Yohamaf Construction Engineering-YCE

Yohamaf Construction Engineering-YCE

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yohamaf Construction Engineering-YCE, Construction Company, Addis Ababa.

Photos from Yohamaf Construction Engineering-YCE's post 21/02/2021

DCI DN 300mm Pipe laying work

02/03/2020

አንድ ቀን በጨረቃ ላይ እራመዳለሁ!!!(Dr. Eyob)
በሕይወታችን የሚቻለውንና የማይቻለውን የሚወስነው ማን ነው? ገደባችንስ ምንድን ነው? ካለንበት ተነስተን መድረስ ወደምንፈልግበት ቦታ ለመድረስ የሚያስፈልገን ዋነኛ እውነታ ምንድን ነው? እይታ! የአንድ ሰው አይነህሊና ሲበራ የማይቻለው ወደመቻል ይመጣል - በድንገትም ሆነ በሂደት!
ከዚህ በፊት ያልተቻለው ነገር ያልተሞከረው ነገር ነው፤ ያልተሞከረው ነገር ደግሞ በአይነ-ህሊናና በይቻላል መንፈስ ለማየት ያልደፈርነው ነገር ነው፡፡ በማየት፣ በማመን፣ በመንቀሳቀስና ሲወድቁ ተነስቶ በመቀጠል የማይቻል ይቻላል፡
ጄምስ አርዊን (James B. Irwin) እንደማንኛውም ልጅ በአማካኝ ቤት ውስጥ ያደገ ሰው ነው፡፡ በውስጡ ግን ያልተለመደ እይታ የነበረው ልጅ ነበር፡፡ በአንድ ምሽት ጄምስ ራቱን ከበላ በኋላ ሲጫወት ሳለ እናቱ፣ ሰዓቷን ካየች በኋላ፣ “መሽቷልና ወደ መኝታህ መሄድ አለብህ፣ እኔ ስራዬን ስጨርስ እመጣለሁ” ብላ ወደ ክፍሉ ላከችው፡፡ በዚያ ጨረቃዋ ደምቃ በምትታይበት ብሩህ ምሽት ጄምስ ወደክፍሉ የሚወስደውን ደረጃ ከወጣ በኋላ ክፍሉ ውስጥ ተቀመጠ፡፡
እናቱ ከአንድ ሰዓት በኋላ ልታየው ስትሄድ ጄምስ በመስኮቱ አጠገብ ተቀምጦ ብሩኋን ጨረቃ ትኩር ብሎ ሲያይ አገኘችው፡፡ በመገረም፣ “ምን እያደረግህ ነው” በማለት ጠየቀችው፡፡ “ጨረቃዋን እያየሁ ነው” አላት፡፡ “የመኝታህ ሰዓት አልፏል፣ መተኛት ነበረብህ እኮ” አለችው፡፡ በማንገራገር ወደ መኝታው እየሄደ እንዲህ አላት፣ “አንድ ቀን በጨረቃ ላይ እራመዳለሁ”፡፡
አድጎ በበረራ ስልጠና የተመረቀው ጄምስ፣ በአንድ ወቅት በልምምድ አይሮፕላኑ ላይ ከደረሰው የመከስከስ አደጋ ተርፏል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረዶች እንዳለፈ ይነገራል፡፡ ጄምስ አርዊን ያንን ራእይ የተሞላበትን ሃሳብ ለእናቱ ከተናገረ ከ32 ዓመታት በኋላ ጨረቃ ላይ እግራቸው ከረገጡት ሰዎች መካከል ራሱን አገኘው፡፡ የራእይ ጉልበት!!!
(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)፡፡

15/01/2020

የምትገባበትና የምትወጣት በር(Dr. Eyob)
አልፎ አልፎ በትውውቅና በገጠመኝ አንዳንድ እድል በሮች የመከፈታቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሕይወትህ የታላላቅ ስፍራዎችን በር የሚያስከፍትልህ አንድ ቀንደኛና ወሳኝ ነገር አለ፣ እርሱም በእጅህ ላይ ያለው ችሎታ፣ ተሰጥኦ ወይም የአእምሮ እውቀትህ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ እውቀትም በለው ችሎታ፣ ክህሎትም በለው ተሰጥኦ በሄድክበት ሁሉ የእድል በሮችን የሚያስከፍትልህ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ሁኔታው ግን እዚያ ላይ አያቆምም፣ ችሎታህ ባስገባህ ስፍራ የመቆየትህንና ከዚያም አልፈህ የመዝለቅህን ጉዳይ የሚወስን ደግሞ አንድ ሌላ ነገር አለ፡፡ ይህ ነገር ባህሪህ ነው፡፡ ስለዚህም ችሎታህ የወሰደህና ያስገባህ ስፍራ የሚፈልገውን የማንነት ወይም የባህሪይ ጥራት በሚገባ ተገንዝበህ ለዚያ የሚመጥንን ባህሪይ ካልገነባህ በዚያ ከፍታ የሚኖርህ ቆይታ አያስተማምንም፡፡
በኖርክባት የእድሜ ዘመንህ ወደ አንድ ደረጃ በእውቀት ወይም በሌላ መንገድ ምክንያት እድሉን አግኝተው በማሕበረሰቡ መካከል ወደላይ የወጡ ሰዎችን በደንብ አጢናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ለዚያ የሚመጥን ባህሪይ ይዘው አሁንም እያደጉ ሲኖሩ፣ ሌሎቹ ደግሞ ለደረሱበት ክብር የማይመጥንን የሕይወት ዘይቤና ባህሪይ አልለቅ በማለት ይህ የማይለወጥ ሕግ ከወጡበት ከፍታ እንዳወረዳቸው ታስተውላለህ፡፡
መሪ ሆነህና ብዙ ሰዎች እየተከተሉህ ማንም ሰው የማይከተለው ሰው የሚገልጠውን አይነት ባህሪይ መግለጥ አትችልም፡፡ ባለስልጣን ከሆንክ በኋላ አንድ “ተራ ዜጋ” እንደሚኖረው መኖር አትችልም፡፡ ባለ ትዳር ከሆንክ በኋላ ልክ ብቻውን እንዳ ሰው መኖር፣ መናገርና መውጣት መግባት አትችልም፡፡ በአጭሩ፣ ያለህበት ደረጃ የሚጠይቅብህ የባህሪይና የማንነት ከፍታ አለ፡፡
ይህንን እውነታ ለመለማመድ ምናልባት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራስህን መጠየቅ ትችላለህ፡፡ ላለሁበት ደረጃና ለወደፊት ዓላማዬ እንቅፋት የሆነብኝ ባህሪዬ ምንድን ነው? ለመሆንና ለማድረግ ላሰብኩት ነገር ተገቢ የሆነ ማዳበር ያለብኝ ባህሪይ ምንድን ነው? ማስወገድም ሆነ ማዳበር ለሚገባኝ ባህሪ መውሰድ ያለብኝ እርምጃ ምንድን ነው? ሊያግዘኝ የሚችል ሰው ማን ነው?
አትርሳ . . .
• ካለህበት የሕይወት ወይም የኑሮ ደረጃ ጋር አብሮ የሚሄድና የሚመጥን የባህሪይ ልህቀት ሲኖርህ ይህ ጨዋነትህ በዚያ ደረጃ እንድትቆይ ያደርግሃል፡፡
• ለወደፊት ለመድረስ ለምትፈልገው ዓላማና ደረጃ የሚመጥንን ማንነትና ማህሪይ አስቀድመህ በመለየት ያንን መለማመድና ማዳበር ስትጀመር ባለህበት ቦታ በፍጹም አትቆይም፣ በዚያ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ስለሚፈልጉህ ወደሚቀጥለው ደረጃ ትሸጋገራለህ፡፡
• ይህቺ አለም ያጠራት በባህሪይ ጥራት የላቀ ሰው እንጂ ያወቀና የተራቀቀ ሰው አይደለም፡፡
LIKE & SHARE !!!

Want your business to be the top-listed Engineering Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa