Arts Tv World
Arts Tv World - Digital Media and Satellite Television Service
10/07/2026
የኡጋንዳ ዳኞች "ጌታዬ" እና "እመቤቴ" የሚሉ የቅኝ ግዛት ስያሜዎችን አንተውም አሉ
የኡጋንዳ ጠበቆች ማኅበር ዳኞችን “ጌታዬ” (My Lord) እና “እመቤቴ” (My Lady) በሚሉ ከቅኝ ግዛት በተወረሱ ስያሜዎች መጥራት እንዲቀር ያስተላለፈውን ውሳኔ የአገሪቱ ዳኞች በጽኑ እንደተቃወሙት እየተዘገበ ይገኛል።
ማኅበሩ እነዚህ አጠራሮች እና ፍርድ ቤት ውስጥ ማጎንበስ "የፊውዳልና የቅኝ ግዛት" ቅሪቶች በመሆናቸው ዜጎችን እንደሚያዋርዱና ዳኞችን ከሕዝብ በላይ እንደሚያደርጉ ገልጿል።
በመሆኑም ጠበቆች በምትኩ "ክቡር ዳኛ" ወይም "ክብርት ዳኛ" የሚለውን አጠራር አሊያም የዳኞቹን ስም ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
ይሁንና የዳኞች ቃል አቀባይ ጄምስ ኤርማይ ይህንን ውሳኔ በማጣጣል የጠበቆች ማኅበር ለገለልተኛው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን እንደሌለውና ዳኞች አሁንም በተለመደው ስያሜ መጠራት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
ቢቢሲ እንደዘገበው ይህ የኡጋንዳ ውዝግብ እንደ ኬንያ፣ ዚምባብዌ እና ጋና ባሉ በሌሎች የአፍሪካ አገራትም በፍርድ ቤቶች ውስጥ የቅኝ ግዛት ቅርሶች ተደርገው የሚትዩ እንደ ሰው ሠራሽ ፀጉር እና ካባ የመሳሰሉ ነገሮችን ከፍትሕ ሥርዓቱ ለማስወገድ የሚደረገውን አህጉራዊ ክርክር ዳግም አቀጣጥሎታል።
በአብሳላት ቴዎድሮስ
10/07/2026
በደቡብ ስፔን በተቀሰቀሰ አስከፊ የሰደድ እሳት የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ
በደቡብ ስፔን አንዳሉሲያ ክልል አልሜሪያ ግዛት ውስጥ ትናንት ሐሙስ ከሰዓት በኋላ የተቀሰቀሰው አስከፊ የሰደድ እሳት በክልሉ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አሳዛኝ አደጋ አያስከተለ እንደሆነ የተለያዩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛል።
እስካሁን የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በርካታ ተጎጂዎች ከአደጋው ለማምለጥ ሲሞክሩ በመኪናቸው ውስጥ እሳቱ እንደከበባቸው ታውቋል። በተጨማሪም 19 ሰዎች የት እንዳሉ እስካሁን አልታወቀም ተብሏል።
እሳቱ በሎስ ጋላርዶስ ማዘጋጃ ቤት ተነስተው በኃይለኛ ነፋስ ታግዞ በፍጥነት ወደ ጎረቤቱ ቤዳር የተስፋፋ ሲሆን፣ በደረሰው ጥቅጥቅ ያለ ጭስ ምክንያት ሁለት ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ ተሰምቷል።
ከባድ የቃጠሎ እና የጭስ መታፈን የደረሰባቸው 6 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው የተነገረ ሲሆን፣ ከ50 በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ።
ይፋዊ ምርመራው ቢቀጥልም፣ አደጋው የተከሰተው በወደቀ የኤሌክትሪክ መስመር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ይገኛል።
በአውሮፓ ባለፉት ግንቦት እና ሰኔ ወራት የተመዘገበው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል ምድሪቱን እጅግ ስላደረቃት ለአደጋው መባባስ ትልቁን አስተዋጽኦ ማድረጉ ተዘግቧል።
የዓለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ድርጅት አውሮፓ ከሌላው የዓለም ክፍል በሁለት እጥፍ በፈጠነ ሁኔታ እየሞቀች መሆኑን አስታውቋል።
በአሁኑ ሰዓት ከ300 በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና የስፔን ልዩ ወታደራዊ የአደጋ ጊዜ ክፍል አባላት እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።
በሱራፌል ጉታ
በቻይና የጫማ ፋብሪካ በደረሰ ከባድ የእሳት አደጋ ፕሬዝዳንት ዚ ጂንፒንግ አስቸኳይ ምርመራ አዘዙ
በቻይና ዋነኛ የጫማ ማምረቻ ማዕከል በሆነችው ከተማ በሚገኘው 'ሁይቴንግ' (Huiteng) የጫማ ፋብሪካ ላይ በደረሰ ከባድ የእሳት አደጋ ፕሬዝዳንት ዚ ጂንፒንግ አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥረት እና ምርመራ እንዲካሄድ ማዘዛቸው ተሰምቷል።
በተጨማሪም የደህንነት ጥንቃቄ ጉድለት መኖሩ ከተረጋገጠ ተጠያቂዎች ለሕግ እንዲቀርቡ ጥብቅ ትዕዛዝ መስጠታቸውም ታውቋል።
የቻይና መንግሥታዊ ቴሌቪዥን (CCTV) እንደዘገበው 183 የእሳት አደጋ ተከላካዮች ወደ ስፍራው ተሰማርተው ከ4 ሰዓታት ብርቱ ጥረት በኋላ እሳቱን ተቆጣጥረውታል።
ሆኖም በፎቁ ደረጃዎች ላይ ተከምረው የነበሩ የጫማ ጥሬ እቃዎች የነፍስ አድን ሥራውን እንዳዘገዩት ተገልጿል።
የእሳቱ መነሻ መንስኤ እና ትክክለኛው የጉዳት መጠን እስካሁን ያልተረጋገጠ ሲሆን የ28 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ የተነገረው ይህ አደጋ በቻይና በቅርብ ዓመታት ከተከሰቱት እጅግ ከባድ የኢንዱስትሪ እሳቶች አንዱ በመሆኑ በቀጣይ በስራ ቦታዎች ላይ ባሉ የደህንነት ህጎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ያስገድዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በአሃዱ አባተ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Bole Medhanialem, Awlo Business Center, 8th & 9th Floors, Cameroon Street
Addis Ababa