BE INFORMED FIRST
Welcome Guys! these is one of the best page that you must follow on facebook. we work for better BE INFORMED FIRST
ON TELEGRAM, FACEBOOK AND ON YOUTUBE
05/09/2023
የአርቲስት ሰላም ተስፋዬ መልዕክት
"እግዚአብሔር ሁሌም መሀሪ፣ ይቅርባይ፣ አዛኝ ነው። እሱን አምናቹ መቼም እንደማታፍሩ እኔ ምስክር ነኝ።
በዚህ ሰዓት በምንም ምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ልትሆኑ ትችላላቹ። እኔ እርግጠኛ ሆኜ ምነግራቹ ሁሉንም ነገራቹ እሱ ላይ በእምነት ጣሉ አያሳፍራቹም።
ይሄን ነገር post ያረኩበት ምክንያት
- አንደኛ እግዚአቢሄር ይሄ ምስክርነት ስለሚገባው ነው።
- ሁለተኛ ሰው እሚያልፈበትን አናውቅም እና እርስ በርሳችን መልካም እንሁን።
- ሌላ ደሞ ሁሌ ምቾቴን፣ ደስታየን ብቻ ማሳየት ስለማልፈልግ እና ለብዙ ሰው ትምህርት ሊሆን ይችላል በሚል ነው ።
ከፈጣሪ ውጭ ማንምላይ እምነት አታድርጉ።
ይሄ የተፈጠረው ከ3 ወር በፊት ነው።
ለመመስከር ያበቃኝ እግዚአቢሄር የተመሰገነ ይሁን!"
23/01/2023
"የልጄ ፀጉር እያየነው ረገፈ😭😭😭" #ካንሰር‼️
ይህች አንጀት የምትበላ ህፃን ትባላለች!4ዓመቷ ነው!ከአንድ ዓመት በፊት ቦሌ አራብሳ የሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ከት/ቤት መጥታ ለመቀመጥ ስትሞክር ድንገት ትወድቃለች!!
መቆምና መቀመጥ ሲያቅታት እናትና አባት ተደናግጠው ወደ አቤት ሆስፒታል ሲወስዷት"ምንም የለባትም ህፃን ስለሆነች ነው"ተብሎ በማስታገሻ ቆየች!!ሁለት ወር የራስምታት ማስታገሻ የታዘዘላትን ፓራስታሞል ወሰደች!ምንም ለውጥ የለም!ሲቲ ስካን እና MRI ተነሳች ምንም አልተገኘም!!
ከቀናት በኋላ አንገቷ ስር ቁስል ሲወጣባት ለድጋሚ ምርመራ አቤት ሆስፒታል ሄዱ!!ናሙናዋ ተወስዶ ስትመረመር የደም ካንሰር ምልክት እንደሚያሳይና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በአስቸኳይ እንዲሄዱ ተነገራቸው!!ደነገጡ‼️ያልጠበቁትና ያላሰቡት ዱብዳ ገጥሟቸው ኬሞ በአስቸኳይ ትጀምር ተባሉ!!
እንደ እኩዮቿ ስትቦርቅና ስትስቅ የነበረችው የማርያም ደከመችባቸው፣ጉሊት የምትሰራው እናትና ላዳ ሹፌር የነበረው አባት ስራ አቆሙ!ቤት ኪራይ መክፈል እስኪያቅታቸው ተጨነቁ!!
ወደ ውጭ ሄዳ ታክማ ለመምጣት ከ1,500,000ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ሲያውቁ የበለጠ ግራ ገባቸው!እናንተ ደጋጎች እባካችሁን ምን እናድርግላችሁ? ምን እናግዛችሁ?እያልን ተስፋ እንስጣቸው🙏ምንም ማድረግ ካልቻልን ቢያንስ #እየፀለይን #ሼር በማድረግ ህፃኗን እናድንላቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት በአባት ስም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-1000034719962
አዋሽ ባንክ-01320185936400
አቢሲኒያ-68595398
#ስልክ
0911933141-ሞገስ(አባት)
0984710191-አዳነች(እናት)
21/12/2022
!!
ይድረስ፦
- ለኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ
- ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት
- ለኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
- ለሰላም ሚኒስቴር
ዛሬ የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በቦርድ ደረጃ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰሞኑን ባቀረበች ጥያቄ ዙሪያ ስብሰባ አድርገው ነበር። በስብሰባው ላይ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኒቱን ያስተማረው ትምህርት ላይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፥ ካልጠየቀ ግን፦
- ከሰላም ሚኒስቴር ላይሰንሱ እንደሚሰረዝ
- ሚዲያው እንደሚዘጋ
- እስር እንደሚጠብቀው የተወያዩ ሲሆን የዛሬው ዋናው አጀንዳ በዋናዎቹ አመራሮች ታይቶ የሚወሰን ለነገ ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል።
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የእምነት ተቋምን ሰደበ የሚል ክስ ቀርቦበታል። በእውነት ተሳድቧልን? ቪዲዮውን መመልከት ይቻላል። የጠቀሰው ከቤተ እምነቱ እዕዋልድ መጽሐፍት ነው። መጽሐፍ የእነርሱ ካልሆነ ስም አጥፍቷልና በዚያ ሊጠየቅ ይችላል። ከዚያ ውጪ በየ አደባባዩ የሚሸጥና በቤተክርስቲያኒቱ አሳታሚነትና አከፋፋይነት የታተመን መጽሐፍ ላይ ምላሽ መስጠት በምንም መንገድ ወንጀል አይደለም። ያደረገው ትክክል አይደለም እንኳ ቢባል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተለያዩ መምህራን የወንጌል አማኞችን ሲሰድቡ እና ሁሌም በሚዲያቸው ሲያንቋሽሹ ለምን ዛሬ አገልጋይ ዮናታን ላይ የተወያዩበትን ጉዳይ አላደረጉም? የወንጌል አማኞች ስለ ወንጌል የሚደረግ መገፋትን በደስታ እንቀበላለን። ነገር ግን ፍትሃዊ ያልሆነ አድልዎ ግን አግባብነት የሌለው ነው።
ከጀርባው የተለየ አጀንዳ ከሌለው በቀር አገልጋይ ዮናታን ያስተማረው እና ትክክል አይደለም ያለው ከራሳቸው መጽሐፍ ጠቅሶ ነው እነርሱም ማድረግ ያለባቸው ትክክል አይደለህም ካሉ በመጽሐፍ ቅዱሱ ማስረዳት ነው። በቃ። ሌላው ደግሞ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስራ ሁሉንም እምነቶች እኩል ለአገር አንድነት አያይዞ መስራት እንጂ ለአንደኛው አድልቶ ሌላኛውን መጫን አይደለም።
የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች በዚህ ጉዳይ የመጨረሻውን ውሳኔ ከማስተላለፋቸው በፊት ሊያስቡበት ይገባል። የወንጌል አማኞች ከ ሰላሳ ሚሊዮን በላይ ናቸው ነገሩ በአንድ አገልጋይ ዮናታን ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን መላውን የወንጌል አማኞች ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል። በሌላ መረጃ እንገኛለን። አገራችንን ሰላም ያድርግልን።
ይቅርታ- ይህ ጽሑፍ ቅድሚያ ሲለጠፍ የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋም ጉባኤ ያልነው በስህተት ሲሆን ትክክለኛው የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋም ጉባኤ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
Addis Ababa