Muhe Bale

Muhe Bale

Share

"united we stand, divided we fall....!"

Photos from Muhe Bale's post 09/02/2026

በዞኖቹ በኮሪደርና በሌሎችም የልማት ስራዎች አስደናቂ የእድገት ለውጥ ተመልክተናል

የካቲት፤2/2018(ኢዜአ)፦በባሌ እና ምስራቅ ባሌ እንዲሁም በሮቤ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ በኮሪደርና ሌሎችም የልማት ስራዎች አስደናቂ የእድገት ግስጋሴ መኖሩ አስደስቶኛል ሲሉ የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሐሰን አሊ ተናገሩ።

አቶ ሐሰን አሊ ከ20 ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው በተለያዩ አካባቢዎች የልማት ስራዎችን እየተመለከቱ ነው።

ሰሞኑንም በባሌ እና ምስራቅ ባሌ እንዲሁም በሮቤ ከተማ በለውጡ መንግሥት የተከናወኑና በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በመሆኑም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ተከናውነው በማየታቸው መደነቃቸውን ገልጸዋል።

በባሌ ዞኖች እና ሮቤ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የመንግስት ቁርጠኝነትና የመፈፀም አቅም ያሳዩ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የሶፍ ኡመር ዋሻ ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መስህብ ሥፍራዎችን በማልማት ረገድ አስደናቂ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በምሥራቅ ባሌ አርብቶ አደር ወረዳ አካባቢዎችም የድርቅ ተጋላጭነትን ለመቋቋም እየተገነቡ የሚገኙ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በግብርናው ዘርፍ እመርታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከረጅም ዓመታት በፊት ''ሮቤን ሳውቃት ትንሽዬ ከተማ ነበረች'' ያሉት አቶ ሐሰን አሁን ላይ በኮሪደር ልማት አሸብርቃ፤ የንግድና የቱሪዝም ማዕከል እንዲሁም ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ሆና "ከደብዛዛ ህይወት ወደ ፍካት ተቀይራ ተመለክቻለሁ ብለዋል።

በመሆኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ በኮሪደርና ሌሎችም የልማት ስራዎች ውበት የተላበሰችው ከተማ በአስደናቂ የእድገት ግስጋሴ ላይ መሆን አስደስቶኛል ሲሉ ተናግረዋል።

የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ደግሞ ታትሮ በመስራት የመጣ መሆኑን አንስተው በከተሞች ልማት፣ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰረተ ልማቶችን በመገንባትና በገጠር ልማት ጭምር መንግስት ጥረት አስደናቂ መሆኑን አንስተዋል።

ከረጅም አመታት የውጭ አገራት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሬ ተመልሼ ተዘዋውሬ በተመለከትኳቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚታየው ለውጥ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የእድገት ግስጋሴ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች ፦ 👉 https://linktr.ee/ENADigital

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Ethiopia
Addis Ababa