EAS
EAS በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ የስፖርት ፕሮግራም ሲሆን ዘውትር አርብ ምሽት ከ 3፡00 – 5፡00 እና እሁድ ከሰአት ከ 6፡00-7፡00 የሚደመጥ ነው፡፡
29/05/2026
372
ስንብት!
ዕለተ አርብ ግንቦት 21 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።
ሁሉም ታላላቅ የአውሮፓ የእግር ኳስ ሊጎች ከሞላ ጎደል ተጠናቀው ባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ ሻምፒዮንስ ሊግ ብቻ ቀርቷል። በነገው ዕለት ይህ ውድድር ፔዤ ከአርሰናል ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።
ይህንን ተከትሎም ጊዜው የዓለም ዋንጫ እና የዝውውር መስኮት ይሆናል። ሁለቱም አሁን የሚዲያ ትኩረቱን እየተረከቡት ይመስላል። የዓለም ዋንጫው ተሳታፊዎች ስብስባቸውን በሚያሳውቁበት ጊዜ በሚፈጠሩ ትኩረት ሳቢ ጉዳዮች ማነጋገሩን ሲቀጥል ዝውውር ደግሞ ሌላኛው ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ሆኗል።
ክለቦች ክፍተታቸውን ለመሙላት ተጫዋች ፍለጋ ገበያ ይወጣሉ። የተሳካላቸው በጊዜ የቤት ስራቸውን መወጣት ሲጀምሩ አንዳንዶቹ ደግሞ ካልተሳኩ ድርድሮች በኋላ የራሳቸውን ውሳኔ እየወሰኑ ነው። ከእነዚህ መካከል የአምናው የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሊቨርፑል ተጠቃሽ ነው። ካለፈው አመት ጀምሮ አነጋጋሪ የነበረው የኢብራሂማ ኮናቴ ኮንትራት ጉዳይ በመጨረሻም ያለስምምነት ተጠናቋል። ኢቡም ቀያዮቹን ለመሰናበት ቀናትን ብቻ ይጠብቃል። ዛሬ የምናነሳው ጉዳይም ይህንኑ ነው።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ነገ በቡዳፔስት ፍፃሜውን ያገኛል።
👉 ፔዤ ወይስ አርሰናል?
👉 የዓለም ዋንጫ በቀጣይ ሳምንት ይጀመራል። ምን ያህል እየጠበቃችሁት ነው?
👉 በዝውውር መስኮቱ የምትደግፉት ክለብ ምን አይነት ስራ እንዲሰራ ትፈልጋላችሁ ?
በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን አድርሱን።
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
24/05/2026
371
ዳኒ ካርቨሀል!
ዕለተ እሁድ ግንቦት 16 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።
ከ 9 ወራት በላይ ሲካሄድ የቆየው የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ዛሬ አመሻሽ 12:00 ላይ በእኩል ሰአት በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።
አርሰናል ዋንጫውን የሚያነሳበት
አንድ ቀሪ ወራጅ ቡድን የሚለይበት
ለአውሮፓ የክለቦች ውድድር የሚሳተፉ ክለቦች የሚለዩበት ይሆናል።
ከኛ ግን ዛሬ የተለያዩ አጫጭር ርዕሶች ጋር ቆይታ እናደርጋለን።
👉 የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ
👉 ኸል ሲቲ ወደ ፕሪምየርሊግ መመለሱ
👉 የፕሪምየርሊግ ቡድኖች ገቢ
👉 ካርቨሀል ከ ማድሪድ ጋር መለያየቱ ..
የእለቱ የፕሪምየርሊግ ጨዋታዎች ውስጥ
👉 ብራይተን ከ ማን ዩናይትድ
ብሩኖ ሪከርዱን ይሰብር ይሆን?
👉 ቶተንሀም ከ ኤቨርተን
ዴቪድ ሞይስ ዌስትሀም እንዲወርድ አልፈልግም ብለዋል።ቶተንሀምን በማሸነፍ የቀድሞ ክለባቸው እንዲቆይ ያደርጉ ይሆን።
👉 የውድድር አመቱ ኮከብ ተጨዋች ለብሩኖ ፈርናንዴዝ ተሰጥቷል።ምን ሀሳብ አላችሁ?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
22/05/2026
370
3 Lions 3 Big Omissions!
ዕለተ አርብ ግንቦት 14 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት "የኛ እና የናንተ" መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ይከታተሉ።
አብዛኛዎቹ የሊግ ውድድሮች ሊጠናቀቁ አንድ ጨዋታ ብቻ የሚቀራቸው ሲሆን አሸናፊዎቹም ተለይተው ታውቀዋል።
በሳምንቱ አጋማሽ አርሰናል፣አል ናስር እና ዛማሌክ የየሊጎቻቸው አሸናፊ መሆናቸው አረጋግጠዋል።
በተለያየ አህጉር ላይ ያሉ እነዚህ ክለቦች የሚያመሳስላቸው የሊግ ዋንጫን ካገኙ አመታት የተቆጠሩ መሆኑ ወይንም
በየሊጎቻቸው ላይ ለአመታት የበላይነት ተወስዶባቸው የነበረ በመሆኑ ዘንድሮ ቀምበሩን ሰብረው የድል ረሀባቸውን ያስታገሱበት አመት ነው።
ደስታውን እያጣጣማችሁ ላላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ!
ለመሆኑ የውድድር አመቱን እንዴት አገኛችሁት?ምንስ ታዘባችሁ?
ዛሬ የውድድር አመቱን መቋጫ በማስመልከት ሰፋ ያለ ጊዜ ለተከበራችሁ አድማጮቻችን እንሰጣለን።
እኛ ለመግቢያ ያህል ግን በእንግሊዝ ብ/ቡድን ምርጫ ዙሪያ ጥቂት እንላለን።
የአርሰናል ደጋፊዎች ደስታው እንዴት እያደረጋችሁ ነው?ይህ በጎ ስሜት ለቻምፕየንስ ሊጉ ፍፃሜ አስተዋፅኦ ይኖረው ይሆን?
የ CR7 ወዳጆችስ? ሮናልዶ የመጀመሪያ የሳውዲ ዋንጫውን ሲያሳካ ምን ተሰማችሁ?
ዩናይትድ ወደ ቻምፕየንስ ሊጉ መመለሱ ተጨዋቾችን ለማዘዋወር ቀላል አያደርግለትም?ለናንተ የቀዮቹ ደጋፊዎች አማካይ ላይ ቡድናችሁ ማንን ቢያስፈርም ትመርጣላችሁ?
አጠቃላይ በውድድር አመቱ ዙሪያ በቀጥታ ስልክ ከናንተ ጋር ከ 3፡45 ጀምሮ ቆይታ እናደርጋለን።
👉 ማጓየር፣ሾው፣ትሬንት፣ፎደን፣ፓልOmissionsይት፣ኮልዊል፣ቶሞሪ.... በምርጫው የሉም።የማን መዘለል አስገረማችሁ?
- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Lideta
Addis Ababa