Broadcasting Media Sources - BMS

Broadcasting Media Sources - BMS

Share

Social media plat form of any legal business Advertising and advocating channel. Private Media Outlet

Photos from Bravo Mentioned Situation -BMS's post 23/06/2025
Photos from Broadcasting Media Sources - BMS's post 08/06/2024

የኢትዮጵያ ሙዚቃ አድባር የስለት ልጅ ኪሮስ አለማየሁ ❗️

( በታዴ የማመይ ልጅ )

የነፍስ ስብራት በሙዚቃ ይታሻል፤ የመንፈስ ቅጭት በዜማ ለዝቦ፣ በግጥም ለስልሶ በሙዚቃ ይጠገናል፡፡ ሙዚቃ እንከን አልባ ሐኪም፣ አቻ የለሽ ወጌሻ ነው፡፡

በዛሬው የትዝታ ገፃችን ስለ ዘመን ተሻጋሪዉ ክቡር ዶክተር ኪሮስ አለማየሁ በጥቂቱ ላወጋችሁ ወደድኩኝ ።

ጉሮሮዉ ላይ አንዳች ተአምር የተገጠመለት ይመስል ድምፁ እንደ ቢላል አዛን፤ እንደ ጂብራን ኪታብ፤ እንደሙሉጌታ ብዕር ከነፍስ ማጀት ይፈልቃል፤ በነፍስ ውቅያኖስ ተጠምቆ እንደ ሐውድ ይጠጣል -የማይጠገብ ሰርክ አዲስ ነው ክቡር ዶክተር ኪሮስ አለማየሁ ፡፡

የኪሮስ ሙዚቃዎች አካባቢን ተሻግረው ዘመናትን ተሸክሞ ሁሌም እንደአዲስ የሚደመጡ ከህሊና የማይጠፋ የብዙዎች ትዝታዎች ሲሆኑ ባለቅኔው ባለብዙ መከሰቻ ባለ እልፍ ገፅታ ያለዉ ሰዉ ነዉ መቼም አንተ ማለታችን እንደ አባት ከማቅረብ ነዉና አንተ እያልኩ መዉደዴን ለመግለጽ ያህል የተሰማኝን ልቀጥል ።

ኪሮስ ከሚሰሙ ሳይሆን ከሚደመጡ ጥቂት ሙዚቀኛዎች መካከልል አንዱ ነዉ ፡፡ስራዎቹ በትላንት የትዝታ ቅኝት ታጅቦ በነገው የምኞት ጓዳና በተስፋ ምርኩዝ የሚነጉዱ ህያው ናቸዉ ።
ለዚህም ባልተጠገበ መረዋ ድምፁ የተጫወታቸውን " እንጓይ ፍስስ ፍቅረይ እና ሌሎችም ሥራዎቹን ማድመጥ ምሥክርነቱን ተዓማኒ ያደርገዋል፡፡

ኪሮስ አለማየሁ በሙዚቃዎቹ ሰላምን የሰበከ ያቀራረበ ያዋሀደ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ
በአብዛኛው የኢትዮጵያዊ ልብ የገባዉ 1979 ዓ.ም " አንጓይ ፍስስ " በተሰኘው ሙዚቃው ሲሆን ከዛ በፊት ከአካባቢው ብዙም ያልተሻገረዉን የትግርኛ ዜማ በአራቱም አቅጣጫ በመላው ኢትዮጵያ ዝናዉ እንዲዳረስ አደረገ የመቀሌ ሸጋ የሚለው ሙዚቃው መቀሌን እንድንናፍቃት አድርጎ በከሳች ምስል እንድናያት አድርጎናል ።
የኪሮስ ድምፅ ቀጭን ወይም ባር ቶን ሲሆን ቤዝ ቲነር ወፈርም እያለ ከሁሉም ጋር የመሰባጠር ልዩ አቅምና ዉበት አለዉ ።

በዘመኑ ያልተሞከሩትን የሙዚቃ ስልት እያንቆረቆረ ሲያዜም ቋንቋው አጥር ሳይገድበን እንድናንጎራጉር መገደዳችን አይቀሬ ነዉ ምክንያቱም ሙዚቃው የኪሮስ ነዉና

በርካቶችን ግጥሞችም እራሱ የደረሳቸው ሲሆን
ለትግርኛ ባህላዊ ሙዚቃ እድገት ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ያልተበረዘ ትክክለኛው የህዝብን ማንነት ጠብቀው የተሰሩ መሆናቸው የሙዚቃ ባለሙያዎች ይመሰክራሉ ።

የኪሮስ ሁሉም ሙዚቃዎቹ ግጥምና ዜማ የራሱ ሲሆን በርካቶቹ ዜማዎቹ የተሰሩት ለ 5 አመታት በእስር ቤት በነበረባቸው ጊዜ ነዉ ።
ኪሮስ ለአምስት አመታት በእስር ከቆየ በኋላ ሲወጣ ህይወት ሁሉን አመቻችታ አልተቀበለችውም አሁን ኤፍኤም መቀሌ ፅ/ቤት የሆነዉ የድሮ የቀይ ሽብር እስር ቤት በህይወት ከወጡ ጥቂት እስረኞች መካከል አንዱ ነበር ከእስር ሲፈታ አለም እጆቿን ዘርግታ አልተቀበለችዉም ይልቅስ መቀሌ አዉቶብስ ተራ አካባቢ ለጎዳና ህይወት ተዳርጎ ነበር ይሉናል ፍቅረስላሴ የተባሉ ሙሁር።

ነገር ግን ጎዳና መዉጣቱ ከክራሩ አለየዉም ለጥበብም ያለዉን ፍቅር አላደበዘዘዉም ይልቅስ" ማስ " " አዉርሶ" "ጉማዬ" " ወዘመይና " መቀሌ የተባሉትን ዜማዎች በመስራት በካሴት አሳትሞ በአምስት ሽህ ብር በመሸጥ ህይወቱን በመቀየር ራስ ቲያትር እንዲቀጠር አስችሎታል ።
ኪሮስና ክራሩ የተገናኙት በእድገት በህብረት ወቅት ነበር
ዋሽንትም አሳምሮ ይጫወታል ማህበረ ኪነት አዉላሎ እና ሌሎች ባንዶችን ጨምሮ በሰባዎቹ በሰሜን በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱት ወገኖች የእርዳታ ማሰባሰብያዎች መስራት ችሏል ።
የስለት ልጅ ኪሮስ መሳቅ መጫወት ሰዎችን መርዳት መገለጫዉ

16/04/2024

ለሸዋ ጠቅላይ ግዛት አለም አቀፍ የእርዳታ ማሰባሰብያ ዝግጅት ለመሳተፍ ይህን ዌብሳይት ይጎብኙ፦ http://shewa.org

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Gambia Street
Addis Ababa
27471