Brhanu

Brhanu

Share

ethiopia

11/06/2025

"ሰላም የሚፈልግ ካለ በእኛ በኩል ሁሌም ዝግጁ ነን"
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

መንግስት በሰላም የሚመጡ አካላትን ተቀብሎ ለማወያየት ዝግጁ ነው::ከዚህም ባሻገር ህግ ማስከበር የመንግስት ስራ በመሆኑ መቀጣት ያለበትን አካል መቅጣት ይገባል፥ ሰላም በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ተባብረን መስራት አለብን፡፡ሰላምን በተመለከተ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ትክክለኛ ናቸው::ነገር ግን ሰላም እንዲሰፍን የሚጠይቁ አካላት ራሳቸውን በማግለል የመንግስት ብቻ ጉዳይ የማድረግ ልምምዶች ተገቢ አይደለም::

Photos from Brhanu's post 07/06/2025

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ በአጭር ኮርስ ያሰለጠናቸውን የክፍለ ጦር አመራሮች አስመርቋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በምረቃው ላይ የሥልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ሙሉጌታ አምባቸው ፣ የተቋሙን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑት የክፍለ ጦር አመራሮች ውጤታማ በሆነ መልኩ ስልጠናቸውን አጠናቀው ለምረቃ መብቃታቸውን ገልፀዋል።

የሰራዊቱንና የአመራሩን አቅም ለመጨመር እየተደረገ ያለው ጥረት ማሳያ የሆነ ስልጠና መሰጠቱን የገለፁት አዛዡ ተግባራዊ ልምድ ላላቸው ከፍተኛ አመራሮቹ ተግባር ተኮር የሆነ ስልጠና መሰጠቱ ቀጣይ ለሚገጥማቸው ግዳጅ የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው በጊዜ በአቀራረብና በዓይነቱ ልዩ የነበረና የተቋሙን ፍላጎት ያሳካ መሆኑንም ገልፀዋል።

በምረቃው ላይ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ሀላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና የኮሌጁ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Photos from Brhanu's post 03/06/2025

በክልሉ የተገኘው ሠላም የሠራዊታችን ክቡር መስዋዕትነት ውጤት ነው።
ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

በአማራ ክልል የተገኘው ሠላም የሠራዊታችን ክቡር መስዋዕትነት ውጤት ነው ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በሰሜን ጎንደር ዞን ከደባርቅ ወረዳ አስተዳደር የፀጥታ አካላት ጋር በዞኑ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ሠራዊታችን በማይበገረው የዓላማ ፅናቱ እንዲሁም ጀግንነቱ ክልሉን ከፅንፈኛው መፈንጪያነት ወደ አስተማማኝ ሠላምና ልማት እንዲመለስ አድርጓል ብለዋል።

ፅንፈኛው ኃይል ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና ስልጣንን ኢ-ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ለመያዝ በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተነዳ ያደረገው የቀቢፀ ተስፋ ሙከራ ከባድ ዋጋ አስከፍሎታልም ብለዋል ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ።

እኛ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና ስልጣን በአቋራጭ ለመያዝ የሚመጡ ኃይሎችን ስርዓት እናስይዛለን እያደርግን ያለንውም ይሄንኑ ነው ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ዋጋ የከፈልንበትን ሠላም ማፅናትና በቁርጠኝነት መስራት ከአስተዳደር እንዲሁም ከፀጥታ አካለቱ የሚጠበቅ ቁልፍ ተግባር ስለመሆኑም አሳስበዋል።

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠልና የአካባቢውን ሠላም መጠበቅ እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አቅጣጫ አመላክተዋል።

የዞኑ የፀጥታ ኃላፊዎችም ሚሊሺያ፣ ሠላም አስከባሪውና መደበኛ ፖሊስ ራሱን አደራጅቶ የክልሉን ብሎም የዞኑን ሠላም ለመጠበቅና ለማፅናት በትኩረት እየተሰራ ስመሆኑንም ተናግረዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የፅንፈኛውን አድራጎት ተረድቷልም ተገንዝቧልም ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች አሁንም ሠላሙን ለማፅናት ራሱን አደራጅቶ ስለ ሠላም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ብለዋል። ዘጋቢ አንዷለም ከፍያለው ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

01/06/2025

የሰላም ብቸኛ መንገድ መመካከር መሆኑ የገባቸው !!!
ትላንት በጦር ሜዳ ዛሬ በምክክር መድረክ፤ ለውጥማ አለ።እውነት ለውጥማ አለ። ትላንት በጦርነት ችግርን ካልፈታን ሲሉ የነበሩ ዛሬ ገብቷቸው፣ ተረድተው ለውይይት መድረክ ተቀምጠዋል። ይህ እጅግ ትልቅ ለውጥ፣ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ፣ ትልቅ ምሳሌም ነው። ተመስገን፣ ኢትዮጵያ እውነተኛ እርምጃ እያደረገች ነው።

31/05/2025

ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና ማማ የምታደርገው ጉዞዋን ቀጥላለች!!
ሃገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ነገር ጉዞዋ ወደ ፊት ሆኗል። ወደ ልማት፡ ወደ ብልጽግና፡ ወደ ቀድሞ ከፍታ ብቻ ነው ጉዞው። ምንም እንኳን ፈተናዎች ቢበዙም መሰናክሎች በመንገዷ ቢደረደሩም ሃገራችን ኢትዮጵያን ከጀመረችው የለውጥ ጉዞ የሚገታት የለም። ኢትዮጵያ ድህነትን ታሪክ አድርጋ ለማስቀረትና የተያዘዉን የልማት ጉዞን አጠናክራ ትቀጥላለች። የትንሳኤዋ ጊዜም እጅግ በጣም የቀረበና ወደ በለጸጉት ሃገራት መቀላቀሏም የማይቀር ነዉ።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa