John Tube
Fore new Megazen ande News Service
13/06/2020
┉✽̶»̶̥🌺 #የማይሽር ጠባሳ🌺̶̥✽̶┉
❣:¨·.·¨: ❣
══════❁✿❁ ══════
🌺ክፍል አንድ
🌹🌹🌹እውነተኛ ታሪክ
ታሪኬ የሚጀምረው ገና የሁለት ወር ህፃን እያለው እናቴ ለእንጀራ እናቴና ለ አባቴ እኔና ታላቅ ወንድሜን ጥላን የጠፋች እለት ነበር
አዎ ገና የሁለት ወር ጨቅላ እያለው በእንጀራ እናቴ እጅ እድገቴን ጀመርኩ
በርግጥ አባቴ ልጆቹን ወዳጅ ስለነበር እንጀራ እናታችን እኛን ለመጉዳት መንገድ አልነበራትም
ውልደቴም እድገቴም በ ወለጋ ነቀምቴ ነበር አባታችን የራሱ ገቢ ነበረው እናታችን ጥላን ብጠፋም ታላቅ ወንድሜ እጅግ ይወደኝ ስለነበር አንድም ቀን እንድከፋ አይፈልግም ይበልጥ ከአባቴና እንጀራ እናቴ ወንድሜ ይጠብቀኝ ነበር
ከዛ ባሻገር የእርሻ ቦታም ነበረን
አባቴ ከመደበኛ ስራው ባሻገር የእርሻ ቦታውን ዘወትር የመጎብኘት ልምድ ነበረው
ግን ከለታት በአንዱ ቀን ከስራ መልስ ወደ እርሻ ቦታ የመሄድ ልምድ ስላለው እንደ ልማዱ ወደ እርሻ ቦታ አመራ
ነገር ግን የዛሬው የእርሻ ቦታ ጉብኝቱ የህይወቴን ሁለተኛ ምእራፍ ገና በለጋነቴ በጨቅላነቴ እንድጀምር አረጋት
አባቴ በእባብ ተነድፎ በሰዎች እርዳታ እቤት በገባ በ3 ቀን በህይወት አጣነው
ነገር ግን አባቴ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ለእንጀራ እናቴ ቃል አስገባት
"ልጆቼን በምድር ሰጥቼሻለው በሰማይ እቀበልሻለው "
ይህ ቃል በልጅነት አእምሮዬ ተፅፎ ቀረ
በወቅቱ ወንድሜ እንጀራ እናቴ ስታለቅስ እሱም አብሮ እያለቀሰ ነበር እኔ ግን ልጅነቴ ምኑም እንዲገባኝ አላደረገም ነበር
እንጀራ እናቴ ከሌላ የወለደቻቸውና በትዳር ላይ የሚገኙ ሁለት ሴት ልጆች ነበርዋት
አባቴ ከሞተ በኃላ ግን እንጀራ እናቴም ጤንነት ስለማይሰማት ልጆችዋ ወሰድዋት ።ይህ 3ኛው ምእራፍ የኔና የወንድሜ ነበር እኔና እኔን በ6 አመት ልዩነት ያለን ወንድሜ ብቻችንን ኦና ቤት ታቅፈን ቀረን
የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት ቤት ውስጥ ኑሮአችንን መግፋት ጀመርን
ወንድሜ ከኔ የተሻለ ስለነበር ቀን ቀን ምግብ ፍለጋ ሄዶ ማታ ለሱ ሳይበላ ለኔ ይዞ ይመጣ ነበር
በዚህ ሁኔታ ግን ስላልቻልን ጎረቤት ተጠጋን እሱ በእረኝነት እኔ ደግሞ እንደ ልጅነት ልንኖርበት
አዎ የተጠጋናቸው ሰዎች ያላቸው ስለነበሩ ወንድሜ ለኔ መስዋት በመሆን ደሞዙ የኔ በሳላም በደስታ እዛ ቤት መኖር ብቻ ነበር
እንዲ እንዲ እያልን ለአንድ አመት ኖርን
በመሀል የምንኖርባቸው ሰዎች አዲስ አበባ በትዳር የምትኖር ትልቅ ልጅ ነበራቸው
በተሰብዋን ለመጠየቅ በምትመጣበት ሰአት እኔ አይንዋ ውስጥ ገባው
ስለ እኔ ጠየቀች ሁሉንም ተረዳች አዘነችም ወስዳም እንደምታስተምረኝ ቃል ገባች
ወንድሜም በገጠመኝ እድል ደስተኛ ስለነበር ሳያቅማማ ፈቀደ
እኔም ልጅነቴ እንዳለ ያገኘውት እድል አስደስቶኝ ስለ እኔ መሰዋት የሚሆነውን ወንድሜን ትቼ ወደ አዲስ አበባ ገሰገስኩ...... ታሪኩ እንዲቀጥል ሼር 👍👍
✍ይቀጥላል........ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━...........................%.........................
••●◉Join us share
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉
27/03/2020
22/03/2020
በጣሊያን ዛሬ 5,560 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን 651 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ጣሊያን 59,138 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬ በጣሊያን 5,476 ሰው ሞቷል።‼️
አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት ፔጁን
የቴሌግራም መገኛቺን
19/03/2020
😳የ አይን ፍቅር💖/sight love/
የዓይን ፍቅር /Sight love/ የምንለው አንድን ግለሰብ በተደጋጋሚ በመመልከትና አዕምሮአዊ ስዕል በመሳል የፍቅር ስሜትን ውስጣችን ውስጥ ማዳበር ማለት ነው፡፡
ንቁ የሆነው የአዕምሯችን ክፍል በአካባቢው ያሉ መረጃዎችን የማሰባሰብ ኃይል ያለው ክፍል ነው፡፡
ይህ የአዕምሯችን ክፍል ከአካባቢው ያገኘውን መረጃ የማጠራቀሚያ ቦታ ስለሌለው ወደ ሌላኛውና ንቁ ወዳልሆነው የአዕምሮ ክፍል /the unconscious mind/ መረጃዎችን በሙሉ ያስተላልፋሉ፡፡
ንቁ ያልሆነው የአዕምሯችን ክፍል የተሰጠውን መረጃ እውነት አድርጎ የሚቀበልና ኢ-ምክንያታዊ ስለሆነ ንቁ ከሆነው የአዕምሯችን ክፍል የመጣውን መረጃ በሙሉ ያጠራቅማል፡፡
ከአካባቢያችን ጋር መስተጋብር የሚፈጥረው ንቁ የሆነው የአዕምሯችን ክፍል ስለሆነና በአካባቢያችንም ብዙ ነገሮች ስላሉ ይህ የአዕምሯችን ክፍል የተወሰኑት ላይ ትኩረት በማድረግ ወደ ውስጠኛውና ንቁ ወዳልሆነው የአዕምሯችን ክፍል ይልከዋል፡፡
ወደ ዓይን ፍቅር ስንመጣ አንድ ግለሰብ አንድ የሆነ ሰውን በሚያይበትና ልዩ ሆኖ/ና በሚታይበት ወይም በምትታይበት ጊዜ ንቁ የሆነው የአዕምሯችን ክፍል ትኩረት ሰጥቶ መከታተል ይጀምራል፡፡
ልዩነቱንም ያደንቃል /በተደጋጋሚ መረጃውን ያውጠነጥናል/፡፡
ይህ በሚሆንበት ሰዓት አንድን መረጃ ንቁ ወደሆነው የአዕምሯችን ክፍል በተደጋጋሚ ይልካል፡፡
በዚህ ጊዜ ንቁ ያልሆነው የአዕምሯችን ክፍል በተደጋጋሚ የተሰጠውን መረጃ በመቀበል የታየውን /የታየችውን/ ሰው ምስል ቀርፆ ይይዛል፡፡
በማስታወሻ የአዕምሯችን ማዕከልም ውስጥ ይህ ስዕል በሚገባ ይሳላል፡፡
በተጨማሪም ንቁ የሆነው የአዕምሮ ክፍል ስለፍቅር ወይም ስለወሲብ ወይም በጠቅላላው ስለተቃራኒ ፆታ በሚያስብበት ሰዓት የሚያስበው/የሚያገኘው መረጃ ያን ስዕል ይሆናል፡፡
በመሆኑ ፍቅርን ሲያስብ የሚያስበው በአዕምሮው የሳላትን/የሳለውን ሰው ብቻ ይሆናል፡፡
ታዲያማ ይህ ሰው የዓይን ፍቅር ያዘው ማለት ነው፡፡
➢ በክፍል ሁለት አንዳንድ ገጠመኞች እና መፍትሄዎቹን ይዘን እንቀርባለን!!:
አሪፍ አሪፍ ምክሮችን እና ስለ ፍቅር ምንነት በትኩሱ ለማግኘት ፔጁን
🙏 🙏
በቴሌግራም ተቀላቀሉን
💖 💘
💖 💘
💖 💘
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the university
Telephone
Website
Address
Addis Ababa