Alie Assefa

Alie Assefa

Share

“መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ።”

06/03/2026

እንዲህ ሊሆን ነውና እንኳን ደስ ይበለን ብዬ እኮ ነው።

መልካም ቀን።

28/05/2024

ሁለቱ ታላላቅ ተስፋዎች እነዚህ ናቸው፦

፩ኛ. የመለከቱን ድምጽ የሚሰሙቱ ታማኝ አማኞች ስብስብ/የእውነተኛይቱ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ወደ በጉ ሰርግ በአየር ላይ መነጠቅ፣

፪ኛ. የክርስቶስና ቅዱሳኑ በምድር ላይ ለመንገሥ ሁሉም ነዋሪዎች እያዩ ወደ ምድር ዳግም መመለስ( ዳግም ምጽአት)

የክርስቶስ ከድንግል መወለድ እውን ሆኖ እንዳለፈ ሁሉ የክርስቶስ ዳግም ምጽአትም እርግጥ ሊሆን በደጅ ነው።

እያንዳንዷን ዕለት ዛሬ የመጨረሻ እንደሆነ እያሰብን በንጽሕና፣ በቅድስና፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ኃያል ስም መልካሙን ተጋድሎ እንኑር።

ቃሉንም ዕለት በዕለት በመንፈሳዊነት እንመገበው።

ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤

“የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤”
— ማቴዎስ 24፥30

ራእይ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።
¹² ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
¹³ በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።
¹⁴ በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።
¹⁵ አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።
¹⁶ በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።
¹⁷-¹⁸ አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፥ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፦ መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
¹⁹ በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።
²⁰ አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
²¹ የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።

27/05/2024

ጌታ በደጅ ነው። ነቅተን የመለከቱን ድምጽ ለመስማት የተዘጋጀን እንሁን። በሥጋዊ መሠረት አንታለል። ሕይወት መንፈሣዊ እንጂ ሥጋዊ አይደለችም። ሥጋዊነት የሞት ባላባት ነው። መንፈሣዊነት ግን ከጌታ ጋር ለዘላለም የንጉሥ ክህነትን ተቀብሎ መኖር ነው። የዘላለም ሕይወትን አንጣል። የዘላለም ሕይወትን እንምረጥ።

1ኛ ተሰሎንቄ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።
¹⁴ ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።
¹⁵ በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤
¹⁶ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
251