Addis Ababa University

Addis Ababa University

Share

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Photos from Addis Ababa University's post 06/05/2026

ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የጥናት፣ የምርምር እና የሥራ አውደ ርዕይ ሳምንት ተከፈተ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 7ኛው የምርምርና የሥራ አውደርዕይ ሳምንት "Advancing Education through Research Digitalization Innovation and Industry partnerships" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ የመክፈቻ መርሀ ግብር ተከፍቷል።

የዘንድሮው የምርምር ሳምንት በዩንቨርሲቲው እየተተገበረ ከሚገኘው የ5 አመቱ ስትራቴጂክ እቅድ ጋር የተጣጣመ አላማ ያለው መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ገልጸዋል።

አውደ ርዕዩ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት የተሰጠውን የዲጂታላይዜሽን እንቅስቃሴ ለትምህርት ስርዓት፣ ለፈጠራ እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር ማስተሳሰር ላይ ያተኮረ የምርምር ሳምንት መሆኑን የዘንድሮው የምርምር ሳምንት ዋና አዘጋጅ የሆነው የትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ኤክስኩቲቭ ዲን የቆየአለም ደሴ (ዶ/ር) ጠቁመዋል።

በዕለቱ ከመክፈቻው መርሀ ግብር ጎን ለጎን የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የዪኒቨርሲቲውን ምሁራን ያካተተ በሀገሪቱ የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
በቀጣይ ቀናት በሚኖሩ መርሃ-ግብሮች የተለያዩ ኮሌጆች ምሁራን የተሰሩ የምርምር ውጤቶች የሚቀርቡ ሲሆን የላቀ ግኝት ላገኙ እውቅና የመስጠት መርሃ ግብርም የሚካሄድ ይሆናል።

Photos from Addis Ababa University's post 24/04/2026

የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከልን (China-Africa Research Center) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ትብብር የሚቋቋመው ይህ ማዕከል በቻይና እና በአፍሪካ መካከል ያለውን አካዳሚያዊ ትብብር በማጠናከር፣ የባህል ልውውጥን ለማሳደግ እና የጋራ የምርምር ሥራዎችን ለማከናወን ያለመ ነው።

የማዕከሉ መቋቋም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ለዓመታት የዘለቀ ጠንካራ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውጤት መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ወቅት ገልጸዋል።

የቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት ክቡር ዬ ሃይሊንግ (Ye Hailing) በበኩላቸው ማዕከሉ በቻይና መንግሥት ከሚደገፉት 25 የቻይና-አፍሪካ ምርምር ማዕከላት መካከል እንዱ መሆኑን ጠቅሰው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነትም ይበልጥ እንደሚያጠናክረውም ጠቁመዋል።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa University
Addis Ababa
1176