላበረከታቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እውቅና ተሰጠው ።
ክ/ከተማው ለፋውንዴሽናችን እውቅና የሰጠው የ2017 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለመዝጋትና የ2018 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማስጀመር ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ነው ።
ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን በክፍለ ከተማው በአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እና የንግድ ሱቆች ገንብቶ ማስረከብ፤ በቪላ አፍሪካ ምገባ ፕሮግራም ላለፉት 2 አመታት የእለት ጉርስ የሌላቸውን አረጋውያን መመገብ፤ በአከባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት፤ የህፃናት ማቆያ ቁሳቁስ በማሟላቱ ፤ የበአላት ወቅት ማዕድ ማጋራት እና ሌሎች የአቅም ግንባታ ድጋፎችን ማድረጉ በክፍለ ከተማው እውቅናውን አሰጥቶታል።
12/11/2025
ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን እና ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከእንሳሮ ወረዳ አስተዳደር እውቅና ተሰጣቸው፡፡
ሁለቱም ተቋማት የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ እህት ድርጅቶች ሲሆኑ ፤ ፋውንዴሽኑ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት በመጠገን፤ በሺዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረቡ እንደዚሁም በወረዳው ለሚሰራው የአቅም ግንባታ ስራዎች ነው እውቅናው የተሰጠው፡፡
ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ደግሞ በሃገር አቀፍ ደረጃ የነበረውን የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ ንረት በማረጋጋቱ እንደዚሁም በወረዳው ላመጣው ኢኮኖሚያዊ መነቃቃና ለውጥ፤ በተጨማሪም ለአከባቢው ወጣቶች ለፈጣራቸው የስራ እድሎች ነው፡፡
04/11/2025
ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን (ማኅበራዊ አገልግሎታችንን የሚፈጽመው ምግባረ ሰናይ ተቋማችን) በተሰማራባቸው አካባቢዎች ሁሉ ማኅበራዊ ለውጥና እድገትን ለማምጣት በቁርጠኝነት ይሠራል። #ትብብር፣ እና ሰንቀን፣ ብሩኅ መጪ ጊዜን ለመገንባት እንተጋለን!
በበጎ ፈቃደኝነት አብራችሁን ለመሥራት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡ buzuayehufoundation.org/index.php/volunteer
_
At Buzuayehu Tadele Family Foundation (our wing), we are dedicated to creating lasting impact in everycommunity we serve. Through , and , we work to uplift lives and build a brighter future!
Join our efforts and be part of this meaningful journey by volunteering today: buzuayehufoundation.org/index.php/volunteer
_
23/10/2025
ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን እና ኢስት አፍሪካ ሪልእስቴት ሃላፊነነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የብርና የወርቅ ደረጃ እውቅና ተሰጣቸው።
ኢስት አፍሪካ ሪልእስቴት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ባለ 4 ወለል ህንጻ ለአቅመ ደካሞች ገንብቶ በማስረከቡ ፤ፋውንዴሽኑ ደግሞ ፤ "ለነገዋ "የሴቶች ታሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀግያ ማዕከል ድጋፍ በማድረጉ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለህጻናት ማቆያ ማዕከል ቁሳቁስ በማሟላቱ ፣ በ20ኛው ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ለ500 አረጋውያን በየእለቱ በመመገብ እንደዚሁም በቪላ አፍሪካ ከ50 በላይ ለሆኑ አረጋውያን ለሚያደርገው ምገባ ነው እውቅና የተሰጠው።
ሁለቱም ተቋማት በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ስር የሚገኙ ሲሆኑ ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን ትቋሙ ማህበራዊ ሃሊፊነቱን ለመወጣት የመሰረተው የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው ።
27/09/2025
16/09/2025
በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 400 ለሚሆኑ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እድርገናል ።
ድጋፉ የተደረገው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በሚገኝበት
በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ነው ።
በወረዳው ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ 400 ተማሪዎች የተከፋፈለ 4800 የመማሪያ ደብተር ፡ 2400 እርሳስና 2400 እስኪርብቶ የእንሳሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አከበረኝ አላማውን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው አመራሮች በተገኙበት ነው ድጋፉ የተደረገው።
10/09/2025
እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!
ምግባችንን ከጎረቤቶቻችን ጋር እንካፈል!
ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን እንደሁልጊዜው ለአዲስ አመት ከወገኖቹ አልተለየም፡፡
የዛሬ ሁለት አመት ምግባችንን ከጎረቤቶቻችን ጋር እንካፈል በሚል መሪ ቃል በጀመርነው የፍቅር ማዕድ በቪላ አፍሪካና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዕድ አጋርተናል፡፡
በብዙየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋንዴሽን የፍቅር ማዕድ በተደረገው መርሃ ግብር ላይ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ የ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳና የብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ መሰረት ታደሰ ተገኝተዋል፡፡
አዲሱ አመት ለእርስዎና ለቤተሰብዎ የሰላም፣ የጤናና የስኬት ይሁን !
መልካም አዲስ ዓመት!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
Sarbet
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |
| Saturday | 08:00 - 12:00 |