LDI

LDI

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from LDI, Addis Ababa.

26/06/2025

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ማኔጀመንት ከሥራ ዘርፎች፣ ከመሪ ሥራ አስፈጻሚዎች እና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በመሆን የ2017 የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በተጨማሪም በ2018 ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ ተወያይቶ የ2018 ዕቅድን በማስቀመጥ ለትግበራው አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

Photos from LDI's post 12/12/2024

‹‹እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት በንብ እርባታ ቴክኖሎጂ ሞዴል የስልጠና ማዕከል እንዲሆን እንሰራለን›› አዉራሪስ ጌታቸዉ(ዶ/ር)

ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም እ/ል/ኢ አዲስ አበባ

እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ከ CRS (Catholic Relief Service) ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጊ ድርጅት ዝርያን ለማሻሻል የእናት ንብ እርባታ እና የማር ምርት ጥራት(Queen rearing and Honey quality) በሚል ርዕስ ዙሪያ በዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሮበርት ኦውን (Dr. Robert Owen) ተሰጥቷል፡፡ ሰልጣኞች ከእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ሁለቱንም ማዕከላት ጨምሮ፤ ከግብርና ሚኒስቴር፤ ከኢትዮጵያ ንብ ሀብት ማህበር፤ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፤ አናቢዎች (ከአዲስ አበባ፤ ቢሾፍቱ፤ ሰበታ) እና ማር አቀነባባሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

CRS ዓለም አቀፍ ድርጅት (Farmers to Farmers Program) በእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በዘርፉ የሚያጋጥማቸውን የእዉቀትና ክህሎት ክፍተት በስልጠና በመሙላት እንዲሁም ችግር ፈቺ ምርምር እንዲሰራ፤ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና እንዲሰጥ እና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርግ አስፈላጊዉን ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ (memorandum of understanding) ተፈራርመዋል፡፡

የተቋሙ የእንስሳት ምርትና መኖ ማቀነባበርና ጥራት ምርምር ዶ/ር አዉራሪስ ጌታቸዉ እንደገለፁት ተቋሙ ለሙከራ ያህል 10 የንብ መንጋ በዘመናዊ ቀፎ ጅማሮ መኖሩን ገልጸው በቀጣይ እስከ 30 የንብ ቀፎ ለማድረስ እና በሆለታ ማዕከልም ተጨማሪ የንብ እርባታ ጣቢያ እንደሚቋቋም ተናግረዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ ሀገራችን 7 ሚሊዮን የንብ ቀፎ ቢኖራት ከ90 በመቶ በላይ በባህላዊ ቀፎ የሚመረት በመሆኑ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ባለመሆኑ አጥጋቢ ምርት እያገኘች አይደለም ብለዋል፡፡ ዘርፉን የማዘመን ሥራ በሚፈለገው ደረጃ ባለመስራታችን ሀገሪቱ በዓመት 500,000 ቶን ማር የማምረት አቅም ቢኖራትም እያመረትን ያለነው ከ147,000 ቶን ማር ያልበለጠ ነው፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00