Sheger daily

Sheger daily

Share

እየተዝናኑ ወቅታዊ የሆነና እውነተኛ መረጃ እንዲደርሶ ከፈለ?

11/05/2023

ኢትዮጵያዊያን ዘላቂ ሰላም በምድራችን እንድረጋገጥ ምን እናድርግ?

፻ ጦራችን በሙሉ ወደ አንድ ታሪካዊ ጠላታችን መመለስ ይኖርብናል። ያ ታሪካዊ ጠላታችን ማን ነው? ያ ታሪካዊ ብቻ ሳይሆን አደገኛ ጠላታችን ድህነት ይባላል።

ሰፊ እና ለምለም መሬት፣ ከበቂ በላይ የሆነ ዓመታዊ የዝናብ መጠን፣ ምቹ የአየር ጠባይ ፣ የምያስብ ጭንቅላት ያለው አምራች የሰው ሀይል እና ወዘተ ይዘን ለዕለት ጉርሻችን ሰፌድ ይዘን ሌሎችን ከመለመን በላይ አደገኛ ጠላት ከቶ ከወደዬት ይገኛል?

በሀገር በቀል ማረሻና በበሬዎቻችንን ተጠቅመን እርሻዎቻችን አርሰን የምግብ ዋስትናችን ሳናረጋግጥ ባዒዳን የሰሩትን "ጠብመንጃ" ሸክፈን እርስበርሳችን መተላለቅ ምን የሚሉት ልክፍት ይሆን?

ጎበዝ ትኩረታችን እርስበርስ ከመተላለቅ ወደ አብሮ መስራትና አብሮ መብላት እንመልስ ፣ ግድ የላችሁም ፈረንጅ በፈጠረው መሳሪያ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰብዓዊ ፍጥሩ ከመግደል ወጥተን እግዚአብሔር በጋራ የለገሰን ኢትዮጵያችን ላይ በጋራ ሰርተን በጋራ ለመጠቀም እንነሳሳ!

፳ እንደ ብሄር፣ ሀይማኖት፣ አከባቢ ያለንን ተጠናጠላዊ ማንነት እና እንደ አንድ ሀገር ዜጋ ያለንን የጋራ ማንነትና ጥቅም ዙሪያ ሚዛናዊ የሆነ የእርስበርስ ግንኙነት ማዳበር ይገባናል እላለሁ።

"የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል" እንደምል ቢሂሉ ባለና በሌላ ጉዳይ እንደባላንጣ እርስበርስ ከመፎካከር ወጥተን በወንድማዊ ትብብር አብረን መኖር አለብን እላለሁ። እኛ ተለያይተን መኖር አንችልም ። አንዳችን ያላንዳችን ምሉዕ የሆነ ህልውናና ክብር የለንም።

ጎበዝ መንቃት ያስፈልጋል።

መልካም ዘመን ለኢትዮጵያችን 🇪🇹

16/03/2023

የአዲስ አበባ ከተማ መስተደድር የ1መቶ ሺህ ቤቶችን ግንባታ ልጀምር ነው አለ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።አስተዳደሩ የህዝቡን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በመንግስት እና በግል አጋርነት የሚሰሩ የመጀመሪያ ዙር 100 ሺህ ቤቶችን ግንባታ ፕሮጀክት ለማስጀመር የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት፣ በከተማችን ያለውን የቤት አቅርቦት እጥረት መንግስት ለብቻው የሚፈታው ባለመሆኑ፣ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በማሳተፍ መካከለኛ ገቢ ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው ይህ የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ህዝባችንን ለማገልገል የገባነውን ቃል በማክበር የህዝቡን ችግር ለሚቀርፉ ስራዎች ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

ለመጀመሪያ ዙር ግንባታም በመንግስት 350 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱ ነው የተገለጸው።በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ 68 የሀገር ውስጥና የውጭ አልሚ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa