Desalegn kebede

Desalegn kebede

Share

ዛሬ ከትላንቱ የተሻለ አድርጎልኛል ነገን ደሞ ከዛሬ የበለጠ ? �ከዘረኝነት እና ከፖለቲካ 100% ነፃ የሆነ
ፔጅ ነው! One Love ���

01/02/2021

ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ እንጦንዮስ እናቱ ትዮብስታ ትባላለች
ሕፃን ሆኖ ሳለ አባቱ አረፈ ሃያ አመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን
ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉስ ዱድያኖስ በሄደ ጊዜ ህዝቡን ጣዖት
እንዲያመልኩ ሠዎችን ሲያስገድድ አየ፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ
ጊዮርጊስም እጅግ አዘነ የአባቱንም ሹመት ተወ ገንዘብ ሁሉ
ለድሆች መፀወተ ሠማዕትነቱንም በንጉሡ ፊት በመቆም
በእግዚአብሔር ታመነ ንጉሱም እግዚአብሔርን እንዲክድና
ለጣዖት እንዲሰግድ አባበለው ቅዱስ ጊዮርጊስም በእምነቱ
ፀና፡፡ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ጊዜ
እንደሚሞት ሦስት ጊዜም እንደሚያስነሳው፡፡ በአራተኛውም
የሰማዕትነት የድል አክሊል እንደሚያቀዳጀው ቃል ገባለት
ሰባት ዓመታትም ስለ ሃይማኖቱ እንደሚሰቃይ ነገረው፡፡ ንጉስ
ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመግደል አትናትዮስ የሚባል
ጠንቋይ አስመጥቶ መርዝ በፅዋ እንዲጠጣ ለቅዱስ
ጊዮርጊስ ሠጠው ቅዱስ ጊዮርጊስም ጠጣው ምንም
አልደረሰበትም ጠንቋዩ አትናትዮስም በቅዱስ ጊዮርጊስ
አምላክ አመነ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም እረፍተ ሞቱ እስኪደርስ
ድረስ ብዙ ተአምራት አደረገ፡፡ ንጉስ ዱድያኖስ እና ሰባው
ነገስታት የተቀመጡባቸውን እንጨት ወንበሮች አለመለመ፡፡
በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት አቃጥለው አስረው ረጩት
ይድራስ በተባለ ተራራ አውጥተው በተኑት ጌታችንም ከሞት
አስነሳው ሙታን አስነሳ ብሩክታዊትን ከድራጎን አዳናት
ተጋድሎውን ፈጸመ ሚያዝያ ሰባት ቀን በሠይፍ ራሱን
ቆረጡት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የተጋድሎውን ፍፃሜ ሠባት አክሊላትን አጎናፀፈው፡፡
የልዳው ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቶቻችንን በአድዋ
ጦርነት ሃይማኖት እንዳይበረዝ ሀገር
እንዳይወረር ርስታችን ለባዕዳን እንዳይሆን በተጋደሉበት
ዘመን ተራዳኢነቱን ገልፆአል፡፡ የመናገሻ ገነተ ፅጌ ጊዮርጊስ
ታቦት ይዘው ጠላትን ድል አድርገዋል በወቅቱ አቡነ ማቴዎስ
የእመቤታችን ታቦትና የቅዱስ ጊዮርጊስም ታቦታት ይዘው
ዘመቱ የአክሱም ካህናትም የእመቤታችን ሥዕልና ሠንደቅ
አላማ ይዘው ተሠለፉ የፅዮን እምቢልተኞችም በእቴጌ
ጣይቱ ፊት ይነፋ ነበር፡፡ ከለሊቱ 11፡00 ሠዓት ጦርነቱ
ሲጀመር እቴጌ ጣይቱ በማጅራታቸው ድንጋይ ተሸክመው
በጉልበታቸው ተንበርክከው በጋለ ፀሎት ወደ እግዚአብሔር
ይፀልዩ ነበር፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም ስራሰላቸው
ለሀገሩ ለሃይማኖቱ የተሠለፈውን አላሳፈረውም የሰለጠነውን
የወራሪ ጦር በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳዒነት
አባቶቻችን ድል ነሱ፡፡
በመፀሐፍ ኢያሱ 10፡1-10÷11 ላይ ኢያሱ ታቦተ ጽዮንን
ይዞ የአሞራውያን ነገስታት ድል እንዳደረገ እግዚአብሔርም
አሞራውያንን ለእስራኤላውያን አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
አባቶቻችንም ይህን አብነት አድርገው ታቦት ይዘው ለሠልፍ
ወጡ፡፡
እነሱም በእምነት ነገስታትን ድል ነሱ ዕብ 11÷33
የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከሞት ድረስ ተደበደቡ
ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ
በእስራትና በወይኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ
በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ በመጋዝ ተሠነጠቁ በሰይፍ
ተገድለው ሞቱ፡፡ ዕብ 11÷36
የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የእመቤታችን
አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

12/04/2020

ሥርዓተ ማኅሌት ዘሆሣዕና ' ሚያዝያ 3'

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለዘዚአክሙ ቆም፤ ዓለማተ ዓለም ሥላሴ ዘአልብክሙ ዓለም፤ እምኔክሙ ፩ በእንተ ፩ አዳም፤ እመኒ በምድር ተወክፎ ለነግደ ጲላጦስ ሕማም፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም።

ዚቅ
እምሆሣዕናሁ አርአየ ተአምረ ወመንክረ፤ ዘኢተገብረ እምቅድመዝ፤ ወኢይከውን እምድኅረዝ።

መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሃላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቌጸል በርእሱ፤ አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።

ዚቅ
ሆሣዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት ለንጉሠ ፳ኤል፤ ዘይሁብ ዝናመ ተወን ከመ ትካት ይመልአ ዓውደ እክል፤ በረከተ ምክያዳተ ወይን።

መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለመትከፍትከ ከመ ልብሰ ክህነት ሎግዮ፤ ጊዜ ጸዓተ ፍትሕ ዘፆረ አርዑተ መስቀል በቀራንዮ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በግዓ መድኃኒት ወአስተሥርዮ፤ አስተዳሎከ ለርእስከ ውስተ ዓፀደ ግፍዕ ተርእዮ፤ ወኲሎ በዘይደሉ አቅደምከ ሀልዮ።

ዚቅ
ኢይብከያ ዘከልአ ደናግለ፤ አርዑተ መስቀል ፆረ፤ እስከ ቀራንዮሰ ሖረ፤ ኢይብከያ ዘከልአ ደናግለ።

መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለአእጋሪከ እለ ጠብዐ ለቀዊም፤ ቅድመ ጲላጦስ ፈታሒ መስፍነ ይሁዳ ወሮም፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘትማልም ወዮም፤ ኀበ ወረደ ወነጠበ ዝናመ አእጋሪከ ደም፤ ለመስቀልከ በሰጊድ ሰላም።

ዚቅ
ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት፤ ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል።

መዝሙር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ፤ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ፤ ሀገረ እግዚአብሔር፤ ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን፤ አዕሩግ ወሕፃናት፤ ነሢኦሙ አዕጹቀ በቀልት፤ እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም፤ ተጽኢኖ ዲበ ዕዋል፤ ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም፤ በትፍሥሕት ወበኃሤት ይሁቦሙ ሃይለ ወሥልጣነ።

አመላለስ
በትፍሥሕት ወበኃሤት/፪/
ይሁቦሙ ሃይለ ወሥልጣነ/፬/

👇👇ተቀላቀሉን 👇👇

13/12/2019

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
➢ የእመቤታችን በዓላት በዓመት ውስጥ የሚከበረው (33) በዓላት
አሏት እነርሱም ፦ ለበረከት
➢ነሐሴ ፯ /7/ ቀን የተጸነስችበት ቀን ነው።
➢ ነሐሴ ፲፮ /16/ የፍልሰቷ መታሰቢያ እስከ ፳፩ /21/
በዓሏ ነው።
➢መስከረም ፲ /10/ የእመቤታችን ሥዕል የመሪና ቦታ
ወደምትሆን ጼዴንያ ወደምትባል አገር ገብታ
የተቀመጠችበት ቀን ነው።
➢. መስከረም ፳፩ /21/ ቀንም ትከበራለች።
➢ጥቅምት ፳፩ /21/ ቀንም ትከበራለች።
➢ኅዳር ፮ /6/ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ
የተቀመጠችበት ቀን ነው።
➢ ኅዳር ፳፩ /21/ ዘካርያስ የመቅረዝ ፋና ሲያበራ
ያየበት ቀን ነው።
➢ ታኅሳስ ፫ /3/ ቤተመቅደስ የገባችበት ቀን ነው።
➢ታኅሳስ ፳፩ /21/ ቀንም ትከበራለች።
➢ታኅሳስ ፳፪ /22/ ደቅስዮስ የሚባል ኤጴስቆጶስ
በዓሏን ያከበረበት ቀን ነው።
➢ታኅሳስ ፳፰/፳፱ /28/29/ መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስን የወለድችበት ነው።
➢. ጥር ፳፩ /21/ የእረፍት ቀኗ ነው።
➢. የካቲት ፲፮ /16/ የምሕረት ቃል ኪዳን ከልጇ
የተቀበለችበት ቀን ነው።
➢የካቲት ፳፩ /21/ ቀንም ትከበራለች።
➢ መጋቢት ፳፩ /21/ ቀንም ትከበራለች።
➢መጋቢት ፳፱ /29/ ልጇን የጸነሰችበት ቀን ነው።
➢. ሚያዝያ ፳፩ /21/ ቀንም ትከበራለች።
➢. ግንቦት ፩ /1/ የልደቷ ቀን ነው።
➢ ግንቦት ፳፩ /21/ ደብረ ምጥማቅ በምትባል
ቤተክርስቲያ ከመላእክት : ከጻድቃንና : ከሰማዕታት : ጋር
ተገልጻ ለ ፭ /5/ ቀናት ከ ፳፩-፳፭ /21-25/ ድረስ
የታየችም ነው።
➢ግንቦት ፳፬ /24/ ወደ ግብጽ አገር የገባችበት ቀን
ነው።
➢. ግንቦት ፳፭ /25/ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ
ያለመለመበት ነው።
➢. ሰኔ ፰ /8/ ልጇ ለሕሙማን ድኃነት የሚሆን ውኃን
ከአለት ላይ ያፈለቀበት ቀን ነው።
➢. ሰኔ ፳ /30/ ሐዋርያት የተሰበሰቡት ልጇም ቤቷን
ለመሥራት የወረደበት ቀን ነው።
➢. ሰኔ ፳፩ /21/ ቤቷን ያከበረበት ቀን ነው።
➢ሐምሌ ፳፩ /21/ ቀንም ትከበራለች

ሲተረጉሙት
➢1. ማርያም ማለት መርሕ ለመንግሥተ / ወደ መንግሥተ
ሰማያት
መርታ የምታገባ ማለት ነው።
➢2. ማርያም ማለት ጸጋና ሐብት ማለት ነው።
➢3. ማርያም ማለት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች
ፍጽምት
ማለት ነው።
➢4. ማርያም ማለት ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ማለት
ነው።
➢5. ማርያም ማለት የብዙዎች እናት ማለት ነው ።
➢6. ማርያም ማለት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል
የምትላላክ ማለት
ነው።
➢ማርያም ማለት በእብራይስጥ ቋንቋ ማሪሃም ከሚለው
ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም የብዙኃን እናት ማለት ነው :
አብርሃም የብዙኃን አባት ማለት እንደሆነ ዘፍ. 17:5
➢በቤተክርስቲያናችን ትምህርትመሠረት ማርያም የሚለው ስም
እያንዳንዱ ፊደል የራሱ የሆነ ትርጉም
ተሰጥቶት ይተረጎማል ይኸውም :-
➢ማ...... ማህደረ መለኮት (የመለኮት ማደሪያ )
➢ር...... ርግብዬ ይቤላ (መኅልየ ማኀልየ ሰለሞን 6:-9)
➢ያ...... ያንቀዐዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት (ፍጥነት ሁሉ
ለምኝልን እያሉ ወደ
አንቺ ያንጋጥጣሉ)::
➢ም...... ምስጋድ ወምስአል ወመስተሥራይ ኃጢያት
(መሰገጃ መለመኛ
የኃጢያት ማስተሰሪያ) ማለት ነው። 2ዜና 7:11-18
➢ማርያም ማለት የብዙዎች እመቤት ማለት ነው:: ማርያም
ማለትመርሕ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው:: ምዕመናን
እየመራች ወደ መንግስተ ሰማያት ታስገባለችና:: አንድም :- ፍፅምት
ማለ

13/12/2019

ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደ ሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች
ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም በንፅህና በቅድስና በቤተ መቅደስ
ኖርሽ እንጂ::
እንኳን ለበዓታ ለማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ

Want your business to be the top-listed Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Abeba
Addis Ababa