Tufa Tumicha
From Xexicha
05/10/2024
ኢሬቻ የልምላሜና ተስፋ አመላካች መጻኢን ለስኬት ማዘጋጀት በመሆኑ ሁላችንም ከዚህ በዓል ዕሴቶች ብዙ በመማር፣ያሉንን አቅሞች አሰባስበን ተስፋን መያዝ ያሰፈልጋል፡-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
***************
ኢሬቻ የልምላሜና ተስፋ አመላካች መጻኢን ለስኬት ማዘጋጀት በመሆኑ ሁላችንም ከዚህ በዓል ዕሴቶች ብዙ በመማር፣ ያሉንን አቅሞች አሰባስበን ተስፋን መያዝ ያሰፈልጋልሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊ ፣ ታሪካዊ፥ የምስጋናና የፍቅር፥ የደስታናየሰላም ፣ የእርቅናየወንድማማችነትእና እህትማማችነት ተምሳሌት የሆነዉ ኢሬቻ በዓል - ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የነገ ተስፋ የብርሃን ጮራ ነው ።
አዲሱ ዓመትና የምስጋና በዓል የሆነው እሬቻ በዓል የኦሮም ህዝብ ጭጋጋማውን ክረምት ወቅት አልፎ በሰላም ወደ አዲሱና የብርሃን ተስፋ ወደያዘው ዓመት በሰላም ላሸጋገረ ለፈጣሪ''ዋቃ'' ምስጋና የሚያቀርቡበት በዓል ነው።
የኦሮሞ ህዝብ የኢሬቻ በዓል የሚያከብረው ለዋቃ ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡
ዋቃ ክረምቱን በሰላም ስላሳለፈልንና ከሰማይ ባዘነበው ውሃ መልካም ፍሬ ስለሰጠን ያለ ክፍያ በቸርነቱ ለሚንከባከበን አምላክ ምስጋና ማቅረብ ተገቢ ነው ይላል የኦሮሞ ህዝብ።
የኦሮሞ ህዝብ ችግር ሲገጥመው አቤቱታውን የሚያቀርበው “ለዋቃ” ነው፡፡ በደስታ ጊዜም ተሰብስቦ “ዋቃ”ን ያመሰግናል፡፡ኢሬቻ የዚህ ዓይነቱ የምስጋና ማቅረቢያ በዓል ነው፡፡
ኢሬቻ በክረምቱ የወንዞች ሙላት ምክንያት ተቆራርጠው የነበሩ ቤተ ዘመዶችና ልዩ ልዩ ጓደኛሞች የሚገናኙበት በዓል ነው፡፡ በበዓሉ የተገኙት ሁሉ ይቅር የሚባባሉባት፣ ፀበኞች የሚታረቁበት፣ ቂምና ቁርሾ የሚተውበትና የተጣሉ ይቅርታ የሚደራረጉበት ድንቅ የሆነ የሰላም ግንባታ ተምሳሌት በዓል ነው።
ኢሬቻ በዓል የሁሉም ህዝቦች በመካከላቸው ያለውን የኃይማኖትና የፖለቲካ ልዩነት ጥለው የአንድ አባት ልጆች መሆናቸው የሚገልጽበት ስፍራ ነው።በእሬቻ በዓል ላይ አምላኩን ከማመስገን ደስታን ከመግለፅ ውጪ የግል ወይንም ቡድናዊ ፊላጎት ማንፀባረቅ በበዓሉ አይፈቀድም።
የኢሬቻ በዓል መልካም የስራ ፍሬ የሚሻትበት ፥እንኳን ከጨለማ ወደ ብርሃን አሸጋገረን ተብሎ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ደማቅ ባህላዊ ክዋኔ የሚታይበት ብቻም ሳይሆን ልምላሜ የሚወደስበት ፤ለልማት ፥ለፍሮያማነት፥ ሰርተው ለመለወጥና ለማደግ ተስፋ የመሰነቅ የባህላዊ እሳቤና አንድምታን ያቀፈ በመሆኑ የሀገራችንን ልማት ለማፈጠን ሁላችንንም በአንድነት ለማስተሳሰር እምቅ አቅም ያለው ባህላዊ ትውፊት ነው።
ኢሬቻ የልምላሜና ተስፋ አመላካች መጻኢን ለስኬት ማዘጋጀት በመሆኑ ሁላችንም ከዚህ ከኢሬቻ በዓል ዕሴቶች ብዙ በመማር ያሉንን አቅሞች አሰባስበን ተስፋን መያዝ ያሰፈልጋል።
ኢሬቻ ባህላዊ ክዋኔ የሚታይበት በዓል ብቻ አይደለም። ይልቁንም የምስጋና፣የእርቅ፤የሠላምና የአንድነት በዓል በመሆኑ ከዚሁ በመማር በሀገራችን እየተከሰተ ያለው እርስ በርስ መጠላለፍ፣መጠፋፋትና መገፋት ጠፍተዉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አንድነታችን ማጠናከር አለብን፡፡
ኢሬቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ እርቅና ሰላም ለማስፈን የሚረዳና የሚጠቅም ትምህርታዊ ፋይዳዉ የላቀ በመሆኑ ጠብቀውና አንከባክበዉ ለትዉልዱ ማስተላለፍና በህብረብሔራዊ አንድነታችን መሀል ማስረፅ ይገባል እላለሁ፡፡
ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ የሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ከተማ በሚከበረው የሆራ አርሳዲ ኢሬቻ በዓል የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነትና የአብሮነት በዓል እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።
አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
መስከረም 24፤ 2017
19/09/2024
19/09/2024
09/09/2024
09/09/2024
09/09/2024
ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተዘዋወረ የሚገኘው የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ እና አዲስ የደሞዝ ስኬል ስሌት ትክክለኛ ነው
ባለፉት ሰአታት ውስጥ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አንድ የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ ነው የተባለ ምስል እንዲሁም አዲሱን የደሞዝ ስኬል ያሳያል ተብሎ የተገለፀ ስሌት በስፋት ሲያጋሩ ተመልክተናል።
ደብዳቤው በሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተፈረመ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ለጠ/ሚር ቢሮ ተልኮ ሲቪል ሰርቪስ ደግሞ ኮፒ እንደተደረገ ይገልፃል።
የደብዳቤውን እና ተያይዞ የቀረበውን ስሌት ትክክለኛነት እንድናጣራ በርካታ ተከታታዮቻን ጥያቄ አቅርበውልናል።
እኛም በዚህ ዙርያ አሁን ላይ ለሚድያ መረጃ መስጠት ባይፈቀድላቸውም ያነጋገርናቸው ምንጮቻችን ሁለቱም (ደብዳቤው እና የደሞዝ ጭማሪ ስሌቱ) ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠውልናል።
የደብዳቤው ይዘት ሲጠቃለል ለታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ከ91.4 ቢልዮን ብር በላይ እንደተመደበ እና ጭማሬው ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ይገልፃል። በፋይናንስ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ተጠንቶ የቀረበው የደሞዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡም ተመላክቷል።
በአዲሱ ስሌት መሠረት ነባር ደሞዛቸው በጣም ዝቅተኛ የነበረው እና 1,100 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ332 ፐርሰንት ጨምሮ 4,760 ብር እንደሚሆን ያሳያል።
በሌላ በኩል ደሞዛቸው ከፍተኛ የነበረው እና 20,468 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ5 ፐርሰንት ጨምሮ 21,491 ብር እንደሚሆን ይጠቁማል።
ከሳምንታት በፊት ጭማሬውን ያሳያል የተባለ የተሳሳተ መረጃ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ቼክ
08/09/2024
እሁድ አይቀረም!!!🔥🔥🔥💐🌼🌼🍇🍒🍇🍊🫛🍊🍒🍇💐🍒🍇🫛🍊🌻🌼🌸🌺🌼🌼🌻🌼🌸🌺🌼🌻🌼🌸
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa