DireTube

DireTube

Share

DireTube.com is the #1 Ethiopian Video Sharing Site. DireTube is an Ethiopian media and entertainment website founded on October 26, 2008.

11/06/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአዳዲስ ተሽከርካሪዎች ብቻ እየሰጠ የሚገኘው የአዲሱ ሰሌዳ (ታርጋ) ዋጋ እስከ 56 ሺ ብር እንደሚደርስ ተነግሯል።

​የዋጋ ዝርዝሩ እነኾ:-

​🚗 ለግል (የቤት)፣ ለንግድ፣ ለዲፕሎማት እና ለዕርዳታ ድርጅቶች፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 56,000 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 44,500 ብር

​🚚 ለድንበር ተሻጋሪ ጭነት፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 28,500 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 15,200 ብር

​🚕 ለሕዝብ ታክሲ፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 11,700 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 9,400 ብር

​🚌 ለአውቶቡስ፣ መንግሥት፣ አካል ጉዳተኛ እና ባጃጅ፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 9,400 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 7,100 ብር

​🏍 ለሞተርሳይክል፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 4,700 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 3,550 ብር

#ጥያቄ

የአዲሱን ሰሌዳ ተመን (ክፍያ) እንዴት አገኙት?

Photos from DireTube's post 11/06/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓት መጠናከሩን ገለጸ። በአባላቱ መካከል ያለው የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓት ሙያዊ የስነ-ምግባር ጥሰቶች በምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት እንዲታዩ እድልም ፈጥሯል።

ምከር ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓትን ይበልጥ ለማጠናከር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከጂአይዜድ ኢትዮጵያ (GIZ Ethiopia) ጋር በመተባበር በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። በዛሬው ዕለትም በጂአይዜድ ኢትዮጵያ ድጋፍ የተዝጋጀ ምከር ቤቱንና ስራዎቹን ለማስተዋወቅ የሚያግለግሉ የመልቲ ሚዲያ ውጤቶች ርከከብ ተካሂዷል፡፡

በጀርመን መንግሥት ስም እና የጀርመን የልማት ትብብርን (German Cooperation) በመወከል ጂአይዜድ ኢትዮጵያ (GIZ Ethiopia) የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓት እንዲጎለብትና የግልግል ዳኝነት አካል ዋና ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚረዱ በርካታ ድጋፎችን አድርጓል፡፡ ከድጋፎቹ መካከልም ህብረተሰቡ በተላለፊ ዜና:ማስታዎቂያና ፕሮግራም ላይ የሚስተዋሉ የሚዲያ የስነ-ምግባር ጥሰቶችን ለምከር ቤቱ ሪፖርት የሚያደረግባቸውን አማራጮች ማስተዋወቅና ተደራሽ ማድረግ ይገኙበታል፡፡

የዚህ አጋርነት አካል የሆነው እና የምክር ቤቱ _ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን እንዲሁም የተቋሙን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚረዳ ድረ-ገጽ በአዲስ መልክ የማዘመን ስራም በስኬት ተጠናቋል።

ምክር ቤቱ ከጂአይዜድ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከሚዲያ የስነ-ምግባር ጥሰት ጋር የተገናኙ ቅሬታዎች ለምከር ቤቱ የግልግል ዳኝነት አካል በቀላሉ የሚቀርቡበትን አሰራር ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ በ32 የማህበረሰብ ሬዲዮ እና በአምስት የማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ማስታወቂያዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ሲያስራጭ ቆይቷል።

የምከር ቤቱን የሰው ሃይል በማጠናከር፣ የቅሬታ ማቅረቢያ ዘዴዎችን በማዘመንና በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ በማድረግ፣ የተቋሙን ሎጎና ብራንድ በማሻሻል እንዲሁም የግልግል ዳኝነት አካሉን በማጠናከር ረገድ ከጂአይዜድ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር አመርቂ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በተሰሩት የሚዲያ ዘመቻዎች ምክንያት ህብረተሰቡ በመገናኛ ብዙሃን ይዘቶች ላይ የታዩ የስነ-ምግባር ጥሰቶችን ለምክር ቤቱ እያመለከተ ሲሆን፤ ምከር ቤቱም በቀረቡት ቅሬታዎች ላይ ውሳኔ እየሰጠባቸው ይገኛል፡፡

በዚህ መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 25 ከጋዜጠኝነት የስነ-ምግባር ጥሰት ጋር የተገናኙ ቅሬታዎች ለምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት አካል ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ህብረተሰቡ እነዚህን ቅሬታዎች ያቀረበው በህዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች:በንግድ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች:በህዝብ የህትመት ጋዜጦች እና በበይነ-መረብ ሚዲያዎች ላይ ነው።

ምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት ስራዎችን በማጠናከር በመገናኛ ብዙሃን ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ የሰነ-ምግባር ጥሰቶች እንዲታረሙና ሙያዊ አሰራሮች እንዲጉለብቱ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምከር ቤት የግልግል ዳኝነት አካል ከተለያዩ የሙያ ማህበራት እና የህብረተሰብ ከፍሎች የተወጣጡ 18 አባላት ያሉት ፓናል ነው፡፡

የርክክብ ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በጀርመን መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እና በጂአይዜድ (GIZ) የመልካም አስተዳደር በኢትዮጵያ ፕሮግራም አስተባባሪነት ነው፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሥነ ምግባር የታነጸና በሃላፊነት ስሜት ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ በሀገራችን እንዲጎለብት የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ በሕግ ተመዝግበው ፈቃድ የወሰዱ ከ120 በላይ የህዝብ ፤የንግድ፤ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንን፤ የበይነ መረብ ሚዲያንና የጋዜጠኞች ሙያ ማህበራትን በአባልነት በማቀፍ የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።
#ድሬቲዩብ

Photos from DireTube's post 11/06/2026

በ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ10.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል - አቶ አሕመድ ሺዴ

ኢትዮጵያ ከይፋዊ አበዳሪዎች ጋር የተጀመረው የውጭ ዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ መድረሱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2019 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድን ለውይይት ባቀረቡበት ወቅት ነው።

የመንግሥትን የውጭ ብድር ጤናማ ለማድረግ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የተጀመረው የዕዳ ሽግሽግ ሂደት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ በዋና ዋና የፋይናንስ መለኪያዎች ላይ የተደረሰውን ስምምነት መሠረት በማድረግ የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከአብዛኞቹ አበዳሪዎች ጋር የሁለትዮሽ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነቶች ተፈርሟል።

ከዩሮቦንድ እና ከሌሎች አበዳሪዎች ጋር የሚደረገው ድርድርም ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረቡን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ይህም በየዓመቱ ለዕዳ ክፍያ የሚውለውን የውጭ ምንዛሬ ጫና በመቀነሱ ለኢትዮጵያ የልማት ፋይናንስ ተጨማሪ ሀብት ለማዋል ማገዙን እና የሀገራችን የዕዳ ጫና ስጋት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ እንደሚያደርገው አስረድተዋል።

በመጠናቀቅ ላይ ባለዉ 2018 በጀት ዓመት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ምርታማነት እና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን አቶ አሕመድ ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አማካኝነት ከግሉ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክት መጀመሩን እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚከናወነውን የቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክትን በዋነኛነት ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ እየታየ ያለው አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ካለፉት ዓመታት እጅግ የተሻለ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ በዚህም መሰረት በ2019 በጀት ዓመትም የ10.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመዘገብ ግምት መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

11/06/2026

መንግስት ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም በሚጀምረው በጀት ዓመት፤ ከታክስ ገቢ ወደ 1.5 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱ ታወቀ፡፡

በበጀት ዓመቱ መንግስት ለጠቅላላ ገቢ የውጪ ብድርን ጨምሮ ከ2 ትሪሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ እንዳቀደ ዛሬ ወደ ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ የሚጠበቀው የፌደራል መንግስት የ2019 የገቢ በጀት ረቂቅ ሰነድ ያሳያል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ጠቅላላ ገቢ የውጪ ዕርዳታን ጨምሮ 1.8 ትሪሊዮን ብር እንደሚሆን ተገምቷል የሚለው ሰነዱ ይህም በ2018 በጀት ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ ከተገመተው ጠቅላላ ገቢ አንጻር የ17.4 በመቶ እድገት ያለው እንደሆነ ዘርዝሯል፡፡

ከዚህ ውስጥ 1.5 ትሪሊዮን ብር ወይም 82 በመቶው ከታክስ ገቢ እንደሚሆን አስረድቷል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

ጠቅላላ ገቢና ዕርዳታ 1,816,550,478,151 ብር፣

ከምንዳና ደመወዝ 97,346,528,758 ብር ፣

የአገር ውስጥ ቀጥታ ታክሶች 427,487,817,419 ብር፣

ከኪራይ ገቢ ግብር 2,589,596,337 ብር፣

ከኮርፖሬት ድርጅቶች የንግድ ሥራ ገቢ ግብር 263,009,567,243 ብር፣

ከገቢ ዕቃዎች የቅድሚያ ገቢ ግብር 26,627,285,968 ብር፣

ከአገር ውስጥ ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች 277,988,904,983 ብር፣

በአገር ውስጥ ከሚመረቱ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ 225,535,497,927 ብር፣

በአገር ውስጥ ከሚመረቱ ዕቃዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ 113,422,746,069 ብር፣

ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 3,639,722,663 ብር፣

ከስኳር 2,362,600,874 ብር መንግስተ ለመሰብሰብ ማቀዱን የ2019 በጀት ረቂቅ ሰነድ ያሳያል።

አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የ2019 ጠቅላላ ወጪ በጀት ብር 2.3 ትሪሊዮን ሲሆን፣ ይህም በ2018 በጀት ዓመት ከፀደቀው የወጪ በጀት አንጻር የብር 411.5 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ወይም የ21.3 በመቶ ዕድገት አለው፡፡

የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ወጪ እቅድን በተመለከተ ደግሞ ለመደበኛ ወጪ 1.2 ትሪሊዮን ብር ፣ለካፒታል ወጪ 568 ቢሊዮን ብር ተመድቧል፡፡

የካፒታል ወጪ በጀቱ ከመደበኛ በጀቱ በግማሽ ያንሳል፡፡

ከቀረበው ጠቅላላ የፌዴራል መንግስት የወጪ በጀት ውስጥ 52.9 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ ለመደበኛ በጀት የተመደበ ነው፡፡

ይህም በ2018 በጀት ዓመት ለመደበኛ በጀት ከተመደበው አንጻር የ16.5 በመቶ ዕድገት አለው።

ከዚህ ጠቅላላ የመደበኛ ወጪ ውስጥ ብር 542.1 ቢሊዮን ወይም 43.8 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ የተደለደለው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ዕዳ ክፍያ ሲሆን፣ 236.4 ቢሊዮን ብር ወይንም 19.1 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለማዳበሪያና ለነዳጅ ድጎማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅትን ካፒታል ለማሳደግ የተመደበ በጀት እንደሆነ ሰነዱ አመላክቷል፡፡

520.6 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊና ክልላዊ መንግሥታት የበጀት ድጋፍ እንዲሁም 14 ቢሊዮን ብር ለክልሎች ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የተመደበ በጀት እንደሆነ ተጠቅሷል

የቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የተጣራ የበጀት ጉድለት 308.6 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 5.7 ቢሊዮን ብሩ ከውጭ እና 302.9 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ የተጣራ ብድር በመውሰድ እንዲሸፈን የታቀደ ነው፡፡

ይህም የተጣራ የበጀት ጉድለት ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 1.4 በመቶ እንደሆነ ያሳያል፡፡

(ያሬድ እንዳሻው - ሸገር ኤፍኤም)

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa