Imam Tefera

Imam Tefera

Share

كل نفس ذاقت الموت!
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት!

28/06/2022

የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የአቋም መግለጫ
*****
1. ህዝባችን ሁል ጊዜ ደህንነታቸውን መጠበቅ አለባቸው። ከሌሎች ሀይማኖቶች እና ብሄር ብሄረሰቦች ጋር መግባባት እና በሰላም አብሮ መኖር የሀይማኖታችን መሰረት ነው። የሀገርና የህዝብን ደህንነት የመጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ አለብን። ተቋማችን ለማስተካከልም ሆነ ሃይማኖታዊ መብታችንን ለማስጠበቅ በምንታገልበት ግዜ እያንዳንዱ የሀገራችን ዜጋ መብቱን ማክበር እና በሰላም አብሮ መኖር አለብን። ስለሆነም ህዝባችን ከፀጥታ አካላት ጋር ተስማምቶ የክልሉንና የሀገሪቱን ፀጥታ እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

2. እኛ ሙስሊሞች ነን። የሙስሊም አንድነት ሁሌም አስፈላጊ ነው። በተለይ ጠላት በተለያዩ ሴራዎች አንድነታችንን ለማፍረስ በሚሞክርበት ወቅት አንድነታችን መጠናከር አለበት። አንዴ ሱፊ ሰለፊ እያሉን፣ ሌላ ጊዜ ነባሩ እና መጤ እስልምና በማለት ከፋፍለውናል። ሌሎችም ብዙ ስሞችን ሰጥተውናል። ይህ ድርጊት ኢስላማዊውን ህግ የሚጻረር እና ሙስሊሙን ኡማ የሚያፈርስ ነው። ድርጊቱን በፅኑ እያወገዝን ህዝቡ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን ሴራ ለማክሸፍ በቁርኣንና ሀዲስ ላይ የተመሰረተ አንድነታችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

3. የኦሮሚያ መጅሊስ ስራ አስፈፃሚ ኡለማዎች እና የስራ አመራር ቦርድ ላይ ክፍተቶች እንዳሉ ይታወቃል። ይህን ክፍተት አሟልተናል። አዲሱን የምክር ቤት ፕሬዝዳንትም መርጠን በሙሉ ድምፅ አፅድቀናል።

4. በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየተፈጸመ ያለውን አሰቃቂ ግድያ ሁሉ እናወግዛለን። በተለይ ሰሞኑን በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒ ሻንጉል፣ በራሳችን ክልል በምዕራብ ወለጋ ላይ የተፈፀመው ዘግናኝ ግድያ ከልብ አሳዝኖናል። ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ መስጂድ የተሰደዱትን ህዝበ ሙስሊሙን መግደል ጨካኝ እና ኢሰብአዊ ድርጊት ነው። መሰል ድርጊቶች በአማራ ክልል እና በወለጋ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ ተፈጽመዋል። እነዚህ ግድያዎች ብዙዎቹ በሙስሊሞች ላይ ያተከሩ መሆናቸው ደግሞ ሌላ ስጋት ፈጥሮብናል። ይህ ድርጊት እንደ ሰብአዊም ሆነ እንደማንኛውም ሀይማኖት ዘግናኝ ወንጀል ነው። መንግስት የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ያለፈውንም ሆነ የአሁኑን ግድያ ለህዝቡ እንዲያሳውቅ እናሳስባለን። እንደ ኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ግድያ በእጅጉ አሳስቦናል። እናም ይህንን በጎሳና በሃይማኖት እየከፋፈለ ዜጎችን እየገደለ ያለውን ድርጊት መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው እናሳስባለን።

5. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሆነው የተመረጡትን አዲስ የሽግግር መሪዎች በሙሉ ድምፅ እንደግፋለን። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እነሱን የሚተካ ጠንካራ ተቋም ለማግኘት ለረጅም ጊዜ ሲታገሉ ቆይተዋል። በሽግግር ወቅት በርካታ የህዝብ ጥያቄዎች በተመለሱበት ጊዜ መጅሊሱ ይህንን እድል ተጠቅሞ በተወሰነ ደረጃ ለማሻሻል ተሞክሯል። መጅሊስ በአዋጅ መቋቋሙ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትልቅ እድል ነበር። ለዚህም ስባል የሽግግር መንግስቱን በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ደጋግመን እናመሰግናለን። ነገር ግን የቀድሞው የሽግግር መጅሊስ አመራሮች ተቋሙን ከህዝበ ሙስሊሙ ተቃራኒ አቅጣጫ በመውሰድ ህዝቡ ለብዙ ዙር መራራ ትግል ልጋለጥ ችለዋል። በመሆኑም የፌደራል መጅሊስ ኡለማዎች እና የስራ አመራር ቦርድ አባላት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ህጋዊ ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ ሀሉን ያቀፈ አመራር መርጠዋል። ነገር ግን አመራሩ የመጅሊስን ግቢ ሳይረከብ አንድ ወር ሊሞላው ተቃርቧል። ይህንን ህጋዊ ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የህግ የበላይነትን ማስከበር ከመንግስት ይጠበቃል። ስለሆነም መንግስት ህግ አስከብሮ የህዝቡን ጥያቄ በፍጥነት እንዲመልስ እና የመጅሊሱን ግቢን ለህጋዊው አካል እንዲያስክብ እንጠይቃለን።

6. በፌደራል መጅሊስ ውስጥ ስልጣን የተቆጣጠረው ህገወጥ አመራር በኦሮሚያ መጅሊስ እና በክልሉ ሙስሊሞች ላይ የሚያደርሰውን የስም ማጥፋት ዘመቻን አጥብቀን እናወግዛለን። እንደሚታወቀው በህጋዊ መንገድ ከስልጣን የተነሱ የፌደራል መጅሊስ የቀድሞ አመራሮች በስልጣን ፍቅር ሰክረው በስልጣኑ ለመቆየት ያልተጠቀሙበት ስልት የለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከ120 በላይ ሙስሊሞች በተገኙበት ደም ይፈሳል እንጅ ከስልጣን አልወርድም ሲሉ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። የኦሮሚያ መጅሊስን ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢማሞችን አባረረ፣ የመስጂድ ኮሚቴዎችን አፈናቅሏል፣ ወሃብያዎች ብዙ ሰዎችን በድንጋይ እየገደለ ነው ይላሉ። የኦሮሚያ መጅሊስ አንድም ኢማም አላባረረም፣ የመስጂድ ኮሚቴም አላፈናቀለም። የኦሮሚያ ሙስሊሞችም የተከበሩ ህዝቦች ናቸው። ስማቸው ሙስሊሞች እንጂ ወሃቢዎች አይደለም። እንደዚህ አይነት መጥፎ ሥራዎችንም አይሠሩም። በቀድሞው የፌዴራል መጅሊስ አመራር በኦሮሚያ መጅሊስ እና በክልሉ ሙስሊሞች ላይ የሚደረገው የስም ማጥፋት ዘመቻ በሌሎች ሀይማኖቶች ተከታዮች እና በፖለቲካ ሚዲያዎችም ጭምር እየተካሄደ ይገኛል። እነዚህን ሁሉ የስም ማጥፋት ድርጊቶችን አጥብቀን እያወገዝን መንግስት እነዚህን ሁሉ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን።

7. እንደሚታወቀው የፌደራል መጅሊስ አዲሶቹ አመራሮች የመጅሊሱን ግቢ እስካሁን አልተረከቡም። ስለሆነም የሐጅ ተጓዦች እየተስተናገዱ ያሉት በህገ ወጥ መንገድ በስልጣን ላይ ለመቆየት በሚጥሩ መሪዎች ነው። የነሱ አላማ ህዝበ ሙስሊሙን መከፋፈል እና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በስልጣን ላይ መቆየት ነው። የሚሠሩት ሁሉ በሙስና የተበከለ ነው። በመጀመሪያ 20,000 ሰዎች ሐጅ እንዲሄዱ ተፈቅዶ ነበር፣ ነገር ግን 12,000 ሰው ለመላክ መዝግበዋል። በቀድሞው የፌዴራል መጅሊስ አመራር በአቅራቢያው ካለ ከተማ ፓስፖርት እንዳያወጡ ተደረገ። በዚህ ምክንያት ህዝቡ ወደ ፊንፊኔ መጥቶ ለከፍተኛ ወጪ ተጋልጧል። 12,000 ሰዎች ሁሉንም መስፈርት አሟልተው ከተመዘገቡ በኋላ ዶላር ስለጠፋን 3,000 ሰው ብቻ እንልካለን፣ 1,000 ሰው ተጠባባቂ ናቸው የምል መግለጫ ሰጡ። ህዝቡ ጊዜውንና ገንዘቡን እስኪጨርስ ጠብቀው ትናንት ይህንን መግለጫ ሰጡ። ይህ ማለት 8,000 ሰዎች ያለምንም ጥቅም ጊዜና ወጪን ባክነው ሐጅ ሳይሄዱ ይቀራሉ ነው። ይህ ድርጊት በእውነቱ አሳዝኖናል። ይህ ምክር ቤት ተግባራቸውን አጥብቆ እያወገዘ እነዚህን ሰዎች ለመከራ ያጋለጡ አካላት ተጣርተው ለፍርድ እንዲቀርቡ አጥብቆ ይጠይቃል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00