Fano Intelligence & Security Service-FISS
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fano Intelligence & Security Service-FISS, Legal, Addis ababa, Addis Ababa.
13/12/2024
ከአማራ ፋኖ በወሎ የተላለፈ የስልጠና ጥሪ
ወሎ ቤተ-አምሐራ
የአማራ ህዝብ ዘር ማጥፋት እየፈፀመበት ካለው የአብይ አህመዱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር ሁለንተናዊ ተጋድሎ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል:: ትግሉ ለድል ይበቃ ዘንድ ሁሉም የአማራ ወጣት መደራጀት መሰልጠን መታጠቅና ትግሉን መቀላቀል ብሎም ማስቀጠል ወሳኝ ነው::
በድል ዋዜማ የሚገኘዉ የፋኖ ትግል የሚቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች እየሰፉ በመምጣታቸውና ከፊቱ አዳዲስ ምዕራፎች ስለሚጠብቁት ሰራዊቱን በሰው ሃይል ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ አዲስ ምልምሎችን ለማሰልጠን ወስነናል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም በዚህ የህልዉና ተጋድሎ ወታደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ሽንፈት እየተከናነበ ያለው የብልፅግና አገዛዝ ተስፋ ቆርጦ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን በተለያዩ ቦታዎች በገፍ እያፈሰ ወደ ማሰልጠኛ እያስገባና ጦርነት ላይ እየማገደ ይገኛል::
በመሆኑም የአማራ ወጣቶች በጠላታችሁ አብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ አገዛዝ እየታፈሳችሁ ወደ ጦርነት ከመማገድም ጭምር ነፃ የምትወጡበትን የፋኖ ትግል በመቀላቀል ህዝባችሁን ከተደቀነበት የህልዉና አደጋ እንድትወጡ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
ስለሆነም የአማራ ፋኖ በወሎ የፋኖ አዲስ ምልምል ሰልጣኞች የስልጠና መመልመያ መስፈርቶችን የምታሟሉ ወጣቶች
•ምዕራብ ወሎ ኮር
•ላስታ አሳምነው ኮር
•ምስራቅ አማራ ኮር አንድ እና
•ምስራቅ አማራ ኮር ሁለት እንዲሁም ሌሎች ክፍለጦሮችና ብርጌዶች በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች በመገኘት ስልጠናዉን መውሰድና ህዝባችሁን ብሎም አገራችን ኢትዮጵያን ነፃ ማውጣት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
የመመልመያ መስፈርቶች:-
፩. ሙሉ አካሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
፪. እድሜ ከ18 አመት በላይ የሆነ የሆነች
፫. የአማራ ህዝብ የገጠመዉን የህልዉና አደጋ የተረዳ/የተረዳች እንዲሁም የመረዳት ፍላጎት ያለው
፬. ከማንኛዉም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ/የሆነች
፭. ከዚህ በፊት ምንም አይነት ወንጀል የሌለበት/የሌለባት
፮.የፋኖን ህግና ደንብ ተቀብሎና አክብሮ መታገል የሚችል/የምትችል
፯. የህልዉና ትግሉን እስከ ድል ለመታገል ዝግጁ የሆነ/የሆነች
፰. የት/ት ደረጃ: የተማረም ያልተማረም ሰልጥኖ ለህልዉናው መታገል ይችላል::
፱. ከሚኖርበት አካባቢ መታወቂያ ያለዉና የቅርብ ተጠሪ ያለው
• የምዝገባ ቦታ የተጠቀሱት የአማራ ፋኖ በወሎ ኮሮችና ሌሎች ያልተጠቀሱ ክፍለጦሮችና ብርጌዶች በሚንቀሳቀሱበት ቀጠና ሲሆን የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 5-20 ባሉት ተከታታይ 15 ቀናቶች ነው::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ ስልጠና መምሪያ ክፍል
ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም
07/11/2024
ሰሜን ምስራቅ እዝ ሁለተኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጣዕመ በጀግኖቹ ተጋድሎ ተደመሰሰ!
ዛሬ በቀን 28/2/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ የቃሊሙ ታላቅ ድል በዛሬው እለትም ተደግሟል::
የበላጎው ባለታሪኮች ዞብል አምባ ክፍለጦርና አሳምነው ክፍለጦር በሁለቱ ወንድም አማቾች እየተመራ ታጠቅ ክፍለጦርን ተጠባባቂ አድርገው በጋራ በፈፀሙት ታላቅ ተጋድሎ ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘውን የራያ ቆቦዋ ቃሊም ከተማን ለመቆጣጠር የመጣው ጠላት በጀግኖቹ በርካታ ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ መሆኑ ታውቋል::
ከበላጎ ተራራ ስር የምትገኘዉን ቃሊም ከተማ ለመቆጣጠር አስቦ የመጣው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ አዲስ ምልምል ሰራዊት በጀግኖቹ የዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጆች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ 48ኛ ክፍለጦር 5ኛ እና 2ኛ ሻለቆች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተደምስሰዋል:: በአዲሱ አመት 2017 አ.ም መባቻ ላይ ቃሊም ከተማና አካባቢው ላይ 48ኛ ክፍለጦር 4ኛ ሻለቃ በብ/ጀ አሳምነው ፅጌ ክፍለጦር የጊራናው ባለሽርጡና ታጠቅ ክፍለጦር ሙሉ ለሙሉ መማረኳና መደምሰሷ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው::
በጀኔራል አሰፋ ቸኮል የሚመራው ሰሜን ምስራቅ እዝ ሁለተኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጣእመ በጀግኖቹ ተጋድሎ የተደመሰሰ ሲሆን ሁሉም አጃቢዎቹ እጅ ሰጥተው በቁጥጥር ስር ይገኛሉ::
በዚህ ተጋድሎው በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን ከምርኮ የተረፈዉም እግሬ አውጭኝ በማለት ወልድያ ከተማ እንደገባ ተረጋግጧል::
በምርኮ የተገኙ ድሎች
-ስናይፐርና ብሬን
-ለጊዜው ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ነፍስ ወከፍ ክላሽ
- ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ የብሬንና የክላሽ እንዲሁም የዲሽቃ ተተኳሽ እና በርካታ ቁጥር ያለው ምርኮኛ በነስሮቹ እጅ ላይ ያለ ሲሆን ቀሪውን በቀጣይ ይፋ የምናደርግ ይሆናል ሲሉ የዞብል አምባ ክፍለጦርና የአሳምነው ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነቶች ፋኖ ሃብተማርያም መንበሩ እና ፋኖ ንጉስ አበራ ገልፀዋል::
የህልዉና ተጋድሎው እስከ ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል::
ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ጥቅምት 28/2017 አ.ም
06/11/2024
በዛሬው እለት ማለትም በ 27/2/17 ዓ.ም የ ራያ ቆቦ እና የ ቆቦ ከተማ አመራሮች "የህልም ጉልበት ለ እምርታዊ እድገት" በ ሚል መሪ ቃል በ ራያ ባህል ማእከል እና በራያ ቆቦ መንደፈራ ቀበሌ ህዝቡን ሰብስበው ህዝቡን ሲያወያዩ ውለዋል።
ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካክልም 1) ፋኖን አዳክመነዋል እናም ቶሎ በሰላም ወደ ከተማ እንዲገቡ ንገሯቸው በሌላ አካባቢ ያለው ፋኖ መሳሪያ እያስረከበ በሰላም ወደ ከተማ እየገባ ነው እዚህ ራያ አካባቢ ያለው ብቻ ነው የቀረው እና እንዲገቡ አድርጉ።
2) ከ አሁን በኋላ ከተማ እየገቡ አመራር እንመታለን ካሉ በ ልጆቻቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ ነው እምንወስደው። የሚሉ ሀሳቦችን ምንም የ ፖለቲካ መረጃ በሌለው አርሶ አደር ማህበረስብ ላይ የመርዝ ንግግር ሲረጩ ውለዋል ይህንን ስብሰባ ያካሄዱት የ ገጠር ቀበሌወች ድረስ በመሄድ ነው እና ምናልባትን ወደፊትም በሌሎች ቀበሌወች ሊቀጥል ስለሚችል ይሄን ያክል ሊደነፉበት የቻሉት ምን አይነት አስተማማኝ ዋስትና አግኝተው እንደሆነ ባይታወቅም ይሄ መርዛማ ንግግራቸው ወደሌሎ ች የራያ ቆቦ ቀበሌወችም ሳይዛመት ሀየ ሊባሉ ይግባል።
19/10/2024
Stop drone strikes on innocent amharan people❗❗❗
02/09/2024
ይህ ሰው ብሩክ አበጋዝ ይባላል እናም የወሎ ድምጽ በሚል ገጽ እና በ ወሎ ህብረት የወሎ ህዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል የ አማራን የህልውና ትግል ከአማራ ጠላቶች ባልተናነሰ ለማደናቀፍ እየታተረ ያለ ሰው ነው እናም ይህን ሰው እና ግብረ አበሮቹን(ስማቸውን በዝርዝር በቅርቡ ከንፎቷቸው ) እናሳውቃለን እና ለ ፋኖ ደህንነት በውስጥ መስመር እያንዳንዷን ኣንቅስቃሴ እንድታሳውቁ ስንል ጥሪ እናቀባለን።
የጥንቃቄ መረጃና የትብብር ጥሪ‼️
የአማራ ጠቅላይ ግዛቶችን በጎጥ ለመከፋፈል በተለይ ጎጃምና ጎንደርን በማህበራዊ ሚዲያ ለማናከስ ብልፅግና እየሰራ ይገኛል። ከእያንዳንዱ ከተማ፣ ዞንና ወረዳና የብልፅግና የህዝብ ግንኙነት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል።
በኔ ቀጠና እነማን እንደ ሄዱ የሚለውን በፎቶ አስደግፌ አጋልጣለሁ። በሌሎች አካባቢዎችም ለውስጥ አርበኞች ይሄ አሳይመንት ቢሰጣቸው ጥሩ ነው።
ከሸዋ ቀጠና የተላከልኝ መልዕክት ነው‼️
Via@mulugeta anberber
05/08/2024
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ህዝብ ተፈጥሮዊ የሆነዉን በህይወት የመኖር መብቱን ለማስከበር የህልዉና ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል:: ይህም ከግብ መድረስ የሚችለው የአማራ ህዝብ በቀዳሚነት አማራ ሆኖ ሲቆምና ሲገኝ ብቻ ነው::
በዚህ ሂደትም አንድነትና ህብረት ፈጥሮ መታገል ወሳኝ ነውና በወሎ ቤተ-አምሃራ የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አደረጃጀቶችን ወደ አንድ አደረጃጀት በማምጣት "የአማራ ፋኖ በወሎ" የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በዋርካው ምሬ ወዳጆ ዋና አዛዥነትና በኮሎኔል ፈንታው ሙሃባው ምክትል አዛዥነት እየተመራ እንደነበር ይታወቃል::
ስለሆነም የአማራ ፋኖን ማእከላዊ እዝ ለመመስረት የነበረዉን ሂደት ሆን ብሎ በማቀናጨፍና በመጥለፍ በአቶ እስክንድር ነጋ በኩል ራሱን ሊቀ-መንበር አድርጎ "የጨረቃ" ድርጅት መሰረትኩ ማለቱ የሚታወስ ሲሆን ይህንን ከ60 ሚሊየን በላይ የሚገመተዉን የአማራ ህዝብ ግፍና መከራ ጆሮ ዳባ ያለ አካሄድ እየተቃወምን ባለንበት ሁኔታ ይባስ ብሎ ስራ አስፈፃሚ ማዋቀሩን ይፋ አድርጎዋል::
ስለዚህም የአማራ ፋኖ በወሎ ምክትል አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ፈንታው ሙሃባው ከአማራ ፋኖ በወሎ ከድርጅቱ መርህና አሰራር ብሎም አመራሮች እውቅና ዉጭ የአማራ ፋኖ የሚታገልለትን የአማራን ህዝብ ህልዉና ማረጋገጥ ቀዳሚ መነሻም ሆነ መዳረሻ አላማ ዉጭ ንዋይና ስልጣንን ካስቀደሙ ሃይሎች ጋር ህብረት ፈጥሮ ስለተገኘ ከዛሬ ሃምሌ 29/2016 አ.ም ጀምሮ ከአማራ ፋኖ በወሎ ምክትል አዛዥነት የታገደና የተነሳ መሆኑን እንገልፃለን::
በመጨረሻም እንደ አማራ ፋኖ ይህንን እያደረግን ያለነው የአማራን ህዝብ ህልዉናና ዘላቂ ሁለንተናዊ ጥቅም የምናስጠብቅበት ብቸኛ አማራጫችንና የዚህ ትውልድ የመዳኛ መንገድ የሆነው የተጀመረዉና በድል ዋዜማ የሚገኘው ትግላችን ላይ ዳግም 1983 እና 2010 አ.ም እንዳይፈጠር መሆኑን በመገንዘብ በዉጭም በዉስጥም ያለው መላው የአማራ ህዝብ ከጎናችን እንዲቆምና ትግሉን እንዲጠብቅ ስንል እናሳስባለን::
ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ሃምሌ 29/2016 አ.ም
02/08/2024
የ አማራ ህዝብ እያደረገው ያለውን የህልውና ትግል በ መረጃ እና ደህንነቱ የተሻለ ስራ ለመስራት ይረዳ ዘንድ ታምኖበት ይሄ ፔጅ እንድከፈት ሆኗል።
እናም መላው የ አማራ ህዝብ እንዲሁም የህልውና ትግሉን እሞደግፍ ሁሉ ይሄን ፔጅ ፎሎው፣ላይክ እና ሸር በማድረግ መረጃወችን በቀላሉ ከየትኛውም ቦታ ሆነን ለመለዋወጥ ያመቸን ዘንድ የ በኩላቹን እንድትወጡ እንላለህ።
ድል ለ አማራ ህዝብ!!!
እናሸናለን💪💪💪
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
Addis Ababa