Henok Seid

Henok Seid

Share

Founder @ Hs Group | 🎶 Music Label Hs Entertainment | manufacturing | https://youtube.com/@hsmusicethiopia?si=XuO5BW09ctOKVbxx am singer & songwriter

22/04/2026

ንጉሰ ነገስት አፄ ቴዎድሮስ ሚያዚያ 6 ቀን 1860 ዓ/ም በጀግንነት አረፋ
አባቷ፣ ወንድሟ እና ባሏ የተገደሉባት ምንትዋብ የተሰኘች ሴት ቴዎድሮስን እየተከተለች ታሳቅል ነበር እንዲህ እያለች፦👇

"ጠጅም አያምረኝ፣ ድሮ ጠጥቻለሁ፤
ሥጋም አያምረኝም፣ ቋንጣ ሰቅያለሁ፤
ቢሻኝ ከወንድሜ፣ ካ'ባቴ እበላለሁ፤
ሺ ብረት በግራው፣ ሺ ብረት በቀኙ፤
ሺ ፈረስ ከኋላው፣ ሺህ ፈረስ ከፊቱ፤
ይህን ሳታይ ሞተች፣ ኮሶ ሻጭ እናቱ፤
አንድ እግር በርበሬ፣ መንቀል ተስኗችሁ፤
አቃጥሎ፣ ለብልቦ፣ ፈጅቶ ይግደላችሁ።
ይህንን ሲሰማ፣ ያጓራል ላመሉ፤
ማናት ቢላችሁ፣ ምንትዋብ ናት በሉ።"

እያለች በግጥምም፣ በንግግርም ትሰድብ ታሳቅል ነበር፤ ይህ ወሬ ታዲያ ንጉሡ ጆሮ ደርሶ ተይዛ ቀረበች።

"እስቲ ያልሽውን እዚህ እፊቴ ድገሚው!" ቢሏትስ አንድ ሳታስቀር የስድብ ግጥሟን አወረደችው፥ ቴዎድሮስ ይኸነዜ
"በእኔ ኪሳራ ገነት ልትገቢ?" ብለው ስቀውባት ይልቁንስ እድሜ ዘመኗን ሙሉ ቀለብ እየተሰፈረላት ምንም ሳይጎድልባት እንድትኖር ወስነው አስለቀቋት፥ ኋላ ባለሟሎች "ምነው?" ቢሏቸው
"ዘመዶቿን ሁሉ ገድዬ ልታሞግሰኝ ኖሯል? ልክ ናት!" አሉ። ምንትዋብ ግን እስከ እለተ ሞታቸው በሄዱበት እየተከተለች ስታሳቅላቸው ኖራ በመጨረሻ በመቅደላ አናት ላይ የቴዎድሮስን በድንለመቅበር እንኳ እስክታስቸግር አለቅም ብላ ነበር፥ ያኔ ነው ይህን የገጠመችው👇

"የትግሬን ንጉሥ፣ ሲንቁ ሲንቁ፤
የሸዋንም ንጉሥ፣ ሲንቁ ሲንቁ፤
የጎጃሙን ንጉሥ፣ ሲንቁ ሲንቁ፤
ወንድ ያለ ራስዎ፣ ገድለውም አያውቁ፤
አባ ግራኝ ሞተ፣ የሆዴ ወዳጅ፤
የሚያበላኝ ጮማ፣ የሚያጠጣኝ ጠጅ፤
መቅደላ አፋፉ ላይ፣ ጩኸት በረከተ፤
የሴቱን አናውቅም፣ ወንድ አንድ ሠው ሞተ፤
አባቴን፣ ወንድሜን፣ ልጄን ቢገድሉብኝ ነበር መናደዴ፤
ባሌን ቢገድሉብኝ፣ ነበር መናደዴ፤
ጨከኑ በራስዎ፣ ይቅር አለ ሆዴ"!!! አለች ይባላል!!!

✍️ከሶሻል ሚዲያ

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00