ECNTV
አዳዲስ ሰበር ዜናዎችና መረጃዎችን፣ የመዝናኛ፣ የኪነጥበብ፣ የስፖርት እና ሌሎች አዝናኝ ፕሮግራሞች ይቀርቡበታል። የyoutube ቻናላችንን subscribe ያድርጉ http://www.youtube.com/@ecntvradio
11/02/2026
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት የንቅናቄ ፎረም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በአረርቲ ከተማ በድምቀት ተካሄደ።
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በአረርቲ ከተማ አሰተዳደር በአማረና በደመቀ ዝግጅት በበሱፍቃድ ሪልስቴት ፕሮጀክት ሳይት ግቢ እሁድ የካቲት 1/2018 ዓ.ም. ተካሔደ ።
በአረርቲ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ አቶ ተሻለ ጥላሁን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ማለትም የመንገድ፣የውሀ ፣የመብራትና ሌሎችንም አንስተዋል ።
"ድንቅ የስራ ባህል ወዳለባት ምንጃር ሸንኮራ ወረዳና አረርቲ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ በሰላም መጣችሁ በማለት በጥቅሉ ሰሜን ሸዋ ለኢንቨስትመንት የተመቸ ሰላም ወዳድና ታታሪ ማህበረሰብ ያለበት ዞን ሲሆን ለኢንቨስትመንት በቂ ግብአት ያለው በመሆኑ ከ23 በላይ ማእድናት መኖሩን በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን ለአልሚዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥረም የተናገሩት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ናቸዉ፤ዋና አስተዳዳሪዉ አክለዉም"ልብለልብ ተገናኝተን ሸዋን እናልማ "ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጃር ለኢንቨስትመንት ጥያቄ ፈጥኖ ምላሽ የሚሰጥና ባለፍት አመታት እንደዞን ከ250 በላይ አልሚዎችም ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸውም ጠቅሰዋል ።ምንጃር ለአዲስ አበባ ቅርብ መሆኑ ባለሀብቶች እንክብካቤ ስለሚፈልጉ ልማታቸው ተጠብቆ ምርታማ እንዲሆኑ ሰላም ወዳድ የሆነው ማህበረሰብ ሰላምንና ደህንነትን መጠበቅ እንደሚኖርበትም ገልጸዋል ።
በሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በአቶ ደምሰ ዞናዊ የመወያያ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት በማድረግ ከማህበረሰቡ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የፌደራል የክልልና የዞን አካላት በተገኙበት ምላሽ በመስጠት መግባባት ላይ በመድረስ የእለቱን የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም በልዩ ልዩ ሁነቶች ታጅቦ ማጠናቀቅ ተችሏል ።
በኢንቨስመንት ፎረሙም የተለያዩ የፌዴራል ፣የክልል ፣የዞንና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ወረዳዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካባቢው ተወላጆች ፣ ባለሀብቶች የተገኙ ሲሆን አቶ ዝናቡ ይርጋ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ፣ዶ/ር ደመቀ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ፕላን ቢሮ ሀላፊ ፣አቶ እንድሪስ አብዱ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ፣የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁና ሌሎችም በየዘርፍ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የጸጥታ አካላት የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
እንደሚታወቀው ምንጃር አረርቲ ከተማ
👉ከአዲስ አበባ ምንጃር አረርቲ ከተማ አስተዳደር 133ኪ ሜትር
👉ከደብረ ብርሀን 263ኪ ሜትር
👉ከባህር ዳር 695 ኪ ሜትር
👉ከሞጆ 56ኪ ሜትር
👉ከደብረ ብርሀን በሀገረ ማርያም 178 ኪ/ሜትር ሲሆን በወረዳውና በከተማው የሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ና ምቹ ሁኔታዎችም የሚገኙ ናቸዉ።
ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
👉https://www.facebook.com/ecntv
04/02/2026
መቄዶንያ 🌟 Witness the Heartwarming Journey of Dr. Biniyam and his life-changing work in Mekedoniya! 🌟 In this inspiring video, immerse yourself in the incredible e...
31/01/2026
በ3 ድንቁ ቅፅበት ለወመዘክር ተበረከተ
ደራሲ(አጋዝ) ገብረየሱስ ኃይለማሪያም ያነሷቸው ''የሚሊኒየሙ መሸኛና መቀበያ'' ፎቶግራፎችን ጨምሮ ጥንታዊ መፅሐፍቶቻቸውን ለወመዘክር አበረከቱ።
'ድንቁን ቅፅበት' በሚል የደራሲ ገብረየሱስ ኃይለማርያም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም መባቻ እስከ ወጨጫ ተራራ በመጓዝ ያነሷቸው የሚሊኒየሙ ጀንበር መሸኛና መቀበያ ፎቶግራፎችን ጨምሮ የጫሙት ሽካ፣ ተኬትነት አጂነት/አገኪ፣ ነሁቸርና The Gurage and their Culture የተሰኙ የድርሰት ሥራዎቻቸውን ለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አስረክበዋል።
በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበረሰብ ልማት ዘርፎች ያበረከቷቸው የሕይወት ዘመን አገልግሎቶች "አጋዝ" የሚል ባህላዊ ስያሜ የተሰጣቸው አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃይለማርያም በጉራግኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን ጽፈዋል። ለጉራጌ ባህልና ቋንቋ ልማት ካበረከቱት አስተዋጽኦ ባሻገር የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅትን (ጉህራልድ) መሥርተዋል፤ አገልግለዋልም። በሌሎች ሀገራዊና ዓለምአቀፍ ተቋማትም አሻራቸውን አኑረዋል።
ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከሶዶ ለማ ሚድያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ ነው የተካሄደው።
በዚህም ታላላቅ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበትም የደራሲው ተወዳጅ መጻሕፍትና ያነሷቸው ታሪካዊ ፎቷግራፎች ለታሪካዊው ወመዘክር ተበርክቷል።
''ድንቁ ቅፅበት'' መርሀ ግብር በምርቃት የተጀመረ ሲሆን ደራሲ በብርሃነ ዓለሙ በአጋዝ ገብረየሱሰ መፅሀፍና የአፃፃፍ ስልት ላይ እንዲሁም ገጣሚ ክፍሌ ተመስገን ከጫሙት ሽካ መፅሐፍ የተቀነጨበ ታሪክ አቅርበዋል።
የብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተ መፅሀፍት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ኅላፊ አቶ አባተ ካሣው ሰነዶቹን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር ባለ ታሪኩ አጋዝ ገብረየሱስ ታሪካዊ ሰነዶችን በማስረከባቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልፃለን ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሠረት አመርጋ በበኩላቸው እንዲህ አይነት ታሪካዊ ስራዎች በሰነድነት ታስበው የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ መዘጋጀቱ ለሀገር ትልቅ ነገር ነው ብለዋል። ባህል፣ ቋንቋና ስነ-ፅሑፍን ለትውልድ ከማሸጋገር አንፃር ሚናቸው ትልቅ ነው ያሉት ሀላፊዋ ደራሲው እንደ ሀገር ላበረከቷቸው ታሪካዊ ሰነዶችም ምስጋና አቅርበዋል።
ደራሲ አጋዝ ገብረየሱስ ሀይለማርያም በበኩላቸው ስራዎቹን ሳከናውን እዚህ ይደርሳል ብዬ ባይሆንም የበርካታ ታሪክና ባለታሪኮች ሰነድ መገኛ የሆነው ወመዘክ ፎቶግራፎቼንና የድርሰት ስራዎቼን በአሻራነት መሰነድ በመቻሉ ደስታ ተሰምቶኛል፤ አመሰግናለሁ''ም ብለዋል። ወደፊትም የታሪካዊ ሰነድ ባለቤቶች ስራዎቻቸው ለትውልድ ተደራሽ እንዲሆኑ ለወመዘክር ማስረከብ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ደራሲው ''ድንቁ ቅፅበት'' በሚል መርሃ-ግብሩን ላዘጋጁት ተወዳጅ ሚዲያና ሶዶ ለማ ሚዲያም ልዩ ምስጋና አቅርበዋል።
ℹ️ ለበለጠ መረጃ
▤▤▤▤▤▤▤▤
Youtube ገፃችንን subscribe ያድርጉ
👉 https://www.youtube.com/
Facebook ገፃችንን follow ያድርጉ
ECN TVtv
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa