Y And G Trading

Y And G Trading

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Y And G Trading, Shopping & retail, Megenagna, Addis Ababa.

05/02/2026

ከ 40 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ ምክሮች

1. የደም ግፊት: 120/80
2. ምት፡ 60 - 100
3. የሙቀት መጠን: 36.8 - 37
4. መተንፈሻ፡ 12-16
5. ሄሞግሎቢን: ወንዶች (13.50-18)
ሴቶች (11.50 - 16)
6. ኮሌስትሮል: 130 - 200
7. ፖታስየም: 3.50 - 5
8. ሶዲየም: 135 - 145
9. ትራይግሊሪየስ፡ 220
10. በሰውነት ውስጥ ያለው የደም መጠን: 5-6 ሊትር
11. ስኳር: ለልጆች (70-130)
አዋቂዎች: 70 - 115
12. ብረት: 8-15 ሚ.ግ
13. ነጭ የደም ሴሎች: 4000 - 11000
14. ፕሌትሌትስ: 150,000 - 400,000
15. ቀይ የደም ሴሎች: 4.50 - 6 ሚሊዮን.
16. ካልሲየም: 8.6 - 10.3 mg/dL
17. ቫይታሚን D3፡ 20 - 50 ng/ml (nanograms per milliliter)
18. ቫይታሚን B12;
200 - 900 pg / ml
🔷እድሜ 40 50 60 እና ከዚያ በላይ ለደረሱት ጠቃሚ ምክሮች፡-

✅የመጀመሪያ ምክር

ምንም እንኳን ህመም ባይሰማዎትም ወይም ምንም ህመም ባይኖርብዎትም በየዓመቱ ቼክ ማድረግ አለብዎት ።

✅ሁለተኛው ምክር

ውሃ ባይጠማም ወይም ባትፈልግም ሁል ጊዜ ጠጣ...ትልቁ የጤና ችግሮች እና አብዛኛዎቹ በሰውነት ውስጥ ባለው የውሃ እጥረት ነው።

✅ሶስተኛ ምክር

ጭንቀት በአጋጠመዎት ጊዜ እንኳን ስፖርት መስራት አያቁሙ ።

✅አራተኛ ምክር

ምግብን ይቀንሱ፣
ከመጠን በላይ የምግብ ፍላጎትን ይተዉት ምክንያቱም መቼም ቢሆን ምግብ ማብዛት ጥሩ አይሆንም።ይመገቡ ነገር ግን መጠኑን ይቀንሱ።

✅አምስተኛ ምክር

በተቻለ መጠን መኪናውን በፍጹም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር አይጠቀሙ የፈለጉበት ቦታ በእግርዎ ለመድረስ ይሞክሩ።

✅ስድስተኛው ምክር
አይናደዱ

ጭንቀትን ይቀንሱ ... ነገሮችን ለመተው ሞክሩ
በሚረብሽ ሁኔታዎች ውስጥ እራስዎን አያካትቱ ።

የእኛን ጤና መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ!

ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን
©ጎኅ መረጃ

16/12/2025

አሻም ቴሌቪዥን ሲጀመር ጀምሮ እንደነበረ
(ቴሌቪዥን ለመከፈት የምትፈልጉ ሰዎች ባታደርጉት)
ለምን ተዘጋ ብዬ ሳስብ
።።።።።
ቴሌቪዥን ለመጀመር ስታስቡ
አላማችሁ ላይ
1:- በግል ከሆነ የምትጀምሩት ቴሌቪዥን ዋና አላማው ንግድ ሆኖ ብር ማስገኝት እንደሆነ ብትረዱ። ስለዚህ ሰርታችሁ ለማትረፍ እንጂ ለማስተማር፣ ማህበረሰብን ለመለወጥ፣ ድህነትን ወይም ጭቆናን ለመታገያ ወዘተ የሚሉ እቅዶችን ከአይምሯችሁ ብታወጡት። አላማችሁ ትርፍ ለማግኝት ሲባል መሃበረሰብን መጥቀም ቢሆን።
2:- ትኩረታችሁ በዚህ ሃገር ተጨባጭ ሁኔታ ማህበራዊ ወይንም ፖለቲካዊ ጉዳይ በፍጹም ባይሆን እና መዝናኛውን ብቻ እጅግ በጣም አጠንክራችሁ ለመስራት ብትነሱ።
3:- ትኩረታቸውን አንድ ሁለት ሶስት ጉዳይ ላይ ብቻ ያደረጉ ሚዲያዎች ቢኖራችሁ። ለምሳሌ አዝናኝ የሆነ ድራማ እና ከድራማ ጋር የተያያዙ ጉዳዬች ብቻ፣ አዝናኝ የሆኑ ሪያሊቲ የስፖርት ኮምፒቲሽን ብቻ፣ አዝናኝ የሆኑ የጤና ሪያሊቲ ሾዎች ብቻ፣ አዝናኝ የሆኑ የምግብ ኮምፒቲሽን ሾዎች ብቻ ወዘተ ቢሆን። እስካሁን በኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ቲቪ ስለሌለ።
።።።።
ፕሮግራሞችን በተመለከተ።
።።።።
1:- ቀድማችሁ መነሻ የሚሆኑ በቂ ፕሮግራም ሳይኖራችሁ ለቢሮ እና ለሰው ሃይል ከፍተኛ ብር ባታወጡ።
2:- ፕሮግራም ከያዛችሁ በሁዋላም ትንሽ ቢሮ ይዛችሁ እቃ እና ቦታ በተውሶም በኪራይም ቢሆን ፈልጋችሁ ከየፕሮግራማችሁ አንዳንድ ክፍል ቀርጻችሁ ፕሮግራማችሁን ብታዩት። እና ቅርጽን፣ ይዘቱን፣ ሆስቱን፣ ፕሮዳክሽኑን ወዘተ ላይ ብትወስኑ። እዚህ ላይ በዛ ያለ ጊዜ ሰጥታችሁ ብትሰሩ።
3:- የፕሮግራም ቅርጻችሁ ላይ ከወሰናችሁ በሁላም። በአነስተኛ የሰው ሃይል ቢያንስ የሁለት ወር ፕሮግራም ብትሰሩ። ከሁለት ወር ፕሮግራም በላይም ባይሄድ። ምክኒያቱም አይር ላይ ከዋለ በሁዋላ ደግሞ የሰውን ግብረ መልስ እያያችሁ ብታሻሽሉት።
4:- በቂ ፕሮግራም ከያዛችሁ በሁዋላም በሙከራ እና በዝግጅት ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በላይ ባትቆዩ። ወዲያው ኤር ብታደርጉ።
።።።
ስቱዲዬ በተመለከተ
።።።
1:- ቲቪ የእይታ ሚዲየም ነው ስለዚህ ለብረሃን፣ ለቀለም ለቁሳቁስ ውበት ትልቅ ቦታ ብተሰጡ
2:- እስቱዲዬው ውስጥ ምንም ቋሚ ነገር ባይኖር። ግድግዳውን ጨምሮ ሁሉንም ተንቀሳቃሽ በማድረግ ለየፕሮግራሙ መለዋወጥ ቢቻል።
3:- እያንዳንዱ የስቱዱዩ እቃ ከአንድ በላይ ጥቅም ቢኖረው። ለምሳሌ እንዱ ግድግዳ ከፊት እና ከሁዋላ የተለያየ ቀለም ቢኖረው ለሁለት ፕሮግራሞች የተለያዩ ባክ ግራውንድ ማግኝት ያስችላል።
3:- የሱቱዲዩ ስፋት እና የጣሪያ ሁኔታን በደም ብታስቡበት። ሰፊ አዳራሽ እና ጣሪያው እረጅም ቢሆን።
4:- የቀረጻ እና የብረሃን የድምጽ እቃዎች መረጣ ብትጠነቀቁ።
5:- ከማስታወቂያ ጋር የተያያዘ ካልሆነ አብዛኛው ፕሮግራም እስቱዲዬ ውስጥ ቢሆን።
6:- ለየት ያለ ነገር ከሌለ ፕራይመሪ እና ሰከንደሪ ቀለሞችን ብታበዙ።
።።።።
ባለሞያን በተመለከተ
።።።
1:- የምትቀጥሯቸው ባለሞያዎች በተለይ በስራ አስኪያጅነት በፕሮግራም ፈጣሪነት ወዘተ ከራዲዩ እና ከመንግስት ቴሌቪዥኖች የመጡ ባይሆኑ። በተለይ ቴሌቪዥኑ የፕሮግራም እና የቢሮ አስተዳደር መሰረቱን እስከሚይዝ ድረስ።
2:- የፊልም እና የድራማ ተሞክሮ ያላቸውንም ለማማከር ካልሆነ በብዛት ባትጠቀሙ። ቴሌቪዥናችሁ የድራማ ካልሆነ በቀር።
3:- በተቻለ ትንሽ ሰው ይዛችሁ ጥሩ ክፍያ ክፍሉ። እረጅም ሰአት የሚሰሩ ቢሆኑ።
:::
ወጪን በተመለከተ
::::
1:- ቢቻላችሁ ገንዘብ ወጪ የሚደረግበትን ሁኔታ አንዴ መስመር እስከሚይዝና ብር የሚወጣባችው ሁኔታዎች ምን ምን እንድሆኑ ዋጋቸውም ምን ያህል እንደሆነ እስክታውቁ ድረስ እራሳችሁ ብትቆጣጠሩ ለሌላ ሰው ባትሰጡ።
2:-
እመለሳለሁ።
©ቴዲ አበራ

08/10/2025

የእርስዎ የቱ ነው?

🧼 Obsessive-Compulsive Disorder
OCD ማለት አዕምሮ ደግመህ አድርግ ካልሆነ ዓለም ያበቃል እያለ ሲያስጨንቅ ነው!

🧼 Types of OCD
1️⃣Washing & Cleaning(መታጠብ እና ማጽዳት) ላይ - እንደገና ካላጸዳሁ/ካልታጠብኩ አንድ መጥፎ ነገር ይከሰታል ብሎ መጨነቅ.

2️⃣ checking( በመፈተሽ ) - በሩን መዝጋቴን check ላድርግ again and again.

3️⃣ Ordering & Symmetry - ነገሮች perfect (ፍፁም) ካልሆነ ሊቋቋሙት የማይችሉት ጭንቀት ዉስጥ መግባት::

4️⃣ Intrusive Thoughts (አስጨናቂ ሀሳቦች)
- እውነተኛ የሚመስሉ አስፈሪ እና አላስፈላጊ በየሆኑ ሀሳቦች መወጠር ::🫤

5️⃣ Hording (መሰብሰብ /ማጠራቀም) - ይህ አንድ ቀን ሊያስፈልገኝ ይችላል፣ መጣል አልችልም ብሎ ሰባራ ዕቃና የተቀደደ ወረቀት ሳይቀር ለማስቀመጥ መገደድ

6️⃣ Mental Rituals - ደህንነት እንዲሰማን በጭንቅላት ውስጥ Repeating prayers፣ መቁጠር ወይም ቃላትን መድገም። [ ፈትያ ]

የናንተ የቱ ነው?

28/09/2025


ወሬ አላበዛብኝም ፤ ብዙዎቹ ደምበኞቼ እንደ እሱ ናቸው፡፡ በዝምታ ወደመጡበት ጉዳይ መግባት ነው ምርጫቸው፡፡

እኔም ደስ የሚለኝ እንደዚያ ሲሆን ነው፡፡

እዚህ የመጣነው ልንጠናና እና ስለ የወደፊት ሕይወታችን ልናወጋ አይደለም፡፡

ያልሆንነውን ነገር በመምሰል የሚጠፋ ጊዜ የለንም፡፡ ስራ ነው የያዝነው፡፡ የንግድ ልውውጥ፡፡ መብራት ይጥፋ ወይ ይብራ የእሱ ምርጫ ነው፡፡

ከዚያ የሚሆነው ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ እኛን ላገናኘን ጉዳይ የተገናኙ ወንድና ሴት መሃል የሆነው ፣ የሚሆነው ነው፡፡ ስጋ ከስጋ ይገናኛል፡፡

በቅጽበት ተጠልዞ የጋለ ስሜት በአፍታ ተፈጥፍጦ ወዲያው ይበርዳል፡፡ የልቡን ካደረሰ በኋላ ፍጥጥ ብሎ እያየኝ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

አተነፋፈሱ ከእርካታ ይልቅ የመሰላቸት ይመስላል፡፡ ከሚገባኝ በላይ ቦታ የወሰድኩበት፣የሚተነፍሰውን አየር የተሻማሁት አይነት፡፡

እንድሄድለት ፈልጓል፡፡ ቀልጠፍጠፍ ብዬ ልብሶቼን ለበስኩ፡፡ ገንዘቤን ቆጠርኩ፡፡

ብዙ ሰዎች እንጀራዬ የወሲብ ንግድ ፣ ስራዬ ገላዬን መቸርቸር ብቻ ይመስላቸዋል ፤ በአንድ በኩል ልክ ናቸው፡፡

ይህንን ስራ ስሰራ በዋነኝነት ለሽያጭ የማቀርበውን ነገር ባለማወቃቸው ግን ተሳስተዋል፡፡

ገላን ሸጦ እንጀራ መግዛት ፊት ለፊት የሚታየውና ቀላሉ የስራዬ ክፍል ነው፡፡

ማንም ሴት እየተደናገረች ፣ እየተደናበረችም ቢሆን ልትወጣው የምትችለው የስራዬ ክፍል፡፡

ወንዶች የእኔን አገልግሎት ለመግዛት የሚራኮቱት ከተርታ ሴት የተለየ ሴትነት ወይም አንዳች ምትሃት ኖሮኝ አይደለም፡፡

ከሌሎች ሴቶች የምመረጠው ‹‹ነይ›› ስባል ሳልግደረደር በመምጣቴ ፣ ‹‹ከፊቴ ጥፊ›› ስባል ደግሞ ሳላንገራግር በመጥፋቴ ነው፡፡

የከጀለኝን ወንድ ሻይ ቡና በለኝ ፣ ምሳ ጋብዘኝ ፣ እራት ውሰደኝ ፣ አንሸራሽረኝ ብዬ ደጅ አላስጠናም ፣ ማገዶ አልፈጅም፡፡

የእኔ ዋጋ ከደቂቃዎች በፊት እንዳሻው በፈነጨብኝ ወንድ አፍ ‹‹በይ ሂጂልኝ›› ስባል ሳላኮርፍ መሄዴ ላይ ነው፡፡

ነገ ስንት ሰአት እንገናኝ?

ቅዳሜና እሁድ እንጦጦ ወይ ደብረዘይት አትወስደኝም?

ይህንን ሂውማን ሄር ( ያኛውን ሱሪ )ይሄኛውን ጫማ አትገዛልኝም?

እስቲ የጥፍር መሰሪያዬን ( በናትህ የማሳጄን) ተው ግን የቤት ኪራዬን ክፈልልኝ? ስለማልል ነው፡፡

መወደዴ የሚመነጨው እኔን ብሎ የመጣ ወንድ የሚፈልገውን ካደረገ በኋላ ባሻው ሰአት እንደ ዶሮ ‹‹እሽ›› እንደ ድመት ‹‹ክፍ›› ብሎ ማባረሩን አሜን ብዬ ከመቀበሌ ነው፡፡

Want your business to be the top-listed Shop in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Megenagna
Addis Ababa
1000