Wazema Communication And Events

Wazema Communication And Events

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wazema Communication And Events, Arts and entertainment, Addis Ababa.

24/03/2019

በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን የይለፍ ቃል 20 ሺህ በሚሆኑ ፌስቡክ ውስጥ በሚሰሩ ሰዎች ይታወቁ እንደነበር ይፋ ሆነ።

የኢንተርኔት ደህንነት ተመራማሪው ብሬይን ክሬብስ ፌስቡክ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ ረገድ ችግር እንዳለበት አጋልጧል። በጥናቱ መሰረት 600 ሚሊዮን የሚሆኑ የደንበኞች የይለፍ ቃል ምንም አይነት ጠጥበቃ ሳይደረግላቸው እንዲሁ ተጽፎ ለማንም ግልጽ በሆነ መልኩ እንደሚገኝ ተናግሯል።

እነዚህ የይለፍ ቃሎች ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ የተከፈቱ ናቸውም ብሏል። ፌስቡክ ይህን ተከትሎ ሁሉንም የይለፍ ቃሎች በአንድ ቋት ውስጥ ለማስቀመጥ እየሰራሁ ነው በማለት ለማስተባበል ሞክሯል።

ክሬብስ ከፌስቡክ ሰራተኛ አገኘሁት ባለው ተጨማሪ መረጃ መሰረት፤ እንደዚህ አይነት ችግሮች ያጋጠሙት መተግበሪያውን የሚያበለጽጉት ሰዎች መጀመሪያውኑ የይለፍ ቃሉ ወደ ሚስጥራዊ ኮድ እንዳይቀየር አድርገው ስለሚያዘጋጁት ነው ብሏል።

የፌስ ቡክ ኢንጂኔር ሰኮት ሬንፍሮ እንደሚሉት ችግሮቹ ምን እንደሆኑ ለመለየት ጥረት አድርገናል መፍትሄውንም እናመጣለን ብለዋል።

መረጃው እንደሚያሳው አብዛኛዎቹ የዚህ ችግር ተጋላጮች የፌስቡክ ላይት ተጠቃሚዎች ናቸው። ኩባንያው ለሮይተርስ በሰጠው ቃል መሰረት "በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የፌስቡክ ላይት ተጠቃሚዎች፣ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ የሌላ ፌስቡክ ተጠቃሚዎችና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች የችግሩ ተጋላጮች ናቸው።"

ቢሆንም ግን ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለው መፍትሄ የይለፍ ቃልን እንደገና መቀየር ሊሆን ይችላል ተብሏል። የፌስቡክ መግቢያ (Log in) ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም በማለት ባለፉት ጊዜያት የተለያዩ የዜና ምንጮች ሲተቹት ቆይተዋል። መስከረም ወር ላይ የ50 ሚሊዮን ፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ተጋላጭ ሆኖ እንደነበርም ይታወሳል።

በ2018 መጀመሪያ አካባቢም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዋች መረጃ በካምብሪጅ የመረጃ ሳይንስ ኩባንያ እየተጠና መሆኑንም ፌስቡክ ገልጾ ነበር።

30/12/2018

• ሞዛምቢክ ተማሪዎችን ያበረታታሉ በማለት ነፍሰጡር ሴቶች ከሌሎች ጋር ተቀላቅለው እንዳይማሩ የሚከለክለውን ህጓን አነሳች።
በ2003 በወጣው ህግ መሰረት ነፍሰጡሮች የማታ ትምህርት ብቻ እንዲከታተሉ ነበር የተፈቀደው።
• የ112 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት በአሜሪካ በእድሜ ትልቁ ሰው ሪቻርድ ኦቨርተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ሰውዩው ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ዕድሜ ልኬን ሲጋራ ማጨሴ ምንም ጉዳት አላደረሰብኝም ማለታቸው ብዙዎችን አስገርሞ ነበር።
• ታዋቂዋ የሆሊዉድ ፊልም ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ወደፊት ፖለቲካ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ገለጸች።
ተዋናይቷ በአሁኑ ሰአት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ልዩ አምባሰደር ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች።

18/12/2018

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?
ጤናማና የተስተካከለ ሰውነት ያላቸው ሰዎች ቁርሳቸውን አይዘሉም ይባላል። ነገር ግን ቁርስ መብላት ሙሉ በሙሉ ጤናማ ወይም ቀጭን ያደርገናል ማለት አይደለም።
ነገር ግን ምን ያህሎቻችን ቁርስ በትክክለኛው ሰአት እንመገባለን?
ቁርስ ሳይዘሉ መመገብ ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየት የሚቀርበው ምክንያት ሌሊቱን ሙሉ ሲጾም ያደረ ሰውነታችንን በምግብ መጠገን አለብን የሚለው ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን የሚያድገው እና ጉዳት የደረሰባቸው የሰውነት ክፍሎች የሚጠገኑት በምንተኛበት ወቅት መሆኑ፤ ብዙ ጉልበት እንድንጨርስ ያደርገናል።

ስለዚህ በቁርስ ሰአት ምግብ መብላት ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የስነ ምግብ ባለሙያዋ ሳራ ኤልደር ትናገራለች።
ነገር ግን አሁንም ድረስ ቁርስ የዕለቱ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነው ወይ? በሚለው ሃሳብ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም።
ቁርስ አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም?
በተለያዩ ጥናቶች መሰረት ቁርስ መብላትም ሆነ ቁርስ መዝለል ተያይዘው የሚነሱት ካላስፈላጊ ውፍረት ጋር ነው። ምንም እንኳን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦች ቢኖሩም፤ ግንኙነቱ ግን ምንድነው?
ሰባት ዓመታት በፈጀና 50 ሺ ሰዎች በተሳተፉበት አንድ ጥናት መሰረት የተመጣጠነ ቁርስ በሰአቱ የሚመገቡ ሰዎች ምሳ ወይም እራት ሰአት ላይ ከበድ ያለ ምግብ ከሚመገቡ ሰዎች አንጻር፤ የክብደት መጠናቸው ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደተገኘ ያሳያል።

አጥኚዎቹ እንደሚሉት እነዚህ ቁርሳቸውን በትክከል የተመገቡ ሰዎች ቀኑን ሙሉ የሚሰማቸው የረሃብ ስሜት የቀነሰ እንደሚሆንና የሚመገቧቸው ምግቦች መጠን እንደሚቀንስ ያስረዳሉ።
የተመጣጠነ ቁርስ በተገቢው ሰአት መመገብ ያልቻሉት ሰዎች ደግሞ ሰውነታቸው ሌሊቱን ሙሉ ያቃጠለውን ሃይል መተካት ስላለበት፤ ቀኑን ሙሉ ምግብ ቢመገቡም የመርካት ስሜት ስለማይኖራቸው ከመጠን ያለፈ ምግብ እንዲመገቡ ይገደዳሉ።
ሆኖም አጥኚዎቹ ቁርስ ያልተመገቡ ሰዎች በቀጥታ ላላስፈላጊ ውፍረት የተጋለጡ ናቸው የሚለውን ሃሳብ ማረጋገጥ አልቻሉም።

13/12/2018

To get More Information and Videos
subscribe this page https://www.youtube.com/channel/UCZ7Hh5Frl8BDAoF9WuP3A5w?view_as=subscriber

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
24055