maruf faris ebrahim
And We have certainly made the Qur’ān easy for remembrance, so is there any who will remember?
ኢቅረእ
20/01/2025
16/12/2022
ለቀሪው እንረባረብ
🍁🍁 🍃 🍁🍁
ሸይኽ ጂሃድ ጀማል ሁሰይን አባ መጫ ይባላሉ። በ1962 ዓ.ል በኦሮሚያ ክልል በኢሉ አባቦራ ዞን ዴዴሳ ወረዳ ደንጎ በተባለች መንደር ተወለዱ። ክፉ ደጉን መለዬት በማይችሉበት የልጅነት ዕድሜ ሙሉውን ቁርኣን አኸተሙ። ለአካለ መጠን ሲደርሱ የሸሪዓ ዕውቀቶችን በተለያዩ የገጠር ቦታዎች ተንቀሳቅሰው ቀሰሙ። ከዚያም በ 1982 ዓ.ል ትውልድ ቀያቸውን ለቀው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ አደረጉ። የከተማ ህይወት ከቀያቸው ለቀው የወጡበትን ዓላማ ሳያስታቸው በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በገጠር የሰነቁትን ዕውቀት በማካፈል ኢስላማዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በቁ።
በ1985 ዓ.ል ታላቁ የአዝሃር ዩኒቨርሲቲ ለአንዳንድ የአፍሪካ አገራት የሰጠውን የነጻ ትምህርት ዕድል በመጠቀም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን ወደ ግብፅ ካይሮ ከተጓዙት አስር ተማሪዎች መካከል አንዱ ሸይኽ ጂሃድ ነበሩ። ቀደም ሲል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች የዕውቀት ጥማቸውን ለማርካት ወደ አዝሃር ዩኒቨርሲቲ የሚያቀኑት በእግር ጉዞ እንጂ ሌላ የትራንስፖርት አማራጮችን ተጠቅመው እንዳልሆነ የሚታወቅ ጉዳይ ነው።
ሸይኽ ጂሃድ ከአዝሃር አሸሪፍ ትምህርት ፋኩልቲ ከሸሪዓ ዲፓርትመንት በ1996 ዓ.ል ተመረቁ። በዚያው ዓመት ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰው አዲስ አበባ በሚገኙት የየመን ኮምዩኒቲ ት/ቤት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት እና በአንደሉስ ት/ቤት ለሰባት ዓመታት በመምህርነት አገለገሉ። በመቀጠል ጅማ በሚገኘው የአባጅፋር ኢስላሚክ ኢንስቲትዩት ለአስር አመታት ሳያቋርጡ እስከ 2014 ዓ.ል ድረስ በመምህርነት እንዳገለገሉ የግል ታሪካቸው ይናገራል።
ሸይኽ ጂሃድ አሁን ላይ የጤና እክል ስላጋጠማቸው ማስተማሩን አቋርጠዋል። የሁለት ሴቶችና የስድስት ወንዶች ልጆች አባት ናቸው። ከሁሉም ጋር መግባባት የሚችሉና ከፊታቸው ፈገግታ የማይለይ የዕውቀት አባት እንደሆኑ እሳቸውን የሚያውቁ ሁሉ ይመሰክራሉ። ብዙዎችን ኮትኩተው በማነጽ ለጥሩ ደረጃ ያበቁና አርዓያ መሆን የሚችሉ የዕውቀት ማዕድ ናቸው ይሏቸዋል። ከሁለት አስርት አመታት በላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉና በዱንያ ጥቅም ተስበው ሌላ አቅጣጫ ሳይመርጡ ጊዜያቸውን ለእስልምና በመስጠት አቅማቸው የፈቀደውን ያህል ያገለገሉ እንቁ መምህር ናቸው።
ወገኖቻችን ሆይ ‼
በአገር ውስጥና ባህር ማዶ የሚገኙ ሃኪሞች እና አማካሪዎች ሸይኽ ጂሃድ በከባድ በሽታ እንደተጠቁ ጠቁመዋል። በሽታው በአንጎል ውስጥ የተፈጠረ እጢ እንደሆነም ገልጸዋል። በሽታው በሰውነት ውስጥ በፍጥነት በመሰራጨት ህይወትን ለከፋ አደጋ የሚጥል በመሆኑ ያለምንም መዘግየት በውጭ አገር ቀዶ ጥገና ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው እነኝሁ የዘርፉ ባለሙያ የሆኑ የተለያዩ አገራት ሃኪሞች በአጽንዖት አሳስበዋል። ህክምናው በቱርክ አገር የሚካሄድ ይሆናል። ለህክምናው የሚያስፈልገውም አጠቃላይ ወጪ 20,000 ዶላር እንደሆነ ተገምቷል። እስካሁን በተደረገ ርብርብ በተለያዩ ባንኮች ድጋፍ የተደረገ አጠቃላይ 1,041, 940 ብር ገቢ ሆኗል።
አላህ ዕውቀትን የሚያነሳው ዑለሞችን ወደርሱ በመውሰድ ነውና ከእጃችን አፈትልከው ካመለጡ በኋላ ራሳችንን ጨለማ እንዳይወርሰን ሸይኽ ጂሃድን ተረባርበን እንታደጋቸው ስል ወንድማዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ከዚህ በታች በተጠቀሱት የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል ማስገባት ትችላላችሁ
ሂጅራ ባንክ
100268510001
Ali Mohammed and/or Yakob Abduletif and/or Anwar Nasser Kassim
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000515546085
Areba qasim or yaeqob abdultif
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
1007900141112
Areba kassim or Yakob Abduletif
አዋሽ ባንክ
014251048378000
Areba kassim /Yakob Abduletif and/or
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa