MaBizplus

MaBizplus

Share

https://www.tiktok.com/@mabizplus?_r=1&_t=ZS-94lOqkY2SM0 The goal is to give simple, timely insights that help people stay informed through social media.

25/05/2026

የዕቃ አስተላላፊነት ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት ሆነ‼
MaBizplus
​የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ፣ የዕቃ አስተላላፊነት (Freight Forwarding) የኢንቨስትመንት ዘርፍን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ ወሰነ።

​ቀደም ሲል በደንብ ቁጥር 474/2012 መሠረት ዘርፉ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች በቅንጅት ብቻ የተከለለ የነበረ ሲሆን፣ የውጭ ባለሀብቶች ድርሻም ከ49% እንዳይበልጥ ተገድቦ ቆይቷል። ይህ አሰራር በዘርፉ ላይ የሚፈለገውን የአዲስ ኢንቨስትመንት ፍሰት ገድቦት መቆየቱ ተገልጿል።

​ይህ አዲሱ የቦርዱ ውሳኔ፡-

📌​ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት፣

📌​አገራዊ የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ፣
​የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት፣

📌 እንዲሁም ​የአገር ውስጥ ተዋናዮች አቅማቸውን አሳድገው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Debra Markos?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Sudan Street
Debra Markos