ETHIO FM 107.8
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ ሊተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብ የሚያስቀድም ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ
06/06/2026
በምርጫዉ እለት የፀጥታ ችግር ባጋጠማቸዉ በመኮሳቺ እና ቢሎኖፓ ምርጫ ክልሎች አራት ምርጫ ጣቢያዎች ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ተነገረ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬዉ እለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ሀይሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ግንቦት 24 በተደረገው ጠቅላላ ምርጫ በፀጥታ ችግር ምክንያት የድምፅ መስጠት ሂደት የተቋረጠባቸዉ አካባቢዎች መኖራቸዉን አስታዉሰዋል ።
በዚህም በእለቱ በመኮሰቺ ፥ በቢሎኖፓ እንዲሁም ቀርሳ እና ኩታበር አካባቢዎች ያሉ ምርጫ ክልሎች የሚጠቀሱ ናቸዉ።
እንደ ሰብሳቢዋ ገለፀ በቢሎኖፓ አካባቢ 77 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን የድምፅ መስጠት ሂደት ተጀምሮ በተቋረጠባቸዉ መኖራቸዉን ገልፀዉ በዚህም በ75 ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጠት ሂደቱን ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል።
ሆኖም በሁለት ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የቁሳቁስ ጨምሮ ጉዳት መድረሱን አያይዘዉ ተናግረዋል።
ሌላኛዉ መኮሰቺ 75 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ መሆኑን የተናገሩት ሰብሳቢዋ በ64 የድምፅ መስጠት ሂደቱን ለማስቀጠል መቻሉን ገልፀዋል። በቀሪዎቹ ዘጠኝ ጣቢያዎች ላይ ግን የፀጥታ ችግሩ አስቻይ ባለመሆኑ ሂደቱን ማድረግ እንዳለተቻለ ተነግሯል።
በዚህ ምርጫ ክልል ካሉ የምርጫ ጣቢያዎች ዉስጥ በሁለቱ ጉዳት እንደደረሰ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ሀይሉ በመግለጫቸው ገልፀዋል።
ሌላኛዉ የቀርሳ ምርጫ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት ሂጀቱ የተቋረጠበት አካባቢ ሲሆን ምርጫ ክልሉ 105 የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ የቦርዱ ሰብሳቢ በመጥቀስ ሁኔታዉ እስኪያመች በመጠበቅ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ሂደቱ እንዲቀጥል ተደርጓል ብለዋል።
የኩታበር ምርጫ ክልል 73 የምርጫ ጣቢያዎችን ያሉበት ሲሆን በ19ቱ የድምፅ መስጠት ሂደቱ የተቋረጠባቸዉ መሆናቸው የገለፁት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ አስቻይ ሁኔታ በመፈጠሩ በ15ቱ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ሂደቱን ማካሄድ መቻሉን ገልፀዉ በቀሪዎቹ ግን ሂደቱ አለመካሄዱን አንስተዋል።
ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በ143 የምርጫ ጣቢያዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የድምፅ መስጠት ሂደቱን ያልተካዱባቸዉ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል።
ቁምነገር አየለ
ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
05/06/2026
ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
05/06/2026
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ጥሪ አቀረቡ
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማቆም በሚደረገው አዲስ ጥረት፣ ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመወያየት ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለሩሲያው አቻቸው በጻፉት ይፋዊ ደብዳቤ፤ በአውሮፓ ምድር ላይ እየተካሄደ ያለው ይህ ጦርነት በድጋሚ የአሜሪካ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል እስኪሆን ድረስ ‹‹በዝምታ መጠበቅ ስህተት ነው››ብለዋል።
አክለውም ዘላቂ ሰላም ሊመጣ የሚችለው በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል "በቀጥታ ግንኙነት" ብቻ መሆኑን አስምረውበታል፡፡
የዩክሬኑ መሪ ከዚህ በተጨማሪም በታቀደው የድርድር ወቅት ሙሉ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የጠየቁ ቢሆንም፣ፕሬዝዳንት ፑቲን ግን ይህንን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት ሁለቱ መሪዎች ፊት ለፊት ቢገናኙ ‹‹በጣም መልካም ውሳኔ ይሆናል›› ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቢሮ ክሬምሊን በበኩሉ ደብዳቤው እንደደረሰው አረጋግጧል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በደብዳቤያቸው ላይ ‹‹ከ26 ዓመታት የሥልጣን ቆይታ በኋላ፣ ዕድሜ በፑቲን ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ጀምሯል›› የሚል ጠንከር ያለ ሐሳብ አስፍረዋል።
ይሁን እንጂ ደብዳቤው ይፋዊ የውይይት ግብዣን ያካተተ ሲሆን፤ ‹‹ዩክሬን ይህንን ጦርነት በእኛ እና በእርስዎ መካከል በሚደረግ ቀጥተኛ ግንኙነት ለማቆም ሃሳብ ታቀርባለች፤ በመሆኑም የፊት ለፊት መገናኛ ስብሰባ እንዲደረግ እጠይቃለሁ››ሲሉ ዘለንስኪ ጽፈዋል።
ክሬምሊን ለጥሪው በሰጠው ምላሽ ዘለንስኪ ወደ ሞስኮ በመምጣት ከፑቲን ጋር ለመገናኘት የሚፈልጉ ከሆነ በሩ ክፍት መሆኑን በድጋሚ አስታውቋል።
በዚህ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ትኩረት የሳበው ጉዳይ የኪቭ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ዋሽንግተን ‹‹ሙሉ በሙሉ በኢራን ጉዳይ ላይ ማተኮሯን›› በይፋ ማመኑ ነው።
ዘለንስኪ ‹‹በአውሮፓ ያለው ጦርነት በድጋሚ የአሜሪካ የትኩረት ማዕከል እስኪሆን ድረስ እንዲሁ ዝም ብሎ መጠበቅ ስህተት ይሆናል›› ሲሉ ያለውን ስጋት ገልጸዋል።
ሀና ሰይፉ
ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bole Medehanialem, Selam City Mall 5th Floor
Addis Ababa