Ethio-Mereja

Ethio-Mereja

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio-Mereja, Media/News Company, Addis Ababa.

09/11/2020

ህወሀት ጀት አልጣለችም ለምትሉ ይሄው 😎

Photos from Ethio-Mereja's post 24/10/2020

ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያ በፍጣሪዋ ታምና በሕዝቧ አንድነትና ጽናት የቆመች ሀገር ናት ጥቂት ሰጥተው ብዙ ሊያዟት በሚሞክሩ ተማምና አታውቅም። ሕይወታቸውን ሰጥተው ሊታዘዟት በተዘጋጁ ልጆቿ እንጂ። ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ነው። የገነቧት ደግሞ ልጆቿ ናቸው። እነዚህ ልጆቿ በከፈሉት መሥዋዕትነት ዓለምን ጉድ ያሰኙ ታሪኮችን ሠርታለች። እነዚህን አስደናቂ ታሪኮችን ስትሠራ አብረዋት ታሪክ የሠሩ ወዳጆች ነበሯት። የከዷት ወዳጆችም ነበሩ። ይህ ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም።

ነገር ግን የዓለም ታሪክ ያረጋገጣቸው ሁለት ሐቆች አሉ። ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም የሚለው ቀዳሚው ነው። ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለአንድ ዓላማ ከቆሙ ድል ማድረጋቸው አይቀርም የሚለው ደግሞ ሁለተኛው። የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ግድብ ነው። ኢትዮጵያውያን፣ አሰቡት፤ ኢትዮጵያውያን ጀመሩት፤ ኢትዮጵያውያን ገነቡት፤ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ይጨርሱታል። አይቀሬ ነው።

የሚያዋጣን ኅብረት አንድነታችን ነው። ለእኛ ያለነው እኛ መሆናችንን ዐውቀን ስለ እኛ ጉዳይ እኛው ራሳችን ኢትዮጵያን አለንሽ እንበላት። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን ለኢትዮጵያ እንቁም። ከባዱ ፈተና ከውጭ የሚመጣው አይደለም። ከባዱ ፈተና ተለያይተን ችግሩን ከተጋፈጥነው ነው።

ማንም ገዝቶን አያውቅም። ወደፊትም ማንም አይገዛንም። ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም። ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም።

ክንዳችንን እናበርታ። ትከሻችንን እናስፋ። ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር።

በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ እንቀርም። ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም። አንድ ሆነን የምንይዘው ጋሻ ኃያላኑን ሁሉ ሲመክት የኖረ ነው። ዛሬም ያንን ጋሻ በአንድነት እናንሣ። ሁላችንም፣ በየቦታችን፣ 24 ሰዓት፣ ለኢትዮጵያ እንቁም።

08/10/2020

በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ የተጠረጠረው የፖሊስ መኮንን በ1 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ከእስር ተለቀቀ።

ባልታጠቀ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ የተከሰሰው የቀድሞው የአሜሪካ ፖሊስ መኮንን በዋስ ተለቋል ፡፡

ዴሪክ ቻውቪን የ1ሚሊዮን ዶላር ዋስ በማምጣት ነው ትላንት ጠዋት ከእስር እንደተለቀቀ የፍርድ ቤቱ መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa