Opia Notitia

Opia Notitia

Share

Like & share to entertain

31/12/2025

የአመቱ (2025) ምርጥ 11 ስብስብ

21/11/2025

ዛሬ ከመገናኛ ወደ ፒያሳ በታክሲ እጓዛለሁ፡፡
ከጎኔ የተሳፈረችዋ ወጣት “አቁም ሹፊር
ሞባይሌን
ተሠርቄአለሁ” አለች አንዴ ቦርሳዋን አንዴ
ደግሞ እኔን
እየተመለከተች፡፡ ወዲያውኑ ከፊታችን
የተቀመጠው ተሳፋሪ ወደ እኛ ዞሮ“ቁጥርሽን
ስጭኝና ልደውል” አላት ስልኩን አቀባብሎ
እየጠበቀ፡፡ እሷም ሠጠችውና ደወለ፡፡
እኔ ኪስ ውስጥ የስልክ ጥሪ ተሠማ፡፡
ከፊትም ከኋላም ያሉ ተሳፋሪዎች ሁሉ እኔን
አፍጥጠው ተመለከቱኝ፡፡ ከመቅጽበት
“ሌባ_በለው” ብሎ
ከኋላዬ የተቀመጠው ተሳፋሪ የድብድቡን
መጀመር አበሠረ፡፡
ከዛማ ተሳፋሪው በሙሉ እየተነሳ በቦክስ
ይደበድበኝ
ጀመር፡፡ “እንዴ እኔ አልሠረኩም” ስል “የሌባ
አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” አለ ከኋላዬ
የተቀመጠው ተሳፊሪ፡፡ ሞባይሏ የጠፋባት
ተሳፋሪ ደግሞ
“እስኪ ቆዩ አንዴ አትደብድቡት” ስትል“ሌባ
ተይዞ ዱላ
ይጠየቃል” ይላል ከፊት ያለው ተሳፊሪ ያቅሙን
ያክል ቡጢ
እያሳረፈ፡፡ “ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል” ይላል
ሌላኛው ጥፊ
እያበረከተ፡፡
በመጨረሻም “ይሄ የኔ ሞባይል ጥሪ
አይደለም”
ስትል ሁሉም ተሳፋሪዎች ደነገጡ፡፡
ለካንስ ከፊታችን የነበረው ተሳፋሪ ወደ እሷ
ስልክ ሲደውል
ለኔ ደግሞ ጓደኛዬ እየደወለልኝ ኖሯል ስልኬ
የሚጠራው፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ይቅርታ
የጠየቀኝ አልነበረም፡፡
የሆነው ነገር ባጠቃላይ ከወቅቱ ፓለቲካችን ጋር
ይመሳሰላል።................
ለማንኛውም ሁል ግዜ ለመፍረድ አንቸኩል!
ነገሮችን በሰከነ መንገድ እንመልከት!
ይቅርታ ማለት ሽንፈት አይደለም! ለማለት
ያክል እንጂ ነገሩ በኔ ላይ ተከስቶ አይደለም።

17/11/2025

ማስጠንቀቂያ ለተማሪ ቤተሰቦች!

ቤተሰብ ልጆችዎን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲችል ይንገሯቸው። ከሰሞኑን በሀገራችን ጂንካ ከተከሰተው ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ...
👉 ከመመገባቸው በፊት እጆቻቸውን በሚገባ በውሃ እና ሳሙና እንዲያፀዱ፣
👉ብትችሉ ፌስ ማስክ ብታደርጉላቸው።
👉በትምህርት ቤት ውስጥ የተለየ የህመም ስሜት ከተስተዋለበት ተማሪ ጋር ንክኪ እንዳያደርጉ። ካስተዋሉም ለመምህራን እንዲያሳውቁ። መምህራንም ለጤና ባለሙያዎች ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
👉ከጓደኞቻቸው ጋር ቢያንስ ጉዳዩ በጤና ሚኒስቴር በቁጥጥር ስር መዋሉ እስኪገለፅ ድረስ እርስ በእርስ ጨዋታዎችን እና አላስፈላጊ ንክኪዎችን እንዳያደርጉ መምከር ያስፈልጋል።

ጤናችንን በጋራ እንጠብቅ !!

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa