Ethio Technology
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Technology, Computer training school, Addis Ababa.
11/02/2026
ነፍስህ በሰላም ትረፍ!!
ለአቶ አማን ፍስሃጽዮን ፈጣሪ ገነትን ያወርስልን፤ ለወዳጅ ዘመድ እና ለሚዲያው ማህበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
04/02/2026
በኢትዮጵያ የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአይፎን በከፍተኛ መጠን ብልጫ እንዳለው ተገለጸ
ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ይፋ ባደረገው የ"መሣሪያዎች ስርጭት" (Device Pe*******on) ዳታ መሠረት፣ በሀገሪቱ ካሉ ዘመናዊ ስልኮች (Smartphones) መካከል የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በከፍተኛ ደረጃ የበላይነቱን ይዟል።
በአጠቃላይ 90 ሚሊዮን የተገናኙ መሣሪያዎች ባሉበት በዚህ ሪፖርት፣ የስልኮቹ የገበያ ድርሻ እንደሚከተለው ቀርቧል፡
• አንድሮይድ (Android): በአጠቃላይ በስማርት ስልኮች ገበያ ውስጥ 96.3% የሚሆነውን ድርሻ በመያዝ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል። ይህ ማለት በሀገሪቱ ካሉ 100 ስማርት ስልኮች ውስጥ 96ቱ የአንድሮይድ ስልኮች ናቸው።
• አይፎን (iOS): የአፕል ምርት የሆነው አይፎን የ2.3% የገበያ ድርሻ ብቻ እንዳለው ተመልክቷል።
በሀገሪቱ ካሉ ጠቅላላ መሣሪያዎች ውስጥ 42.2% የሚሆኑት ስማርት ስልኮች ናቸው። ከስማርት ስልኮች በተጨማሪ ፊውቸር ፎኖች (29.1%) እና ቤዚክ ፎኖች (26.6%) አሁንም ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። 29.7 ሚሊዮን የሚሆኑ መሣሪያዎች የ4G (LTE) የኢንተርኔት አገልግሎትን የመደገፍ አቅም አላቸው።
ይህ መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ የዲጂታል ገበያ ውስጥ የአንድሮይድ ስልኮች ተደራሽነት እጅግ ሰፊ ሲሆን፣ የአይፎን ተጠቃሚዎች ቁጥር ግን አሁንም በጣም አነስተኛ መሆኑን ያረጋግጣል።
source: Fast Mereja
30/01/2026
ጎግል በAI መተግበሪያው Gemini ላይ ሰዎች በነፃ የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተናን መለማመድ እንደሚችሉ አስታወቀ።
ጎግል ፕሪስተን ሪቪው ከተሰኘ የትምህርት ተቋም ጋር በመተባበር ሰዎች በGemini የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተናን (SAT) በነፃ እንዲለማመዱ ማስቻሉን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ከሚወስዷቸው ፈተናዎች አንዱ የሆነው የአፕቲቲዩድ ፈተና፣ በርካታ የውጪ ሃገር ኮሌጆችም ተማሪዎችን ለመቀበል የሚሰጡት ፈተና ነው።
ጎግል በAI መተግበሪያው የመለማመጃ ፈተናን ይፋ ያደረገ ሲሆን ተጠቃሚዎች " I want to take a practice SAT test” የሚለውን "prompt" በመጠቀም የመለማመጃ ፈተናውን ማግኘት ይችላሉ።
የመለማመጃ ፈተናውን ከጨረሱ በኋላም Gemini ተፈታኞች የቱ ጋር ጥሩ እንደሆኑና የቱ ጋር በይበልጥ ማጥናት እንዳለባቸው ግብረ መልስ ይሰጣቸዋል ሲባል፣ ትክክለኛ ምላሾች በሚጠይቁበት ወቅትም ከማብራሪያ ጋር ምላሽ ይሰጣል።
ጎግል ለጊዜው የአፕቲቲዩድ ፈተናን ይጀምር እንጂ ተጨማሪ ፈተናዎችን ወደፊት እንደሚያካትት ገልጿል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addis Ababa