Defence Construction Enterprise-DCE
PURPOSE
TO ENGAGE IN ANY CONSTRUCTION ACTIVITY MAINLY TO SATISFY THE NATIONAL DEFENSE CONSTRUCTION NEEDS
18/08/2024
28/05/2024
መከላከያ የጀመረውን መጨረስ የሚችል ያሰበውንም የሚያሳካ ተቋም ነው" ዶክተር አብረሃም በላይ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 06 ቀን 2016 ዓ.ም
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ይዞታ ስር በነበረው ወሎ ሰፈር ለሚገነባው ከነዓን ታውን ሺፕ የሚኒ ሲቲ ግንባታ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።
በዚሁ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ የመሠረት ድንጋዩን ካስቀመጡ በኃላ እንዳሉት፦ ለረጅም ዓመታት በመከላከያ ይዞታ ስር የነበሩ መሬቶች መልማት በሚገባቸው ልክ ሳይለሙ ቆይተዋል።
አሁን ላይ ተቋሙ ከተያያዘው ሪፎርማዊ ለውጥና አኳያ በርካታ አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጀምረናል ያሉት ሚኒስትሩ የወሎ ሰፈር ሚኒ ሲቲ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ መከላከያ ለከንዓን ግሩፕ ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሰለሞን ደመቀ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዙ በአቅሙ ልክ ሚናውን መጫወት እንዳይችል ያደረጉት በርካታ ማነቆዎች አሁን ላይ የተፈቱ መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ አቅሙን ከፍ የሚያደርጉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።
የወሎ ሰፈር ሚኒ ሲቲ ግንባታው የበርካታ ዲፕሎማት መቀመጫ ለሆነችውና የአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ ውበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የተናገሩት ደግሞ የከንዓን ታውን ሺፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በረከት ጎይቶም ናቸው።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ባለ 24 ወለል ዘመናዊ የመኖሪያ አፖርታማዎች፣የንግድ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞሎች ለዕይታ ማራኪና ዘመናዊ መንገዶች፣የቢሮ ህንጻዎች፣ ለከተማ መለያ የሚሆን የተዋበ የአርክቴክት ውጤትን ያካተተው የሚኒ ሲቲ ግንባታው ለዘመናዊ ከተማነት ጉልህ ድርሻ የሚያበረክቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:00 |
| Tuesday | 08:30 - 17:00 |
| Wednesday | 08:30 - 17:00 |
| Thursday | 08:30 - 17:00 |
| Friday | 08:30 - 17:00 |
| Saturday | 08:30 - 13:00 |