Ethio Newsflash

Ethio Newsflash

Share

ኢትዮ ኒውስፍላሽ በጋዜጠኞች ሚዛናዊ፣ አዳዲስ እና ፈጣን መረጃዎችን ለአንባቢዎች ያደርሳል።

Photos from Ethio Newsflash's post 23/08/2022

#ኒውስፍላሽ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ) ያቀረበውን የምዝገባ ፈቃድ ከለከለ!

ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በእነአቶ ዮሐንስ ታደሰ በቁጥር 001/ምቦ/01/14 በተጻፈ ደብዳቤ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የሀገር ዐቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ እንዲሰጣቸው አመልክተው ነበር።

በዚህም መሠረት ቦርዱ ኢ.ሠ.ፓ በሚል ስያሜ ሀገራዊ ፓርቲ ለማስመዝገብ የቀረበለትን ጥያቄ በምርጫ ዐዋጁ አንቀጽ 69(1) ለ መሠረት ክልከላውን አሳውቋል። ለዝርዝሩ ደብዳቤው ተያይዟል።

23/05/2022

ግንቦት 30 በካፒታል ሆቴል በሚካሄደው የጣፋጭ ሕይወት ሽልማት ላይ የእርሶ ማህበራዊ ሚድያውን ለመልካም ምግባር የተጠቀመው ማን ነው?
ኮሜንት ያድርጉ ግንቦት 30 በካፒታል ሆቴል በደማቅ ስነ ስርዓት ሽልማቱ ይሰጣል።
#ቅን ልባዊ ድርጊት
ለጣፋጭ ህይወት

21/05/2022

#ኒውስፍላሽ የጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬን እስር/አፈና በተመለከተ ኢትዮ ኒውስፍላሽ ከእህቱ ትግስት ሹምዬ ጋር ያረገው አጭር ቃለመጠይቅ

ትናንት ጠዋት ምን ነበር የተከሰተው?
ትግስት: ጠዋት ላይ ለሰለሞን እንደሁሌው ቁርስ ላደርስለት ስሄድ በር የሚያንኳኳ ሲቪል የለበሰ ሰው አገኘሁ። ምን እንደሚፈልግ ስጠይቀው ሊነግረኝ አልፈለገም፣ ከዛም ሄደ። እኔም ወደቤቴ ተመልሼ ኋላ ላይ ቆየት ብዬ ሰለሞን ቤት ስመለስ ሌሎች ሲቪል የለበሱ ሰዎችን አገኘሁ። በግድ ቤቱን ክፈቺ አሉኝ፣ እኔ ደግሞ ስለተጠራጠርኩ ለጎረቤቶች ፖሊስ እንዲጠሩ ነገርኳቸው። መታወቂያ እንኳን ሊያሳዩኝ አልፈለጉም። ፖሊሶች ሲመጡ ግን እያመናጩቁኝ ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱኝ።

ሰለሞን እንዴት ተያዘ?
ትግስት: ሰለሞንን ፖሊስ ጣብያ ነው ያገኘሁት። ስልኩን ቀምተው ከዛም ቤቱ ፍተሻ አርገዋል። ምንም ነገር አላገኙም። ሰለሞን ከመጣ በኋላ ሁለት ሰአት አቆይተው እኔን ለቀቁኝ።

ሰለሞን አሁን የት ነው?
ሶስተኛ ፖሊስ ጣብያ ነው። ምግብ እና ልብስ አድርሼለታለሁ።

ፍርድ ቤት ዛሬ ምን ተባለ?
ትግስት: ዛሬ ጠዋት ሶስተኛ አካባቢ ያለው ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ቃል በቃል ባላስታውሰውም ብጥብጥ እንዲፈጠር አነሳስተሀል ምናምን የሚል ክስ አንብበዋል፣ ክሱ ለብቻው ሳይሆን ሌሎችን ስዎችን ያካተተ ነበር።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


4 Kilo
Addis Ababa