KALID ISLAM
የጣት ምልክቱን በመንካት ገፄን በፍጥነት ተቀላቀሉ አመሰግናለዉ:: ��� ገፄን ስለተቀላቀሉ ከልብ አመሰግናለው።���
22/06/2023
ቆሎ ሻጩ ሁጃጅ😊
በሀብቱ የሚታወቀዉ ቱጃር ሰዉዬ በሀጅ ወቅት አረፋ ተራራ ላይ በአከባቢያቸዉ ዝቅተኛ የኖሮ ደረጃ ኖሮት ቆሎ እየሸጠ የሚተዳደርን ሰዉ ያገኘዋል።
በጣም ተደነቀ። በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ከስክሶ ለሀጅ የሄደዉ ባለሀብት የደሀዉን ሰዉዬ በቦታዉ መገኘት አስገርሞታል። ወደ'ሱ ጠጋ በማለት ሰላምታ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩም ሰላምታዉን መለሰለት።
"እንዴት እዚህ ልትገኝ ቻልክ?" በማለት ጥያቄ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩ ትንሽ ግራ ተጋባ። አረፋ ተራራ ላይ ለሌላ ጉዳይ እንዳልመጣሁ እያወቀ ሳለ እንዴት ጠየቀኝ ሲል አሰበ።
"ያዉ ... ለሐጅ ስነ ስርአት ነዋ አመጣጤ"
"ገባኝ ግን ያዉ... በየትኛዉ አቅምህ እዚህ ልትመጣ ቻልክ?.. ማለቴ ቆሎ ቸርቻሪ ሆነህ ሳለ ገንዘቡን ከየት አመጣሃዉ?" በማለት ጠየቀዉ።
ቆሎ ሻጩም በተረጋጋ መንፈስ መለሰለት።
"እኔ ቆሎ ሻጭ ብሆንም ጌታዬ ግን ቆሎ ሻጭ አይደለም! እዚህ ቦታ ላይ ሆኜ እሱን እንድለምነዉና እንድገዛዉ ስለፈለገ ጌታዬ እንድመጣ ፈቀደ። ይኼዉ ነዉ...."
ኢላሂ! ለኛም ሀጅን ወፍቀን! ሁሌም ካንተ ከጃይ ነንና! አንተ ምንም አይሳንህምና 🤲🤲
✍️ KALID ISLAM
⊱⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━
20/04/2023
ሰበር ዜና
_____________________
||♥ እንኳን ለ1444ኛው የኢደል ፊጥር በዓል አደረሳችሁ፣አደረሰን
በዛሬው ዕለት ማለትም ዕለተ ሐሙስ ምሽት ሚያዝያ 12 ቀን 2015፣ የሱዑዲት ዐረቢያ የሥነ- ፈለክ ሳይንቲስቶች የዘመኑ ቴክኖሎጂ ባፈራው ቴሌስኮፕ በመታገዝ ባደረጉት ቅኝ፣ አዲሲቷ የሸዋል ወር ጨረቃ ለመታየት በመቻሏ፣
የሸዋል ወር የመጀመሪያው ዕለት የሚጀምረው፣ ማለትም ዒድ አል-ፊጥር የሚውለው በነገው ዕለት፣ ዕለተ ዐርብ ሚያዝያ 13 ቀን 2015 መሆኑ ተረጋግጧል ሲል "ሐረመይን ሸሪፈይን" የዜና ምንጭ ዘግቧል!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Meskel Square
Addis Ababa