Brightmind

Brightmind

Share

ይህ ፔጅ ለህይወት ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን የሚያስተላልፍ ሲሆን

23/10/2025
Photos from Brightmind's post 02/09/2024

?????

የሰዉ ልጅ ስንት ችግሮችን እየፈታ የአለም ስልጣኔን ጫፍ ያደረሰ አእምሮ እያለዉ። የሰዉን ልጅ ችግር የሚፈቱ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በሚሰራበት ሰዓት ለሰዉ ልጅ ምቾት ስንት እና ስንት የሰዉ ስሪቶች በሞሉበት በዚች ሁሉነገር በሚታይበት አለም...እኛ ኢትዮጱያኖች ግን እርሃብን የሚያጠፋ😭 መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በሽታን,,, የሚያጠፋ መድሃኒት ከመፍጠር ይልቅ ''' የህዝቡን ሰላም ከማስፈን በላይ! የተሻለ ስራ ከመፍጠር ይልቅ .... #ጦርነት ቀለብ ይመስል #ጦርነት ስራ ይመስል #ጦርነት ሰላም ይመስል #ጦርነት ምቾት ይመስል ---በመሳሪያ ድምፅ እና በጥይት ተኩስ በፈንጅ ፍንዳታ ሰዉን ከማስደንገጥ ከማሸበር በላይ መግደል ማሳደድ ማቁሰል መረበሽ እንደመፍትሄ ይዘነዋል። እና መቸ ነዉ የምንነቃዉ ስንት መፍጠር የሚችል አእምሮ ይዘን በመነጋገር በቀላል አማረኛ መግባባት ካቃተን በቀላል ቋንቋ አለመግባባቶችን መፍታት ካልቻልን በጦርነት እስከመቸ መፍትሄ የሚፈለገዉ። አቦ ጦርነት ያስጠላል።😭😭😭😭😭

ጦርነትን ከሩቅ ሆኖ ስለጦርነት ማዉራት በጣም ቀላል ነዉ። ጦርነትን ከሩቅ ሆኖ መደገፍ ማበረታት ቀላል ነዉ። ግን ጦርነትን የሚያዉቀዉ በጦርነት ዉስጥ ያለ ብቻ ነዉ። የሚተኮሰዉ የመሳሪያ ብዛት ምድርን ሲያናዉጣት የተተኮሰ ጥይት መታኝ አልመታኝ ሰዉነትህ ሲረበሽ እዚህም እዛም የፈራረሱ የጋዩ ቤቶች ስታይ የሰዉ ልጅ በየቦታዉ ሰዉነቱ ተገነጣጥሎ ስታይ እንስሳት አራዊት ያለስራቸዉ በየምንገዱ ላይ በየጥሻዉ ሞተዉ ተሰንቅረዉ ሲታዩ። የሚጨሱ የቤት ፍርስራሾች የተረበሸ መንገድ የተቆራረሰ አስፓልት ስታይ ወድህም ወዳም የሚያለቅሱ እናቶች ህፃናቶች ብቻቸዉን የቀሩ ልጅ እናት አባት ስታይ። በዚህም በዛም የተኩስ መዓት ስትሰማ የጭንቀት መዓት ስታስተናግድ የሰላም አየር የሰላምን ትልቅነት አስፈላጊነት የዛኔ ይገባሃል። ጦርነት ያስጠላል....አሁንም ......ወደፊትም.....

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa